Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2021
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for April 19th, 2021

የቀን ጅቦች (የግራኝ ሰአራዊት) ንጉሥ አንበሣን (አክሱም ጽዮንን) ከብበው አጠቁት ከዚያ…

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 19, 2021

የአባ ዘ-ወንጌልን መልዕክት የ666ቱ ጭፍሮች ለራሳቸው አጀንዳ ያመቻቸው ዘንድ እንዳሰኛቸው ጠምዝዘው ሲያቀርቡት ይታያሉ። 👉 አባታችን አባ ዘ-ወንጌል የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል በማለት ጉዳዩን እነ ዘመድኩን በቀለ ለተከታዮቻቸው በተደጋጋሚ ሲያወሱት ነበር። ስለ አባ ዘ-ወንጌል የተወራው ሁሉ ትክክል አይደለም የማለት ድፍረት የለኝም፤ ሆኖም እራሳችንን መጠየቅ ያለብን፤ “እባቡ ግራኝ አብዮት አህመድና እንደ ጋንኤል ክስረት እና ገመድኩን ሰቀለ ያሉት ካድሬዎቹ ተዋሕዶ ክርስቲያኑን የትግራይን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ አስቀድመው ያወጡት ጽሑፍ/ስክሪፕት ቢሆንስ? “የራሳችሁ አባት አባ ዘ-ወንጌል የተነበዩት ነውና ጭፍጨፋውንም፣ የዓብያተ ክርስቲያናትና ገዳማቱን ውድመትም ተቀበሉ፤ በሃጢአታችሁ ነውና፤ አሁን ለደህንነታችሁና ብልጽግናችሁ ስትሉ በሉ ጴንጤ ሁኑ” ብለው ተንኮለኛው ፈላስፋ ጆርጅ ሄገል ያረቀቀላቸውን “ችግር – ምላሽ – መፍትሔ / “Problem – Reaction – Solutionየተባለውን መመሪያ ተከትለው ቢሆንስ? መቼስ ይህን እንደሚያደርጉት አልጠራጠረም።

💭 አባ ዘ-ወንጌል ‘አስተላልፈውታል’ የተባለው መልዕክት እንዲህ ይላል፦

በአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያ ትወረራለች። ሰላም በማስከበር በሚል ሰበብም በ፪/2 ሃያላን ሀገራት የሚመሩ ሰባት የሙስሊም ሀገራት በኢትዮጵያ ምድር ላይ እሳት ያዘንባሉ። በአሰብ ወደብ ላይ በልዩ ሁኔታ የተከማቸው የጦር መሣሪያ በኢትዮጵያ ምድር ላይ እንደበረዶ ይዘንባል። ብዙ ፍጅትም ይሆናል። ኦርቶዶክሳውያን በያሉበት፣ በየተገኙበት እንደከብት ይታረዳሉ። የኢትዮጵያ ምድር በደም ትጨቀያለች። የደም ጎርፍ፣ የደም አበላ በምድሪቱ ላይ ይፈሳል።”

👉 ሰባቱ የሙስሊም ሀገራት እነ ግራኝ ትግራይን ለመጨፍጨፍ ገና ከሦስት ዓመታት በፊት የሰበሰቧቸው እነዚህ የጅቦች መንጋ ሰራዊት አይደሉምን?

🔥 አማራ

🔥 ኦሮሞ

🔥 መናፍቅ

🔥 እስላም/አረብ

🔥 ኤርትራ

🔥 ሶማሊያ

🔥 ብሔር ብሔረሰቦች

የይሁዳ አንበሣን (አክሱም ጽዮን)ከብበው አጠቁት፤ በመጨረሻም ረዳቱ/ረዳታችን (መንፈስ ቅዱስ) ደረሰለት። ነጫጮቹን እርግቦች አየናቸው?

ያዘው! በለው! ስቀለው!”ሲሉ የነበሩት መቶ ጅቦች ፈረጠጡ! ሦስቱ አንበሦች ግን አንድ ሆነው ንጉሥነታቸውን አረጋገጡ!

ዲያብሎስ የአክሱም ጽዮን ልጆች የእርሱ አለመሆናቸውን ቆጭቶት እነርሱን ለመጣል ብሎ ለዘመናት በተለያየ መንገድ ተፈታተናቸው[ማቴ.፬፥፫]፡፡ ጌታችንን ከሀገራቸው እንዲሄድላቸውና ወደ ግብጽ እንዲሰደድ እንደ ለመኑት፤ የአክሱም ጽዮን ልጆችንም የክርስቶስ በመሆናቸው ከሀገራቸው እንዲወጡላቸው እያደረጓቸው ነው፤(ማቴ.፰፥፴፬)፡፡ የይሑዳ አንበሣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን “ጋኔን አለበት”(ሎቱ ስብሐት!)እንዳሉት ለአክሱም ጽዮን ልጆችም የተለያየ ስም እየሰጧቸው በመጥፎ እና በጠላትነት እንዲታዩ አደረጓቸው፤[ዮሐ.፲፥፳]፡፡ የይሑዳን አንበሣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በቅንዓት ተነሣሥተው “ይሰቀል ይሰቀል” እንዳሉት፤ እንደዚሁ የክርስቶስ ተቃዋሚው የግራኝ አህመድ የአህዛብ አገዛዝም በተለያየ መንገድ አመካኝቶ ግርግር አንሥቶ፣ መነሻውም ሰሜን ዕዝ እንደ ሆነ ዋሽቶ መንጋ ተከታይ መንጋውን “ያዘው! በለው! ይወገሩ፣ ይቀጥቀጡ! ግደላቸው!” እያስባለ የአክሱም ጽዮን ልጆች የክርስቶስ በመሆናቸው ብቻ እግዚአብሔር በሰጣቸው ምድር ገረፏቸው፣ ደፈሯቸው፣ አስራቧቸው፣ ጨፈጨፏቸው[ማቴ.፳፯፥፳፪፡፳፫]፡፡

ገና ከልጅነታችን በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠምቀን ክርስቲያን የሆንን ሁሉ ከእኛ ጋር ያለውን፣ “በኪሳችን የያዘነውን” ተንከባክበን ወደ ውስጥ ከተመለከትን ከውጭ ያለውና አላፊና ሰብዓዊ ከሆነው እርዳታ መጠበቅ አይገባንም/ አያስፈልገንም። ይህ ሰው፣ ይህ ሕዝብ፣ ይህ ተቋምና ድርጅት ለምን ስለኛ መከራ እና ሰቆቃ አልተናገረልንም? ለምንስ ለእርዳታ ከእኛ ጋር አልቆሙልንም? እያልን እራሳችንን የሚያጽናናን፤ ማለትም የሚያጽናን፣ የቅርብ ረዳታችን፣ የመንገዳችን ደጋፊ፣ የነፍሳችንን ሲቃ አዳማጭና የማይለይ ታዳጊ መንፈስ ቅዱስ ሁሌ ከእኛ ጋር አለና ነው። መንፈስ ቅዱስ በማይመረመር ፍርዱ የደሀን ደም ይበቀላል፣ ፍትሕን ይተክላል፣ እውነትን ያነግሳል፣ ሀሰትን ይደመስሳል፣ በኃጢአት የከበሩትን ያዋርዳል፣ ስለጽድቅ የተዋረዱትን ግን ያከብራል።

[የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፬፥፳፮]

አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።”

✞✞✞የሐና ማርያም ወራዊ መታሰቢያ በዓል✞✞✞

[መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ ፪]

፩ ሐናም ስትጸልይ እንዲህ አለች። ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፥ ቀንዴ በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህ ደስ ብሎኛል።

፪ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለምና፥ እንደ አምላካችንም ጻድቅ የለምና፤ ከአንተ በቀር ቅዱስ የለም።

፫ አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ።

፬ የኃያላንን ቀስት ሰብሮአል፥ ደካሞችንም በኃይል ታጥቀዋል።

፭ ጠግበው የነበሩ እንጀራ አጡ፤ ተርበው የነበሩ ከራብ ዐርፈዋል፤ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው ደክማለች።

፮ እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል።

፯ እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል፤ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል።

፰ ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ።

፱ እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል ኃጥኣን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ፤ ሰው በኃይሉ አይበረታምና።

፲ ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቅቃሉ፤ በሰማይም ያንጐደጕድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፤ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።

_______________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Isaias Afewerki Stealing Donkeys from Tigray | ኢሳያስ ከትግራይ አህዮች ሲሰርቅ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 19, 2021

ትልቅ ቅሌት! እጅግ በጣም አሳፋሪ ተግባር ነው! ከግራኝ አብዮት አህመድ አሊ እና ተከታዮቻቸው ጋር ሁሉም “አሊ ባባ እና አርባ ሌቦቹ “ን ሆነዋል። እነዚህ አውሬዎችና ጭፍሮቻቸው ሞትን እስኪመኟት ድረስ ገና ብዙ ይዋረዷታል። ለምስኪኖቹ አህዮች አዘንኩ!

____________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የአረመኔው ግራኝ ኦሮሞ ሰአራዊት በመቀሌ ዝነኛውን የአፄ ዮሐንስን ትምህርት ቤት አፈራረሰው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 19, 2021

በምስጋና-ቢሱ የግራኝ ኦሮሞ ሰአራዊት በመቐለ ተዘርፎ የፈራረሰው የአፄ ዮሐንስ ፬ኛ ትምሕርት ቤት። ሰአራዊቱ ሕፃናት ተማሪዎችን አባርሮ በማስወጣት እዚህ መሽጎ ሴቶችን ይደፍርና ይገድል ነበር።

ትግራዋይ ለኦሮሞ ጠላቱ ሰርቶለት መቀሌ ገባ፤ በተቃራኒው ፥ ዓለም ተገለባብጦ፤ ከሃዲውና ምስጋና-ቢሱ ኦሮሞ ትግሬ በሰራለት ፈጣን ጎዳና አድርጎ ወደ መቀሌ ፈጥኖ በመሄድ ትግራዋይን ጨፈጨፈ፣ ትምህርት ቤቱን አፈራረሰበት። አዎ! ለትግራይዋ እና ለጀግናው ኢትዮጵያዊ ንጉሥ ለአፄ ዮሐንስ ያላቸው ጥላቻ ደም ስራቸው ውስጥ ነው። በዚህ ለቅንጣት ያህል እንኳን አንጠራጠር፤ ይህን አስመልክቶ በግል ብዙ ኡ ኡ! የሚያሰኝ ነገር አይቻለሁ። ለሌላ ቀን!

✞✞✞ዛሬ ሚያዝያ ፲፩፤ የሐና ማርያም ዕለት ነው። የዚህ ቪዲዮ ግዝፈት በተዓምር ፻፲፩/111 MB. ! ! ! ለከሃዲዎችና ለምስጋናቢሶች✞✞✞

Hell is full of the ungrateful.” ― Spanish Proverb

ሲኦል በከሃዲዎች የተሞላች ናት። ” የስፔን ምሳሌ

___________________________________

Posted in Ethiopia, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የትግራይ አባቶች ለማኅበረ ቅዱሳን | ለምን የ666ቱ ግራኝ አብዮት አህመድ ተላላኪ ሆናችሁ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 19, 2021

👉 የትግራይ ማህበረ ቅዱሳን በይፋ የፈረሰበት ከፍተኛ የማህበሩ አመራር የተገኙበት የመቐለ ጉባኤ

በፊት የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ ነበርኩ፤ ቤተ ክርስቲያን የተደራጀ ማኅበር ያስፈልጋታል የሚል እምነት አለኝና። በተለይ መናፍቃንና አህዛብ ማኅበረ ቅዱሳንን በጣም ይጠሉትና ይፈሩት ነበር። አንድ ማኅበር ወይም ግለሰብ በእነዚህ ሁለት የክርስቶስ ተቃዋሚ ቡድኖች ከተጠላ “አቤት ሲሳይ!” የሚያሰኝ በረከት ነው። ከዓመታት በፊት በመሀመዳውያን ዘንድ ወንጌልን ለመስበክና ስለ እስልምና የክርስቶስ ተቃዋሚነት ታዋቂውን ግብጻዊ አባታችንን አባ ዘካርያስ ቦትሮስን ለማስተዋወቅ ይደፍር ነበር። አባ ዘካርያስ በቴሌቪዥን ጣቢያቸው ሃምሳ ሚሊየን ለሚሆኑት ሙስሊም ተመልካቾቻቸው ስለ እስልምና ድቅ ድቅ ጨለማነት ቁርአንን፣ ሃዲስና የእስልምናን ታሪክ ከክርስትና እና መጽሐፍ ቅዱስ ጋር እያነጻጸሩ ባሳማኝ መልክ በማቅረብ በዓመት እስከ ስድስት ሚሊየን ሙስሊሞችን ከእስልምና ጨለማ አውጥተው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን ለማምጣት የበቁ ትክክለኛ የኦርቶዶክስ አባት ናቸው።

ዛሬ ግን ማኅበሩ መስመሩን እየሳተ በመምጣቱ እየተለሳለሰ ሁሉንም አቃፊ የሆነ ማኅበረ በመሆኑና ለ666ቱ አረመኔ ግራኝ አብዮት አህመድ በመንበርከኩ ለመውደቅ ገደል አፋፍ ላይ ይገኛል። ማኅበረ ቅዱሳን በዋቄዮአላህ ልጆች የተጠለፈ መስሎ ስለታየኝ ከዓመታት በፊት “ባካችሁ የላቲን ፊደል በሚጠቀመው የኦሮሙኛ ቋንቋ ፕሮግራም አትሥሩ፤ በግዕዝ ቋንቋና ፊደል ላይ ወንጀል እየሠራችሁ ነው፤ ሙስሊም ኦሮሞዎች እኮ በአረብኛው ነው ቁርአናቸውን የሚቀሩት፤ የግ ዕዙን ፊደል እስካልተቀበሉ ድረስ በኦሮምኛ ቋንቋን ማስተላለፉን ብታቆሙ ይሻላችኋል።” የሚል ደብዳቤ ጽፌላቸው ነበር። ያው ዛሬ ውጤቱን እያየነው ነው፤ ዛሬ በ “አደባባይ ሜዲያ”፣ በ “ቤተሰብ ሜዲያ” እና በሌሎችም በተዋሕዶ ስም ለኦሮሙማ ተልዕኮ የቆሙት ደቡባውያን ኢትዮጵያ ዘስጋ የዋቄዮአላህ ባሪያዎች ማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ ከዓመታት በፊት በኢሬቻ በላይ በኩል ሰርገው በመግባት ማኅበሩን በቁጥጥራቸው ሥር አውለውታል። በዋልድባ ገዳም በሺህ የሚቆጠሩት ትግርኛ ተናጋሪ መነኮሳት መባረራቸው እና በትግራይ የቅርስ ዘረፋ ዘመቻው በማኅበረ ቅዱሳን እና በጋንኤል ክስረት በኩል ሳይካሄድ አይቀርም የሚል ጥርጣሬ አለኝ።

👉 በጣም አስገራሚ ነው፤ ከወር በፊት ልክ በዚህ “የሐና ማርያም” ዕለት የሚከተሉትን ቪዲዮና ጽሑፍ አቅርቤ ነበር። አሁን የማኅበረ ቅዱሳን ዩቲውብ ቻነል ገብቼ ስዳስስ፤ በአማርኛ እና እንግሊዝኛ ብቻ እንጂ በኦሮምኛ ቋንቋ በየዕለቱ ሲቀርቡ የነበሩት ፕሮግራሞች ባለፉት ፪ ሳምንታት አልቀረቡም።

“ማህብረ ቅዱሳን የትግርኛ ቋንቋ ሥርጭቱን አቁሟልን? በአማርኛ፣ በኦሮምኛ እና በእንግሊዝኛ ብቻ ነው ፕሮግራሙን ተንኮለኛ በሆነ መልክ በማሰራጨት ላይ ያለው።”

💭 ክፍል ፩

ማህብረ ቅዱሳን የትግርኛ ቋንቋ ሥርጭቱን አቁሟልን? በአማርኛ፣ በኦሮምኛ እና በእንግሊዝኛ ብቻ ነው ፕሮግራሙን ተንኮለኛ በሆነ መልክ በማሰራጨት ላይ ያለው።

💭 ክፍል ፪

ጥምቀት ከተራ ፪ሺ፲፫ ዓ.ም

አርዮስ ኢሬቻ ጂኒ በላይ “ነጭ ለብሶ” ቤተ ክህነትን በሂደት ሲረከባት፤ እግዚኦ!

🔥 “ፈንቅል! ፈንቅል! ፈንቅል!” ሲሉን የነበረው መፈንቅሉ በተዋሕዶ እና ኢትዮጵያ (ትግራይ) ላይ መሆኑ ነው።

ወንጀለኛው እባብ አብዮት አህመድ አሊ ለ“ፈንቅል ድራማው” በመሪነት አስቀምጦት የነበረውን አቶ የማነ ንጉሴን (ነፍሱን ይማርለት!)ልከ እንደ እነ ኢንጂነር ስመኘውና ጄነራል ሰዓረ አስጠግቶት አመቺ በሆነለት ወቅት ገደለው። አሁን ያቀደውን በቅደም ተከተልና አንድ በአንድ በማስፈጸም ላይ ነው። ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ በቅርቡ የእርሱ ተራ ደርሶና በእሳት ተጠርጎ ወደ ሲዖል እስከሚወረወር ድረስ ደጋፊዎቹን ቃኤላውያኑን እያጋለጠልልንና እየገላለጠልን ያዋርድልን፣ ያቅበዝብዝልን! እኛ ሁሉንም እንመዘግበዋለን።

🔥 “ፈንቅል! ፈንቅል! ፈንቅል!”

🌑 ከሦስት ዓመታት በፊት የኦሮሞ መፈንቅለ መንግስት በአራት ኪሎ ተካሄደ

🌑 በሦስት ዓመታት ውስጥ መፈንቅለ ሠራዊት፣ ድርጅቶችና ተቋማት ተካሄደ

🌑 የመውረሱ ሂደቱ የቆየ ቢሆንም አሁን በማህበረ ቅዱሳን መፍንቅለ ማህበር ተካሄደ

🌑 ዛሬ ደግሞ መፈንቅለ ቤተ ክህነት በቅደም ተከተል እየተካሄደ ነው። እነ ኢሬቻ በላይን ቤተ ክህነትን እናወርሳችሁና ኢትዮጵያን የእግዚአብሔር ሳይሆን የዋቄዮ-አላህ-አቴቴ ምድር ታደርጓታላችሁ ፤ አትቸኩሉ መገንጠል አያስፈልግም”አሏቸው።

💭 ቀደም ሲል የቀረበ፦

✞ “በተዋሕዶ ትግራዋያን ላይ እየተካሄደ ያለው አሰቃቂ የአህዛብ ጂሃዳዊ ጭፍጨፋና ግፍ”

ሙሉው ፕሮግራም ባጠቃላይ አርባ አምስት ደቂቃ ያህል ወስዷል፤ ለትግራዋዩ የዓይን ምስክሩ ዲያቆን ቢኒያም እንዲተነፍስ የተደረገው ግን አስራ አምስት ደቂቃ እንኳን አይሞላም። ቆርጬ ያቀረበኩት ነው፤ ሙሉውን በማህበረ ቅዱሳን ቲቪ ቻነል መከታተል ይቻላል።

ሆን ተብሎ በተንኮል ተዘጋጅተውበት እስኪመስል ድረስ ቀዝቃዛና “ርህራሄአልባዎች” የሆኑት አዘጋጆቹ የሚናገሩት ነገር ሁሉ በእውነት እሬት እሬት ይላል። በብዙዎቹ ቃኤላውያን አጀንዳ ጠላፊዎች ዘንድ እንደምናየው ስለ “መተከልማይካድራ” ብቻ መናገር የፈለጉ ይመስላሉ። በቆለኞቹ ደቡባውያን እጅ ላይ የወደቀችው “ማህበረ ቅዱሳን?” ዋይ! ዋይ! ዋይ! ከፍሬያቸው እንደምናየው እንግዲህ እነዚህ አህዛብ እንጂ በጭራሽ ኢትዮጵያውያንም ተዋሕዶ ክርስቲያኖችም ሊሆኑ አይችሉም! በጣም ያሳዝናል! ዲያቆን ቢኒያም፤ የእግዚአብሔር መላእክት ይጠብቁህ!

💭 በተለይ የፕሮግራሙን ግብዝ አቅራቢዎቹ አስመልክቶ በቻነሉ ላይ የተሰጡት አስተያየቶች በተገቢ መልክ እንዲህ ገልጸውታል፦

✞ “አስመሳይ ናችሁ እናንተ ለትግራይ ያላችሁ ጥላቻ ለክርስቶስ ካላችሁ ፍቅር ይበልጣል አመንክም አላመንክም የትግራይን ቤተክርስቲይን አጥታችኃትል አይግረምህ ክርስትና እንደናንተ ከሆነ ይቅር ግብዞች የተለሰነ መቃብር ናችሁ”

✞ “ቢኒ እዚህ ሚድያ መቅረብ ኣልነበረብህም፡ እኒህ ጭራቆች ኣያስፈልጉንም”

✞ “I wonder why the reporter is interrupting the doctor while he is talking ?”

✞ “አያቹ ዲያቆን ታደስ የሚናገረው ንግግር በትግራይ ላይ ያለው ጥላቻ ዲያቆን ዶክተር ቢኒ ላስህን ጠብቕ መንፈሳዊያን ናቸው ብለህ አትእመናቸው እንዳይገድሉህ”

✞“አንዳንድ ሰዎች ትገርሙኛላቹ የጎጃም ቄስ የጎንደር ጳጳስ ስለ ትግራይ አድባራት ና ገዳማት ይጨነቃሉ ብላቹ ማሰባቹ ማህበረ ቅዱሳን እራሱ የአማራ እኮ ነው እዚ መተህ ማላዘንህ ለነሱ ደስታ ነው የሚፈጥርላቸው በዚ መጠን ጥላቻቸውን እየገለፁልህ እዚ መተህ ማለቃቀስህ ይገርማል”

✞“ቢኒያም ወንድማችን እሳት ላይ ቆመህ ስለተፈፀመው ሁሉ ቅምፅ በመሆንህ እግዚአብሔር ይጠብቅህ።

እንደ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ግን በዉኑ ቤተክህነት አለ ወይ?”

✞“Dr Biniam is trying to tell you the atrocities that happened in Tigray. You bringing Metekel And Oromia, why? We Tegaru’s don’t expect anything from you except to remove your killer Fano’s and your priest killer, church looter, and rapist armies out of Tigray.”

✞“ዝም ብላችሁ አትዘባርቁ ግደሉ ብላቹ መርካቹ ስታበቁ ስለ ትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን አይመለከታችሁም ቢንያም ደግሞ የትግራይን ህዝብ መወከል አይችልም ይህ ሁሉ ሴራ የደረሰብን በእናንተ ምክንያት ነው ይሁዳዎች!”

✞“ለምንድነው ዲ/ን ዶ/ር ቢንያም እውነታውን ሲናገር የምታቋረጡት ወደድንም ጠላንም እውነትቱ ይህ ነው ወረኛው የመናፍቅ መንግስታችን አብይ አህመድ አንድም ሰው አልሞተም ይላል አላማው ኦርቶዶክስን ማጥፋት ነው ሰው በዚህ ደረጃ የአገሩ ሰው ላይ ይጨክናል”

✞ “ዲያቆን ታደሰ ወርቁ የሚሉት ምን አይነት ጭንቅላት ነው ያለው ? እንዴት ብለው ነው ካህናት እየተገደሉ እየተባለ ኣብያተ ክርስትያናት እየወደሙ ኣለያም እየተዘጉ እንዴት ነው ሪፖርት የሚያቀርቡት ???? ኣያፍርም ። ይህን ሰው አሁንም በጥላቻ ስለተደፈነ እውነታውን ዘንግቶታል ። ስለ ትግራይ ላይ የደረሰው ጭፍን ኣጠቃላይ የውድመትና ጥፋት ርብርብ ለማሳነስ ከመተከልና ከኦሮምያ ማወዳደርህ ይገርማል ? ቢያንስ መተከልና ኦሮሞ 46 /ጦር የኤርትራ ወሯል ወይ ? የዓረብ ኢሚሬት ድሮኖች ተሳትፏል ወይ ? ኣክራሪ እስላማዊ የሶማሊያ ወታደር ታድሟል ወይ ? ጽንፈኛ ትግራዋይ ጠል የአማራ ሙሉ ሀይል ዘምቷል ወይ ፋኖ፣ ሚሊሺያ ፣ ልዩ ሀይል ወዘተ ፤ ሌላው ስለ ሀይማኖት ሲወራ ኣስሬ ኣክቲቪስት ማለትህ እምነት ሳይሆን ፖለቲካ እንደ ሸፈነህ ያሳብቅብሃል ። ይብላኝ ለናንተው ፈጣሪ ይቅር ይበላቹህ እንጂ ትግራይ ከእንግዲህ የናንተው ኣካል ኣይደለችም 100% ።”

✞“የውጭ ሚድያ ከዘገበው በኋላ ነው ኣሁን ጉዳቱ የሚነገረን ሁሉም ሰው በጦርነቱ ግዜ ሲያጨበጭብ ነበር ለኢ/ያ ህዝብ በኢቲቪ ዜና የሚነገረው ብቻ ነበር እውነት ብሎ የተቀበለው እግር ሰብሮ ዊልቸር መስጠት የባሰ ያማል በማሕበረ ቁዱሳን ትልቅ እምነት ነበረኝ የምኮራበት ማሕበር ነበር ኣሁን ግን ላይመለስ ልቤ ተሰብሯል በርግጥ የራሴ ጥፋት ነው በእግዚአብሔር ብቻ ተስፋ ማድረግ ነበረብኝ የውጭ ሚድያ ከዘገበው በኋላ መዘገብ ዋጋ የለውም በጣም ነው ያዘንኩት ለማንኛውም እናመሰግናለን”

✞ “እጅግ ያሳዝናል ዘንድሮ አክሱም ተወልዶ ያደገውን እና ኢትዮጽያውያንን ስነልቦናና ምግባር የቀረጸው የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በመሃል አገር ጭምብላም ፖለቲከኞች እና ለዘመናት ሲነግዱበት የነበረውን በእግዚኣብሔር ሀይል ዘንድሮ ተጋልጧል ። ድሮውንም ለዘመናት ጨቋኞች መጠቀምያ አድርገውት የክርስቶስ እና የድንግል ወላዲተኣምላክ ስብከት ሳይሆን በክርስቶስ ስም ቅብ የመተትና የደብተራዎች የውሸት ተረት ተረትኛ ነበረና ። ትግራይን ሰሚ እንዳይኖር ከአለም አቆራርጠህ ከባእድ ወራሪ ተሰባስበህ በ46 ክፍለጦር የሻእብያ ጦር (240 ሺ ወታደር በላይ) 5 ሺ ከሞቃድሾ ሶማልያ ቅጥረኛ ወታደር ፤ ከኣማራ ክልል ሙሉ ሃይል ፤ ከዓረብ ኢሚሬት ሰው አልባ ድሮን እየደበደብክ ህዝብን ለማጥፋት ቅዱሳን ስፍራዎች ለማጥፋት በግብር እምነታቹህ ኣይተናልና ፍርዱን ለፈጣሪ እንሰጠዋለን ።”

✞“አይ ማህበረ ቅዱሳን የት ነበራችሁ ፻/100 ቀን?? ሳታውቁ ቀርታችሁ ነው?? አይደለም! አሁንም አረጉ ለመባል ነው እንጂ ፕሮግራሙን የሰራችሁት ልጁ እንዲያወራ፣ ሀሳቡን እንዲጨርስ እንኳን አልፈቀዳችሁለትም።

አሁን እዚጋር መተከልን ምን አመጣው??? ለመተከል ሌላ ፕሮግራም መስራት ስትችሉ። ከትግራይ የመጣ ሰው ጋብዛችሁ ስለመተከል ማውራት ምን ይሉታል?? የትግራይ ሀዘን ሳያሳዝናችሁ ገና ለገና ፕሮግራም ሰራችሁ ተብላችሁ በምርጦቹ ኦርቶዶክሶች እንዳትወቀሱ ዝብዝብ ያለ ፕሮግራም ሰራችሁ። ጥሩ ነው በሚያምኑት መከዳት። የአንድ ዘር ብቻ ጠበቆች መሆናችሁን መች አውቀን?? የምትሰብኩት/ ስትሰብኩን የኖራችሁት እግዚአብሄር ግን ዘር እየለየ አያዝንም። እናንተ ሀዘኔታ ባታሳዩ እግዚአብሄር ለንፁሀን ያዝናል። እናንተን ግን እንኳን አወቅናችኩ!”

✞“ይገርማል ግን እውነቱን እግዚአብሔር ይፈተዋል ግዜ ቢረዝምም ስጀመር የኦርቶዶግስ ተዋህዶ ኣባቶች የትግራይ ህዝብ ጭፍጨፋ ደስ ብላቸው ኢ/ያ በኣሁኑ ስዓት ከፋታላይ ናት ብለዋል ግን እግዚኣብሄር ሁሉም ቻይ ነው እሱ ባለው በፍቃዱ ይፈርዳል ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ተስፋችን ኣንድ እግዚኣብሄር ነው ለወንድማች ለዲ/ን ደ/ር ቢንያም እናመሰግናለን ግን ለማ/ረ ቅዱስን እባካቹህ ሰው ሁኑ የሰውን ህመም ተረዱ ስለ እውነት ኑሩ የክርስቶስ ሃወርያ ሁኑ ራሳችህን መርምሩ ኣስተውሉ መፅሓፍ ቅዱስ ስላወቃቹህ እና የሃይማኖት ኣባት ስለሆናቹህ ብቻ ኣደለም የሃይማኖት ኣባት ልትባሉ ምትችሉ የሃይማኖት ኣባት መሆቹህ በተግባር ኣሳዩን ግን ለሁላችን ኣስተዋይ ልቦና ይስጠን ልዑል እግዚአብሔርር ኣሜን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏”

_______________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: