ታሪካዊው ምስካየ ኅዙናን (የሐዘንተኞች መጠጊያ) መድኃኔ ዓለም ገዳም | መድኃኔ ዓለም በትግራይ ያሉትን ወገኖቻችንን ሁሉ ያጽናናልን
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 5, 2021
✞✞✞እንኳን ለዓመታዊው የመድኃኔ ዓለም ክብረ በዓል አደረሰን!✞✞✞
👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም
መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ አስቀድሞ ለአዳምና ለሔዋን በሰጣቸው ተስፋ መሠረት ፭ሺ፭፻ /5500 ዘመን ሲፈጸም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ፪/2 ዓመት ከስድስት ወር በግብጽ በረሀ ተሰዶ ስደታቸውን ሻረላቸው በ፴/30 ዓመቱ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ባሕር ተጠምቆ ልጅነታቸውን መለሰ እንዲሁም በዮርዳኖስ ወንዝ “አዳም የዲያብሎስ ባሪያ” የሚል ጽሕፈት ስለነበረ በጥምቀቱ ደምስሶላቸዋል። ሦስት ዓመት ከ፯/7 ወር ወንጌል በእስራኤል ተአምራትን እያደረገ ሙታንን እያስነሳ፣ እውራንን እያበራ፣ ለምጻሞችን እያነጻ፤ ፴፫/33 ዓመት ከ፫/3 ወር በዚህች ዓለም ከተመላለሰ በኋላ መጋቢት ፳፯/27 ቀን በእፀ መስቀል ላይ ተሰቅሎ በሞቱ ሞታችንን ሻረልን።
መድኃኔ ዓለም ማለት የዓለም መድኃኒት ማለት ነው።
ቸሩ መድኃኔ ዓለም በግራኝ አብዮት አህመድ አሊ የኦሮሞ አህዛብ አገዛዝ በተለይ በትግራይ የሚጨፈጨፉትን፣ የሚበደሉትን፣ የሚደፈሩትን፣ የሚሰደዱትንና የሚጎሳቆሉትን ወገኖቻችንን ሁሉ ያጽናናልን!
በ፲፮ ኛው ክፍለ ዘመን በግራኝ አህመድ ወረራ ጊዜ፤ በወቅቱ ነግሠው የነበሩት አፄ ልብነ ድንግልም ሆኑ
እሳቸውን የተኳቸው ነገሥታት፤ በጦርነቱ ምክኒያት በቅድስት ሀገር ለተቋቋሙ አብያተ ክርስትያናት ዕርዳታቸውን ስላቋረጡ፤ ካህናቱ የሚያስፈልጋቸውን ቁሳቁስ፣ ምግብ ባለማግኘታቸው፤ ገዳማቱን ግማሹን በአደራ ለአርመንና ለግሪኮች እየሰጡ፤ ሌሎቹን ደግሞ ዘግተው ወደ አውሮጳ ተሰደዱ፡፡
ከዓመታት በኋላ ተመልሰው ሲመጡ ግን ሁሉንም ለማግኘት ባይችሉም አሁን በእጃችን ያሉትን ይዘው አገልግሎታቸውን ቀጠሉ፡፡ ግራኝ ድል ሆኖ ጦርነቱ ከቆመም በኋላ፣ አንድ ወጥ መንግሥት የነበረው ቀርቶ የዘመነ መሳፍንት አገዛዝ ስለቀጠለና ፣ አሁንም በቂ ዕርዳታ ማግኘት ስላልቻሉ፤ ድርጎ፣ ልብስ፣ የመሳሰሉትን የሚያገኙት ከአርመንና ከግሪክ ገዳማት ነበር፡፡
በ፲፱ ኛ ክፍለ ዘመን የነገሡት ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ቋሚ ገቢ እንዲኖራቸው በማሰብ እዚያው ኢየሩሳሌም ውስጥ ሕንፃ ተሠርቶ የሚከራይበት መሬትና ተጨማሪ ሌላ ባለ ሁለት ፎቅ ሕንፃ በሺ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ዓ.ም. በመግዛት አበርክተዋል፡፡ በዚያው ዓመት
የመድኃኔዓለምን ታቦት ዴር ሱልጣን መድኃኔዓለም በሚል ተሰይሞ መምህር ፈቃደ እግዚእ በተባሉ መነኩሴ ወደ ኢየሩሳለም ልከው በዴር ሡልጣን ገዳም ለ፴፬ ዓመታት ሲቀደስበት ሲወደስበት ኖሯል፡፡
በስደት የነበረው ታቦት መድኃኔዓለም ነሐሴ ፳፫ ቀን ፲፱፴፫/1933 ዓ.ም. እቴጌ መነን ወደ አዲስ አበባ በተመለሱ ቀን፤ አባ ኃይሌ ቡሩክ ታቦቱን ይዘው ተመልሰው በገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት የአሁኑ የስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ጸሎት ቤት ውስጥ እያጠኑና እየጠበቁ ከቆዩ በኋላ፤ ሚያዚያ ፳፯/27 ቀን ፲፱፴፭/1935 ዓ.ም. የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ተብሎ ተሰይሞ
በቀድሞ ቤተ ሳይዳ ቀዳማዊ ኃ/ሥለሴ ሆስፒታል አሁን የካቲት ፲፪ ቀን ተብሎ በሚጠራው ግቢ ውስጥ ተተከለ፡፡
የምስካየ ኅዙናን ትርጓሜ ለተበደሉትና ላዘኑት ማረጋጊያ ማጽናኛ ማለት ነው፡፡
አዎ! የዘመናችን ግራኝ አህመድ በለገጣፎ ያፈናቀላቸውን ወገኖቻንን መጠለያ የሰጣቸው የመድኃኔ ዓለም ቤተክስቲያን ነው፤ ለሙስሊሙ ሳይቀር። ቸሩ መድኃኔ ዓለም ሁሌም ለሁሉም በሩን ይከፍታል።
ምስካየ ኅዙናን (የሐዘንተኞች መጠጊያ) – መጠሪያ ስሙ ብቻ በጣም ይመስጣል፤ እግዚአብሔር የገዳሙን ደጅ መርገጥ ፈቅዶልኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ማየቴ ነበር፤ ይገርማል የአዲስ አበባ ሰው ሆኜ፤ በጣም ከተደሰትኩባቸው ዕለታት መካከል አንዱ ነበር።
የምስካየ ኀዙናን መድኃኔ ዓለም አፄ ምኒልክ ታቦቱን ወደ ቅድስት ሀገር ልከው፤ ከዚያም በእንግሊዝ ሀገር በስደት ለብዙዎች መጽናኛ ሆኖ ቆይቶ ወደ ሀገራችን ተመልሶ እስከመጣበትና እስከ አሁንም ድረስ፤ ታሪካዊና፣ በሥራ ሂደቱ፣ በእንቅስቃሴው፣ ልዩ ልዩ ሥራዎችን በመጀመር ለሌሎች አብያተ ክርስቱያናት አርአያ በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገ ገዳም ነው፡፡
ይህ ድንቅ ገዳም ወደፊትም የበለጠ ሥራ የሚሠራና፤ ለእናት ቤተ ክርስቲያናችን የሚያኮራ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም፡፡
መድኃኔ ዓለም ይህንን እና ሌሎቹን ገዳሞቻችንን እንዲጠብቅልን፤ ሀገራችንንም በበረከቱ እና ቸርነቱ እንዲጎበኝልን ዘወትር እንጸልያለን፡፡
መድኃኔ ዓለም ተብሎ መድኃኒታችን የሆነን አምላክ ይክበር ይመስገን። አሜን!
_____________________________________
Leave a Reply