Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2021
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for April 4th, 2021

The Weeknd – aka R&B Artist Abel Tesfaye Donates $1 Million to Tigray, Ethiopia

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 4, 2021

✞✞✞የጸሎት ኃይል ይህ ነው✞✞✞

ዛሬ ከቤተ ክርስቲያን መልስ የተዋሕዶ ዘማሪውን የአቤል ተስፋየን የበገና መዝሙሮች እየሰማሁ፤ “እንደው እኔ በገንዘብ እንኳን ይህን ያህል ኃብታም አይደለሁም፤ ግን እስኪ ለመጭው የፋሲካ በዓል ወደ ሱዳን ወርጄ በካህናት የተባረከና ለወራት የሚበቃ የአንባሻ ገብስ ላቅርብ” በማለት ሳሰላስል፤ ያው ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ሌላው ታዋቂ ሙዚቀኛ ወንድማችን አቤል ተስፋዬ አንድ ሚሊየን ዶላር በግራኝ ዲያብሎሳዊ ሤራ በመቸገርና በመሰቃየት ላይ ላሉት የትግራይ አባቶቼ፣ እናቶቼ፣ ወንድሞቼ እኅቶቼ ለመስጠት ወሰነ። ያውም የፈረንጆቹ የፋሲካ በዓል ሚከበርበት ዕለት። ዋው! ድንቅ ነው! ተዓምር ነው።

✞✞✞ መድኃኔ ዓለም አለና/ አለን!✞✞✞

The Weeknd is donating $1 million to hunger relief in Ethiopia amid the ongoing conflict between the government in Addis Ababa and the Tigray region.

The conflict has resulted in the deaths of thousands and the displacement of more than two million people, according to N P R. Last month, the New York Times obtained an internal U.S. government report that said Ethiopian officials are “leading a systematic campaign of ethnic cleansing” in the Tigray region.

The singer announced his donation via Instagram on Sunday morning and encouraged others to give, too.

My heart breaks for my people of Ethiopia as innocent civilians ranging from small children to the elderly are being senselessly murdered and entire villages are being displaced out of fear and destruction,” The Weeknd wrote. “I will be donating $1 million to provide 2 million meals through the United Nations World Food Programme and encourage those who can to please give as well.

His post also included striking images of children from the region.

Both of The Weeknd’s parents immigrated to Canada from Ethiopia, and The Weeknd grew up speaking Amharic, the official language of Ethiopia.

This is not the first time The Weeknd has aided a humanitarian cause. In June 2020, he donated $1 million to COVID-19 relief, giving $500,000 each to MusiCares and the front-line hospital workers of Scarborough Health Network in his hometown. That same month, he gave another $500,000 to the racial justice causes Black Lives Matter, National Bailout and Colin Kaepernick’s Know Your Rights camp. In August 2020, The Weeknd also donated $300,000 to Global Aid for Lebanon to help those affected by the Beirut explosion.

_____________________________________

Posted in Ethiopia, Infos, Life, Music | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Debre Zeit Jerusalem | ደብረ ዘይት በ ኢየሩሳሌም | ክርስቶስ በማታስቡበት ሰዓት ስለሚመጣ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 4, 2021

መዝሙር ዘደብረ ዘይት፦ እንዘ ይነብር እግዚእነ

ምስባክ፦ እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ፤ ወአምላክነሂ

ኢያረምም፤ እሳት ይነድድ ቅድሜሁ [መዝ. ፵፱፥፪፡፫]

“ጌታችሁ በየትኛው ሰዓት በየትኛው ቀን እንደሚመጣ አታውቁምና ተግታችሁ ጠብቁ”

[ማቴ ፳፬፥፵፪]

‹‹የሰው ልጅ (ክርስቶስ) በማታስቡበት ሰዓት ስለሚመጣ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ›› [ማቴ ፳፬፥፵፬]

ይህ ዓለም ኃላፊ፣ ረጋፊ፣ ጠፊ መሆኑን ቤተ ክርስቲያን ሁልጊዜ ታስተምረናለች። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንም ይህ ዓለም ዘለዓለማዊ አለመሆኑን፤ አንድ ጊዜ የሚያልፍና የሚጠፋ መሆኑን ቢያንስ በዓመት ሁለት ጌዜ ለምእመናን ልጆችዋ

፩ኛ/ በደብረ ዘይት (በግማሽ ጾም ላይ)

፪ኛ/ በዓመቱ የመጨረሻው እሑድ ላይ አጽንኦት ታሳስባለች

ዓለም ስንል መላውን የዓለምን ሕዝብ ጭምር ነው። ታዲያ ሁላችንም ለመጨረሻው ቀን ሁልጊዜ ተዘጋጅተን እንድንጠብቅ ቅደስት ቤተ ክርስቲያናችን ‹‹ጌታችሁ በየትኛው ሰዓት በይትኛው ቀን እንደሚመጣ አታውቁምና ተግታችሁ ጠብቁ፤›› [ማቴ ፳፬፥፵፪] እያለች ዘወትር ታሳስበናለች።

ደብረ ዘይት ይህ የዛሬው ሰንበት ደብረ ዘይት ይባላል። ደብረ ዘይት ከኢየሩሳሌም ከተማ ባሻገር በስተምሥራቅ በኩል የሚገኝ ኮረብታማ ቦታ ነው። በመካከሉ የቄድሮስ ወንዝና ሸለቆ ይገኛሉ። ቦታው የወይራ ዘይት ዛፍ በብዛት የሚገኝበት ስለሆነ ደብረ ዘይት ተባለ። የዘይት ዛፍ የሞላበት ተራራ ማለት ነው። ጌታ የጸለየበትና እመቤታችን የተቀበረችበት ጌቴሴማኒ የተባለውም የአትክልት ቦታ በዚሁ ኮረብታ ስር ነው የሚገኘው። ደብረ ዘይት የሚያስታውሰን ጌታ ስለ ዳግም ምጽአቱ በቦታው ያስተማረው ትምህርት ነው።

አንድ ቀን የጌታ ደቀ መዛሙርትና ፈረሳውያን ስለ ጌታ መምጣትና የዓለም መጨረሻ መቼ እንደሚሆን በዚሁ ኮረብታማ ስፍራ (ደብረ ዘይት) ጌታችንን ጠየቁት። የጌታም መልስ ‹‹ጌታችሁ በየትኛው ቀን እንደሚመጣ አታውቁምና ተግተቃችሁ ጠብቁ›› እንዲሁም ‹‹የሰው ልጅ በማታስቡት ሰዓት ስለሚመጣ ተዘጋጅታችህ ኑሩ፤›› [ማቴ ፳፬፥፳፬፡፵፬] የሚል ነበር።

ዳግም ምጽአት፦ ምጽአት ምንድን ነው? ምጽአት ሲባል እጅግ ያስደነግጣል፣ ያስፈራልም። ምጽአት ማለት ጌታችን ወደዚህ ዓለም የሚመጣበት ጊዜ ማለት ነው። ይኸውም አንደኛ የጌታ ምጽአት፣ ሁለተኛ የጌታ ምጽአት በመባል ይታወቃል። ‹‹ወአውሥአ ወይቤሎሙ ዑቁ ኢያስሕቱክሙ» ኤፌ፭፥፮ ያንጊዜ ክርስቶስ ከወዲህ አለ ከወዲያ የለም ቢላችሁ አትመኑ እነሆ አስቀድሜ ነገርኳችሁ ከቤተ አለ ከበርሐ አለ ቢላችሁ አትውጡ እነሆ በምኩራብ ይስተምራል ቢላችሁ በጀ አትበሉ ›› [ማቴ. ፳፭፥፳፫]

የመጀመሪያው የጌታ ምጽአት፦ ነቢያትና የጥንት አባቶች በተነበዩትና ተስፋ በአደረጉት መሠረት ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ ከቅዱስት ድንግል ማርያም ተወልዶ እኛ ሕዝቦቹን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ አድኖናል። ጌታ ቀድሞ የመጣው ለምሕረት፣ ለቸርነት፣ ለይቅርታና ሰውን ለማዳን፣ ሰውን ይቅር ለማለት፣ ለማስተማር ትሑት ሆኖ፣ በፈቃዱ ክብሩን ዝቅ አድርጎ፣ የሰውን ሥጋ ለብሶ ነው የመጣው። ይህንንም ፈጽሞ እኛ በረከተ ሥጋንና በረከተ ነፍስን የምንገኝበትን ቤተ ክርስቲያንን መሥርቶልናል። ይህ የጌታችን የመጀመሪያው ምጽአት ይባላል።

ሁለተኛው ምጽአት፦ ወደፊት ክርስቶስ የሚመጣበት ሁለተኛው ምጽአት ይባላል። ክርስቶስ ወደፊት የሚመጣው ከፍ ባለ ግርማና በታላቅ ክብር፣ በአስፈሪነት፣ በእምላክነቱ ክብርና በግርማ መለኮቱ በመላእክት ታጅቦ ነው። ዛሬ በቅዳሴ ጌዜ የተነበበው የማቴዎስ ወንጌል ‹‹የሰው ልጅም በኃይልና በታላቅ ክብር በደመና ላይ ሆኖ ይመጣል፤›› [ማቴ ፳፬፥፴] ሲል አስረድቶናል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጨረሻ የሚመጣው ለምሕረትና ለይቅርታ ሳይሆን ለእያንዳንዱ ሰው በዚህ ዓለም እንደ ሠራው ሥራ መሠረት ዋጋውን ለመስጠት፣ ዋጋውን ለመክፈል እንደ ሠራው ሥራ መሠረት ዋጋውን ለመስጠት፣ ዋጋውን ለመክፈል እንደ ታላቅ ዕለተ ዕለት (የክብር ዕለት) ወይንም ዕለተ ፍዳ ወደይን (የፍዳና የመከራ ዕለት) ትባላለች። ዕለተ ክብር (የክብር ዕለት) የምትባልበትም ምክንያት ጌታ ጌትነቱን፣ ከብሩን የሚገልጥባት፣ ለወዳጆቹ ለጻድቃን፣ ለሰማዕታትና በአጠቃላይ ሕጉን ትእዛዙን አክብረውና ፈጽመው ለኖሩት ለተቀደሱት ምእምናን ክርስቲያኖች ዋጋቸውንና የሚገባቸውን ክብር የሚሰጥባተ ዕልት ስለሆነች ነው። እነዚህ ቅዱሳን በዚህ ጊዜ ታልፋልች የምትባለውን መንግሥተ ሰማያት የሚወርሱባት ቀን ስልሆነች ነው።

ስለ ሰው ልጅ ትንሣኤ፦ ሰው ከሞተ በኋላ አንድ እንስሳትና እንደ አራዊት ፈርሶ በስብሶ አፈር ትብያ ሆኖ የሚቀር ፍጥረት አይደለም ነገር ግን ሰዎች ቢሞቱም በመጨረሻው ጊዜ በዕለተ ምጽአት ሕይውትን አግኝተው ለዘለዓልም ለመኖር በሥጋ ይነሣሉ። የሰው ልጅ ትንሣኤ ሁለት ዓይነት ነው፦

(ሀ). የከብር ትንሣኤ

(ለ). የሐሳር (የመከራ) ትንሣኤ

ይባላል።

የክብር ትንሣኤ የሚባለው ሰዎች በምድር ሕይወታቸው ሳሉ በሚሠሩአቸው መልካም ሥራ ሁሉ እንዲሁም ሕጉን ትእዛዙን አክብረውና መፈጽመው ስለኖሩ ከልዑል እግዚአብሔር የክብር ዋጋ ጽድቅን መንግሥተ ሰማያትን የሚያገኙበት ስለሆነ ነው። የመከራ ትንሣኤ የሚባለው ደግሞ ሰዎች በምድር ሕይወታቸው ሳሉ በሚሠሩተ ክፉ ሥራ ሁሉ በጌታ ዘንድ ፍዳና መከራ፤ ሐሳርና ኵነኔ የሚያገኙበትና ወደ ገሃነመ እሳት የሚወርዱበት ስለሆነ ነው።

የሰው ልጀ በምድር ላይ ሲኖር በሚሠራው ሥራ ሁሉ ከሞተ በኋላ ክልዑል እግዚበሔር ዘንድ ተገቢውን ፍርድ ያገኛል። የሚሰጠውም ፍርድ በሁለት ይከፈላል፤

፩ኛ/ ጊዜያዊ ፍርድ

፪ኛ/ የመጨረሻ ፍርድ ይባላሉ

ጊዜያዊ ፍርድ፦ ሰው ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየ በሠራው ሥራ መሠረት ጊዜያዊ ፍርድ አግኝቶ ወደ ጊዜያዊ ማረፊያወደ ገነት ወይም ወይም ሲኦል ይገባል።

የመጨረሻው ፍርድ፦ የመጨረሻው ፍርድ የሚባለው ደገሞ ሰዎች በምድር ሕይወታቸው መልክም ሥራ የሠሩ፤ የእግዚብሔርን ሕግን ትእዛዝ ጠብቀው የኖሩ በመጨረሻው ጊዜ በሥጋ ተነሥተው ዓለም ሲፈጠር ጀምቶ የተዘጋጀውን መንግሥተ ሰማያትን እንዲወርሱ የሚሰጣቸው ፍርድ ነው። [ማቴ. ፳፭፥፵፩፡፵፮] ያለውን አንብብ።

ገሀነመ እሳት፦ ገሃነመ እሳት የሚባለው ደግሞ ሰዎች በዚህ ዓለም ሕይወታቸው ክፉ ሥራ ሲሠሩ የቆዩ፦ ሕጉንና ትእዛዙን ሳይፈጽሙ የኖሩ ሁሉ በመጨረሻው ፍርድ ጊዜ እነሱም በሥጋ ሥቃይና መከራ ቦታ ገሀነመ እሳት ይገባሉ። ማቴ 25፥ 41 -46 [ማቴ ፳፭፥፵፩፡፵፮] ያለውን አንብብ።

ምስጋና ወቀሳ፦ በመጨረሻው ፍርድ ጊዜ ጌታ ለጻድቃን የሚሰጠው ምስጋናና ኃጥአንን የሚወቅስበት የተግሣጽ ቃን የማኀበራዊ አገለግሎትን የሚመለከት ነው።

✞ ✞ ✞ ደብረ ዘይት = ደብረ ዘይት ✞ ✞ ✞

______________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: