የዋልድባ ገዳም አባቶች ሰቆቃ | በትግራይ እየሆነ ባለው የአባቶች እንባ ሲደርቅ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ደም ያለቅሳሉ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 29, 2021
❖ [መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፮፥፲፮፡፲፱]❖
“እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤ በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥ ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥ በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ“
ዋልድባ ይናገር ዜጋመልም ሳይቀር
እንባቸው መፍሰሱ ለምን እንደነበር።
ነበር ወይ ፈልገው ሹመት ሽልማት
ወይስ ሃብት ንብረት የተሟላ ቤት
ወይስ አምሯቸው ነው ፈልገው መሞት
እናንተ ገዳማት ምስጢሩን አውሩት።
ጎበዝ ሰው አማረኝ በእምነቱ የፀና
ምግባር ሃይሞኖቱን በእጅጉ ያቀና።
እንጦንስ የወለደው በምግባር በእምነት
ተምሮ ያደገ ከተክለሃይማኖት።
የጊዮርጊስ ወዳጂ የት ነው የሚገኘው
በመሃል ከተማ በአራዳ ውስጥ ነው
ወይስ በዝቋላ በደብረ ሊባኖስ በደብረ ዳሞ ነው።
ወገን ሰው ናፈቀኝ አይኔን ሰው አማረው
የሃይማኖት ጀግና የት ነው የማገኘው?
ልግባ ወይ ዋልድባ ጫካ ካለበት
ማህበረ ስላሴ ከቅዱሳን ቤት
አክሱም ጊሸን ማርያም ከቃልኪዳን ቦታ
ይገኛል ወይ ጀግና ጠላት የሚረታ።
________________________________
Leave a Reply