Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for March 22nd, 2021

እኅት አዱ | ወዮልህ፤ አብዮት አህመድ! እስከ ፯/7 ዘርህ እናሳድድሃለን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 22, 2021

💭 ብዙ ነገርሽ ትክክል ነው፤ እህታችን! ግን “ውሻ” አይገባውም፤ ውሻ ተሰደበ እኮ! ውሻማ ታማኝ ነው፤ ተበየነበት እኮ!

😳😳😳

_______________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

NPR | The Case of PM Abiy Ahmed | What is Happening in Tigray is Worse Than War

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 22, 2021

🔥 A Nobel Peace Laureate and Horror in Ethiopia

🔥 የኖቤል የሰላም ተሸላሚ እና አስፈሪ ሰቆቃ በኢትዮጵያ

👉 የጠ / ሚ አብይ አህመድ ጉዳይ | በትግራይ እየሆነ ያለው ከጦርነት የከፋ ነው

🔥 ዛሬ ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በጦርነት በምትገኘዋ ትግራይ ምክኒያት እንደገና በዜና ውስጥ አለች። እዚያ እየሆነ ያለው ከጦርነት የከፋ ነው ፥ ትግራይ የጦር ወንጀልና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ቲያትር ናት።

🔥 አስገድዶ መድፈር ከረጅም ጊዜ በፊት የጦር መሣሪያ ሆኖ ቆይቷል ፥ በሱዳን ፣ በባልካን ፣ በበርማ እና በሌሎች በርካታ ቦታዎች። በትግራይ በጅምላ መድፈር እጅግ ዘግናኝ በሆነ ደረጃ ላይ ይገኛል። እ... ጃንዋሪ 21 አንድ የተባበሩት መንግስታት ባለስልጣን ፕራሚላ ፓተን መግለጫ ሰጡ። የተባበሩት መንግስታት “በግጭቶች ውስጥ ወሲባዊ ጥቃት” በሚለው ርዕስ ጉዳይ ላይ “ልዩ ተወካይ” ነች። የእርሷን መግለጫ የመጀመሪያዎቹን ሁለት ዓረፍተ ነገሮችን ብቻ እጠቅሳለሁ፦

በትግራይ ዋና ከተማ በመቐለ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ ከባድ የወሲብ ጥቃቶች መከሰታቸው በጣም አሳስቦኛል። በቅርቡም “የኃይል እርምጃ ይወሰድባችኋል” የተባሉ ግለሰቦችም በማስፈራራት የገዛ ቤተሰቦቻቸውን ለመድፈር ተገደዋል የሚሉ የሚረብሹ ዘገባዎች አሉ።”

🔥 ለትግራይ ሲኦል ተጠያቂው ማነው? ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ? የጥፋተኝነት ምደባ ብዙ የመተንተን ገጾችን ይወስዳል። በትግራይ እና በውጭው ዓለም መካከል ያለው የግንኙነት መቆራረጥ እና የሰብዓዊ ዕርዳታ መዘግየትን ለክልሉ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ ፣ በብዙዎች ዘንድ ዋናው ተጠያቂ አብይ አህመድ እንደሆነ ግልጽ ነው። ብዙዎች የአብይ የኖቤል የሰላም ሽልማት እንዲሰረዝ/ እንዲሻር ጥሪ እያደረጉ ነው።

🔥 የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ ዛሬ ፊቱ ላይ እንቁላል አለበት። ከበርማዋ ጠቅላይ ሚንስትር ኦንግ ሳን ሱ ኪይ ጎን ለጎን የኮሚቴው የ 2019 ተሸላሚ ይህንን ነፍሰ ገዳይ እና ጭራቃዊ/ አሰቃቂ ጭፍጨፋ በትግራይ እየመራ ነው። ግን የ 2019 ሽልማት በኖቤል ውሎች ትርጉም አለው።

🔥 የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ ዛሬ ፊቱ ላይ እንቁላል አለበት። ከበርማዋ ጠቅላይ ሚንስትር ኦንግ ሳን ሱ ኪይ ጎን ለጎን የኮሚቴው የ 2019 ተሸላሚ ይህንን ነፍሰ ገዳይ እና ጭራቃዊ/ አሰቃቂ ጭፍጨፋ በትግራይ እየመራ ነው።

🔥 በትግራይ ያለው ገሃነም ሳይቋረጥ ሊቀጥል ይችላል። ሊዛመትና ኢትዮጵያንም የከሸፈች/ ያልተሳካች ሀገር ሊያደርጋት ይችላል።

🔥 ኢትዮጵያ የተወሳሰበች ሀገር ናት ፣ ግን እኔ ለማንኛውም ለኢትዮጵያተመልካቾች ወይም በአጠቃላይ ለተመልካቾች ምክር አለኝ። ምክሩ የእኔ አይደለም ፣ ግን በባግዳድ ኢራቅ የተወለደው እና ያደገው ታላቁ የእንግሊዛዊ የታሪክ ምሁር ኤሊ ኬዱሪ፤ “አይናችሁን በሬሳዎች ላይ አድርጉ!” ሲል ለዴቪድ ፕራይስጆንስ የሰጠው ምክር ነው።

🔥 Today, Ethiopia is again in the news, for war in Tigray, a region in the country’s north. What is happening there is worse than war, if such a thing is possible: Tigray is a Theater For War Crimes & Crimes Against Humanity.

🔥 Rape has long been a weapon of war — in Sudan, the Balkans, Burma, and any number of other places. Rape in Tigray is on a mass, horrific scale. On January 21, a U.N. official, Pramila Patten, issued a statement. She is the U.N. “special representative” on the subject of “sexual violence in conflict.” I will quote just the first two sentences of her statement:

🔥 „I am greatly concerned by serious allegations of sexual violence in the Tigray region of Ethiopia, including a high number of alleged rapes in the capital, Mekelle. There are also disturbing reports of individuals allegedly forced to rape members of their own family, under threats of imminent violence.”

🔥 Who is responsible for the hell in Tigray? The prime minister, the Nobel peace laureate? The assignment of blame would take many pages of analysis. Suffice it to say, Abiy Ahmed is to blame for a lot, including the cut-off of communication between Tigray and the outside world, and the delay of humanitarian aid — desperately needed — to the region. Many are calling for the revocation of Abiy’s Nobel Peace Prize.

🔥 Today, the Norwegian Nobel Committee has egg on its face. Aung San Suu Kyi aside, the committee’s 2019 laureate is presiding over this murderous, monstrous mayhem in Tigray. But the 2019 award made sense, on Nobel terms. Classically, a committee asks itself, “Who has done the most or best work for fraternity between nations during the preceding year?”

🔥 The hell in Tigray may go on and on. It may spread, making Ethiopia a failed state.

🔥 Ethiopia is complicated, but I have advice for any Ethiopia-watchers, or watchers in general. It is not my advice, but the advice that Elie Kedourie, the great British historian, born and raised in Baghdad, gave to David Pryce-Jones: “Keep your eye on the corpses.”

______________________________________

Posted in Ethiopia, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አቡነ ማትያስ ያኔ ለኦሮሚያ ሲዖል ሰማዕታት እንባቸውን አነቡ ፥ ምነው ዛሬ ስለ አክሱም ጽዮን ዝም አሉ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 22, 2021

ልጆቼ፥ እንባዬን እያፈሰስኩ ስለ እናንተ ስቃይ አምላካችንን በጸሎት እየጠየቅኩ ነውአቡነ ማቲያስ ከዓመት ተኩል በፊት

በኦሮሚያ ሲዖል ከዓመት ተኩል በፊት በተዋሕዶ ልጆች ላይ ከተደረገው አሰቃቂ ጭፍጨፋ በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚከተለውን መልዕክት ከሃዘንና እንባ ጋር አስተላልፈው ነበር።

ልጆቼ እኔ የሃይማኖት አባት ነኝ። እኔ የእናንተ ጠባቂ ነኝ።ይሁንና ከመታረድ ልታደጋችሁ አልቻልኩም።ከሞት ላድናችሁ አልቻልኩም። እኔ የጦር መሪ አይደለሁም።ገዳዮቻችሁን ለፍርድ ለማቅረብ አቅሙ ዬለኝም። በእጄ ሽጉጥ ሳይሆን መስቀል ነው የምይዘው። ልጆቼ እንባዬን እያፈሰስኩ ስለ እናንተ ስቃይ አምላካችንን በጽሎቴ እየጠየኩ ነው። መንግስትንም ዘውትር እየተማጸንኩኝ ነው። ዛሬ ሆድ ብሶኛል።አልቅስ አልቅስ ልክ እንደ ህፃን ይለኛል። ልቤ በሐዘን ተኮማትሯል። እንቅልፍ በአይኔ ጠፍቶ እንባ ብቻ ሆኗል።ከዛሬ ነገ ይሻላል እያልን መንግስትንም እንዲያስቆም ብንጠይቅ ምንም ያየነው ለውጥ የለም። ይልቅስ ልጆቼን አስጨረስኩ።ሰላም ሰላም እያልኩ እናንተን ሳስተምር ሰላምን ማያውቁ ሰላም ነሷችሁ።ልጆቼ አትቀየሙኝ።ዝም ያልኳችሁ እንዳይመስላችሁ።ሁሌም ስለ እናንተ እንዳለቀስኩ ነው።ጌታ ሆይ ፍረድ ወይም ውረድ።በቁሜ የልጆቼን ሰቆቃ ከምታሳዬኝ ሞቴን አቅርብልኝ።ልጆቼ ላይ የሚፈጸመውን ልከላከልላቸው አልቻልኩም። አንተው ተመልክተህ ፍርድ ስጥ!”

ታዲያ ይህን መልዕክት ከሦስት ሣምንታት በፊት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የ፰ተኛ ዓመት በዓለ ሲመት አከባበር ላይ ካስተላለፉት መልዕክት ጋርና በምን ዓይነት መልክ እንዳስተላለፉት እናነጻጽረው። “ለቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ” ሆነው ሳለ የአክሱም ጽዮንን ጭፍጨፋ ሊያነሱ እንኳን ያልቻሉበት/ያልፈለጉበት ሁኔታ በጣም አሳዝኖኛል። ተሳስቼ ከሆነ ይቅርታ እጠይቃለሁ፤ ግን የግራኝ አብዮት አህመድ አማካሪ ጋንኤል ውርደት ጽፎ የሰጣቸውን ጽሁፍ ያነበቡ ሆኖ ነው የተሰማኝ፤ “ጸሎትና ምሕላ ከማድረግና ገንዘብ ከመስጠት በቀር በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው የእርስበርስ ግጭት ምንም ማድረግ አንችልም” ሲሉ፤ ልክ ወንጀለኛው ግራኝ አህመድ አሊ“ከመደመር መጽሐፌ ሽያጭ የወር ደሞዜን አክየበት ለትግራይ ሕዝብ እሰጣለሁ” ያለውን እንዳስታውስ ነው ያረገኝ። ያውም እርሱ በጠላትነትም ቢሆን የሚጨፈጭፋትን የትግራይን ስም ጠርቷል፤ አቡነ ማትያስ ግን ላለፉት አራት ወራት፤ በሁሉም አጋጣሚዎች የትግራይን ስም ሊያነሱ እንኳን አልፈለጉም፤ ምክኒያታቸው ምን ይሆን?

ምናልባት ልክ እንደተቀረው የትግራይ ሕዝብ ለራሱ የአክሱም ጽዮን ሕዝብ በይበልጥ ከመቆርቆር ይልቅ በይሉኝታ ለተቀረው በጠላትነት ለቆመበት ሕዝብ በይበልጥ ተቆርቁረው ይሆን? ህወሃቶች ለምሳሌ ባለፉት ፳፯/27 ዓመታት እና ከዚያም በላይ ለትግራይ ሕዝብ ከዋሉት ውለታ ይቅር፤ በኅልማቸው እንኳን ያላለሟትን ግማሽ ኢትዮጵያን እስከማስረከብ ድረስ ለኦሮሞዎች የዋሉት ውለታ እጅግ በጣም ትልቅ ነው። ዛሬም እንኳን የደቡብ ሕዝቦችን፣ ሶማሌዎችን፣ ቤን አሚሮችን፣ ራሻይዳዎችን፣ አማራዎችንና አረቦችን አስተባብረው በመምራት በትግራይ ሕዝብ ላይ፣ በአክሱም ጽዮን ላይ፣ በምዕመናኑ እና ካህናቱ ላይ በጣም ከፍተኛ የሆነ ግፍ እየሠሩ ያሉት ኦሮሞዎች ሆነው እያሉ፤ ህወሃቶች ክደዋቸው ከአዲስ አበባ ካባረሯቸው ኦሮሞዎች ጎን ተሰልፈው ይታያሉ። ግራኝ አብዮት አህመድ እንኳን “ለሕዝባችሁ” ብሎ ሰሞኑን ሲሳለቅ የነበረው “እኔ ለኦሮሞ ሕዝብ ስልና እንዳይጎዳ ስላሰብኩለት ነው ጦረንቱን ወደ ሰሜን ያዞርኩት፤ ለሕዝቤ ስል እስከ ሰማዕትነት ለመድረስ ዝግጁ ነኝ።” ለማለት ነው። ይህ የዲያብሎስ ጭፍራ ክልጅነቱ ጀምሮ ወደ ትግራይ በመግባት ሲሰልልና ሲያጠና ቆይቷል። ይህ እጅግ በጣም የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ጉዳይ ነው፤ ዓይናቸው እያየ አልማር ባዮች፣ ተምልሶ ተመላልሶ ወደ ጭቃ! ምናልባት የማናውቀው የእነ ጌታቸው ረዳ “የራያ” ምስጢር አለ?!

ምንም እንኳን አፄ ዮሐንስም ብሔር ሳይለዩ ዛሬ ሱዳኖች በሚያሸቷት በመተማ ለአማራዎች አንገታቸውን ቢሰጡም፤ ዛሬ ግን ቢኖሩ ኖሮ ለትግራይ ሕዝብ ሲሉ አስመራን፣ ጂቡቲን፣ ካርቱምን፣ ሞቃዲሾን፣ ጁባንና ኤደንን ከሃያ ዓመታት በፊት ተቆጣጠረው ታላቂቷንና ኃያሏን ኢትዮጵያ መመሥረት በቻሉ ነበር። አፄ ዮሐንስ ናፈቁኝ፤ ለትግራይ ሕዝብ ዳግማዊ አፄ ዮሐንስን ቶሎ ያስነሳለት። አሜን!

እንደ እኔ ከሆነ አቡነ ማትያስ የፓትርያርክነታቸውን ዘውድ እንደ ሮማው ጳጳስ ቤነዲክት፲፮ኛ/Benedict XVI (በእሳቸውም ዙሪያ ጫና የሚያደርጉባቸው የካቶሊክ ጳጳሳት ነበሩ) አስረክበው ገዳም ይገቡ ዘንድ እመኝላቸዋለሁ። አረመኔው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ባፋጣኝ እስካልተደፋ ድረስ አቡነ ማትያስን አስወግዶ ወይ ኤሬቻ በላይን ወይ አቡነ ናትናኤልን ፓትርያርክ አድርጎ ለመሾም አመቺ የሆነውን ወቅት እየጠበቀ ነው። በዲያብሎስ እንጂ በእግዚአብሔር ላልተቀባው ለአረመኔው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ፤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለሌላው ነገር ሁሉ አስቀድመው፤ “አንተ የዲያብሎስ ጭፍራ፤ ጦርነቱንና ጭፍጨፋውን ባፋጣኝ አቁም፣ ስልጣኑንም አስረክበህ ለምድራዊ ፍርድ ቅረብ፤ በሰማይ ቤት ተፈርዶብሃል!” ሊሉት ይገባል።

________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: