Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for March 21st, 2021

ኤርምያስ ፱ | ተወግተው ስለሞቱ ፣ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ፣ ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ፣ራሴን ውሃ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 21, 2021

ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ አቀልጣቸዋለሁ እፈትናቸውማለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት ከዚህ ሌላ የማደርገው ምንድር ነው?

✞ ✞ ✞[ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፱]✞ ✞ ✞

፩ ተወግተው ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ!

፪ ሁሉም አመንዝሮች፥ የአታላዮች ጉባኤ ናቸውና ሕዝቤን እተዋቸው ዘንድ ከእነርሱም እለይ ዘንድ በምድረ በዳ የመንገደኞች ማደሪያን ማን በሰጠኝ?

፫ ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና እኔንም አላወቁምና፥ ይላል እግዚአብሔር።

፬ ወንድምም ሁሉ ያሰናክላልና፥ ባልንጀራም ሁሉ ያማልና እናንተ ሁሉ ከባልንጀሮቻችሁ ተጠንቀቁ፥ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ።

፭ ሰውም ሁሉ ባልንጀራውን ያታልላል በእውነትም አይናገርም፤ ሐሰትን መናገርንም ምላሳቸው ተምሮአል፥ ክፉንም ለማድረግ ይደክማሉ።

፮ ማደሪያህ በሽንገላ መካከል ነው፥ ከሽንገላም የተነሣ እኔን ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፥ ይላል እግዚአብሔር።

፯ ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ አቀልጣቸዋለሁ እፈትናቸውማለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት ከዚህ ሌላ የማደርገው ምንድር ነው?

፰ ምላሳቸው የተሳለ ፍላጻ ነው፤ ሽንገላን ይናገራሉ ሰው ከባልንጀራው ጋር በሰላም ይናገራል፥ በልቡ ግን ያደባበታል።

፱ በውኑ ስለዚህ ነገር አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?

፲ ለተራሮች ልቅሶን ለምድረ በዳ ማሰማርያዎችም ዋይታን አነሣለሁ፥ ሰው እንዳያልፍባቸው በእሳት ተቃጥለዋልና። ሰዎችም የከብቱን ድምፅ አይሰሙም፤ ከሰማይ ወፎች ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል።

፲፩ ኢየሩሳሌምንም የፍርስራሽ ክምር የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ፥ የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይቀመጥባት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።

፲፪ ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ያወራስ ዘንድ የእግዚአብሔር አፍ ለማን ተናገረ? ሰው እንዳያልፍባት ምድርስ ስለምን ጠፋች፥ እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተቃጠለች?

፲፫ እግዚአብሔርም እንዲህ አለ። የሰጠኋቸውን ሕጌን ትተዋልና፥ ቃሌንም አልሰሙምና፥

፲፬ ነገር ግን የልባቸውን ምኞትና አባቶቻቸው ያስተማሩአቸውን በኣሊምን ተከትለዋልና

፲፭ ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ ይህን ሕዝብ እሬትን አበላዋለሁ የሐሞትንም ውኃ አጠጣዋለሁ።

፲፮ እነርሱና አባቶቻቸውም ባላወቁአቸው አሕዛብ መካከል እበትናቸዋለሁ፥ እስካጠፋቸውም ድረስ በስተ ኋላቸው ሰይፍን እሰድድባቸዋለሁ።

፲፯ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እንዲመጡ አልቃሾች ሴቶችን ጥሩ፤ እንዲመጡም ወደ ብልሃተኞች ሴቶች ላኩ፤

፲፰ ዓይኖቻችንም እንባ እንዲያፈስሱ የዓይናችንም ሽፋሽፍቶች ውኃን እንዲያፈልቁ ፈጥነው ለእኛ ልቅሶውን ይያዙ።

፲፱ በጽዮን። እንዴት ተበዘበዝን! ምድርንም ትተናልና፥ ቤቶቻችንንም አፍርሰዋልና እንዴት አፈርን! የሚል የልቅሶ ድምፅ ተሰምቶአል።

፳ እናንተ ሴቶች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ ጆሮአችሁም የአፉን ቃል ትቀበል፥ ለሴቶች ልጆቻችሁም ልቅሶውን፥ እያንዳንዳችሁም ለባልንጀሮቻችሁ ዋይታውን አስተምሩ።

፳፩ ሕፃናቱን ከመንገድ ጕልማሶቹንም ከአደባባይ ያጠፉ ዘንድ ሞት ወደ መስኮታችን ደርሶአል ወደ አዳራሻችንም ውስጥ ገብቶአል።

፳፪ የሰውም ሬሳ እንደ ጕድፍ በእርሻ ላይ፥ ማንምም እንደማይሰበስበው ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል።

፳፫ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤

፳፬ ነገር ግን የሚመካው። ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር።

፳፭-፳፮ አሕዛብ ሁሉ ያልተገረዙ ናቸውና፥ የእስራኤልም ቤት ሁሉ ልባቸው ያልተገረዘ ነውና የተገረዙትን ሁሉ፥ ግብጽንና ይሁዳን ኤዶምያስንም የአሞንንም ልጆች ሞዓብንም በምድረ በዳም የተቀመጡትን ጠጕራቸውን በዙሪያ የተላጩትን ሁሉ፥ ባለመገረዛቸው እነርሱን የምቀጣበት ዘመን እነሆ ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።

________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሰይፍም በከንፈሮቻቸው አለ፤ ማን ይሰማል? ይላሉ። አንተ ግን አቤቱ፥ ትሥቅባቸዋለህ፥ አሕዛብንም ሁሉ ትንቃቸዋለህ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 21, 2021

✞ ✞ ✞ አምላኬ ሆይ፥ ከጠላቶቼ አድነኝ፤ በላዬም ከቆሙት አስጥለኝ። ከግፍ አድራጊዎች ታደገኝ፥ ከደም ሰዎችም አድነኝ። እነሆ፥ ነፍሴን ሸምቀውባታልና፥ ብርቱዎችም በላዬ ተሰበሰቡ። አቤቱ፥ በበደሌም አይደለም፥ በኃጢአቴም አይደለም። እነሆ፥ በአፋቸው አሰምተው ይናገራሉ፤ ሰይፍም በከንፈሮቻቸው አለ፤ ማን ይሰማል? ይላሉ። አንተ ግን አቤቱ፥ ትሥቅባቸዋለህ፥ አሕዛብንም ሁሉ ትንቃቸዋለህ

ድል አድራጊው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ፤ ያ የቀድሞ አመፀኛው አውሬ (ዲያብሎስ) የጥንት ተንኰሉ ሊተወው አልቻለምና፤ የጦር መሣሪያህን ታጥቀህ መጥትህ ድምጥማጡን አጥፋው። ቅዱስ ሚካኤል ሆይ አውሬው ዲያብሎስ በመሀመድ በኩል መጥቶ በሃገረ ኢትዮጵያ፤ በውቅሮ ውስጥ (አል-ነጃሺ) ችግኙን ተክሏልና ከነችግኙ ነቃቅለህ የኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ ውስጥ ጨምረው። አሜን! ✞ ✞ ✞

✞ ✞ ✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፶፰]✞ ✞ ✞

፩ አምላኬ ሆይ፥ ከጠላቶቼ አድነኝ፤ በላዬም ከቆሙት አስጥለኝ።

፪ ከግፍ አድራጊዎች ታደገኝ፥ ከደም ሰዎችም አድነኝ።

፫ እነሆ፥ ነፍሴን ሸምቀውባታልና፥ ብርቱዎችም በላዬ ተሰበሰቡ። አቤቱ፥ በበደሌም አይደለም፥ በኃጢአቴም አይደለም።

፬ ያለ በደል ሮጥሁ ተዘጋጀሁም፤ ተነሥ፥ ተቀበለኝ፥ እይም።

፭ አንተም አቤቱ፥ የኃያላን አምላክ፥ የእስራኤል አምላክ፥ አሕዛብን ሁሉ ትጐበኛቸው ዘንድ ተነሥ፤ ዓመፅ የሚያደርጉትን ሁሉ አትማራቸው።

፮ ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ይራቡ፥ በከተማም ይዙሩ።

፯ እነሆ፥ በአፋቸው አሰምተው ይናገራሉ፤ ሰይፍም በከንፈሮቻቸው አለ፤ ማን ይሰማል? ይላሉ።

፰ አንተ ግን አቤቱ፥ ትሥቅባቸዋለህ፥ አሕዛብንም ሁሉ ትንቃቸዋለህ።

፱ እግዚአብሔር መጠጊያዬ ነውና ኃይሌን ወደ አንተ አስጠጋለሁ።

፲ የአምላኬ ቸርነቱ ይገናኘኛል አምላኬ በጠላቶቼ ላይ ያሳየኛል።

፲፩ ሕግህን እንዳይረሱ አትግደላቸው፤ አቤቱ ጋሻዬ፥ በኃይልህ በትናቸው አውርዳቸውም።

፲፪ ስለ አፋቸው ኃጢአት ስለ ከንፈራቸውም ቃል፥ መርገምንና ሐሰትን ስለሚናገሩ፥ በትዕቢታቸው ይጠመዱ።

፲፫ በቍጣ አጥፋቸው፥ እንዳይኖሩም አጥፋቸው፤ የያዕቆብም አምላክ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ እንዲገዛ ይወቁ።

፲፬ ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ይራቡ፥ በከተማም ይዙሩ።

፲፭ እነርሱም መብል ለመፈለግ ይበተኑ፤ ያልጠገቡ እንደ ሆነም ያንጐረጕራሉ።

፲፮ እኔ ግን ለኃይልህ እቀኛለሁ፤ በምሕረትህም ማልዶ ደስ ይለኛል፤ በመከራዬ ቀን መጠጊያዬና አምባዬ ሆነኸኛልና።

፲፯ ረዳቴ ሆይ፥ ለአንተ ለአምላኬ እዘምራለሁ፤ አንተ፥ አምላኬ፥ መጠጊያዬ ምሕረቴም ነህና።

_____________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: