በጎንደር እና ሐረር ካሉ ‘ክርስቲያኖች’ ይልቅ የቲቤት ተራራ ቡድኻ መነኮሳት ለአክሱም ጽዮን ቀርበዋል
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 14, 2021
❖ ቲቤት ❖ ትግራይ ❖ ተራራ ❖ተዋሕዶ
ይህ በእውነተ በጣም አስገራሚና አስደናቂ መንፈሳዊ/ መለኮታዊ ክስተት ነው። ከአክሱም ጽዮን ፭ሺ፭፻/5500 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኙት ደገኞቹ የቲቤት መነኮሳት የትግራይ ሕዝብ ለቅሶ፣ ጩኸት፣ ከባድ መከራና ስቃይ ተሰምቷቸዋል፤ ለመንፈሳውያን ሰዎች የቦታው ርቀት የሰከንድ ርቀት ያህል ነው።
እኔ በልጅነቴ አገሬን ለቅቄ የወጣሁ የአዲስ አበባ ሰው ነኝ፤ በአክሱምም በአካል ተገኝቼ አላውቅም፤ ነገር ግን ላለፉት አራት ወራት በመንፈስ ወደ ትግራይ ለመጓዝ በቅቻለሁ። እንኳን ኢትዮጵያዊ ሆኖ፣ እንኳን ተዋሕዶ ክርስቲያን ሆኖ፤ እያንዳንዱ በበጎ መንገድ መንፈሳዊ የሆነ ሰው ከአምላኩ ጋር ለመገናኘት በትክክለኛውም መልክ ጸሎት የሚያደርስ ከሆነ የትኛውም ሃገርና ቦታ ቢገኝ የትግራይ አባቶቻንና እናቶቻችን፣ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፤ የህፃናቱ እና አረጋውያኑ ጩኸት በደንብ ይሰመዋል። በተለይ ወደ መኝታ ስንገባ እና በእንቅልፍ ሰዓት ሆነን በታችኛውና (Subconscious Mind) በኃይለኛው ህሊናችን እንቅልፍ እስኪነሳን ድረስ የምናደርሰው ጸሎት/የሚደርሰን መንፈሳዊ መልዕክት የወገኖቻችንን ለቅሶና ጩኸት በደንብ ያሰማናል። ዛሬ የቲቤት ከቀናት በፊት ደግሞ የግብጽ መነኮሳት የተሰማቸው ይህ ነው።
አብዛኛው “ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ ተዋሕዶ ነኝ” የሚለው ይህ ስለማይሰማው ነው ጭጭ ያለው፤ ትክክለኛውን ኢትዮጵያዊነቱን፣ ተዋሕዶ ክርስትናውና መንፈሳዊ ማንነቱንና ምንነቱን ስለተገፈፈ ነው ከአህዛብ ጠላቶች ጋር ተሰልፎ ለእሱ፣ ለቤተሰቡ፣ ለኢትዮጵያ እና ለመላው ዓለም ጸሎት የማድረስ ብቃት ያላቸውን ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ለማስጨፍጨፍ ወደ ትግራይ የዘመተው።
መኩራታቴ አይደልም፤ ግዴታዬ ስለሆነ ነው፤ ላለፉት ሃያ ዓመታት ለግብጽ፣ ለመካከለኛው ምስራቅ፣ ለእስያና ለናይጄሪያ ክርስቲያኖች እንደሚገባኝ ባይሆን በቻልኩት አቅም ያለማቋረጠ ድምጽ ስሆናቸው ቆይቻለው። እንዲያውም ለቤተ ክህነት፤ “ባካችሁ በመሰቃየት ላይ ያሉትን ግብጻውያን ኦርቶዶክስ ወገኖቻችንን ለመደገፍ በአዲስ አበባ አንድ ትልቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሩና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለመላው ዓለም ክርስቲያኖች ድምጽ ትሁን፤ ይህን በማድረግ ከወገኖቻችን ጋር አንድነት ማሳየታችን ብቻ ሳይሆን፤ ችግሩ ወደኛም ሃገር እንዳይመጣ ይረዳል ወዘተ” የሚል ደብዳቤ ጽፌ ነበር። ይህን በጦማሬ ሳስተጋባ ነበር። ለክርስቶስ ልጆች ያልቆመ፣ ድምጽ ለሌላቸው ተበዳዮች ድምጽ ያልሆነ ሰው በፍጹም ክርስቲያን ሊባል አይገባውምና እራሱን ቢመረመር ይሻለዋል።
የዛሬ አስራ ዓምስት ዓመታት ገደማ በቤልጂም ብሩሴል አንድ ዓለም አቀርፍ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉባዔ ላይ ለመገኘት በቅቼ ነበር። ብዙ ኢትዮጵያውያንም ተገኘትው ነበር። ኢትዮጵያውያኑ በተሰባሰቡበት ቦታ በጣም የጦፈ ጭቅጭቅ ተነስቶ ወደ ቦታው አመራሁ እና “ምንድን ነው?” ብዬ ስጠይቃቸው፤ አንዱ ከጎንደር አካባቢ የመጣውና ዶክትሬቱን እየሠራ ያለ ኢትዮጵያዊ “እነርሱ እኮ (ትግሬዎች) ወደኛ ተሰድደው ለዘመናት እየኖሩ ነው… ቅብርጥሴ” በሚል የማንነት ጭቅጨቅ ውስጥ ከሌላው ጎንደሬ ጋር መግባቱን ተረዳሁ። እኔም እንደ እብድ ቆጣ ብዬና ነጮቹ እስኪገርማቸው ድረስ መጮኽ ጀመርኩ፤ “ስሙ፤ ኢትዮጵያን በዚህ መልክ የምታዋርዷትና የምታወርዷት ከሆነ፣ ሕዝቧን እንዲህ ለባዕዳውያኑ አሳልፋችሁ ለመስጠት እየሠራችሁ ከሆነ፤ ያው ቻይናዎቹ ጠጋ ጠጋ እያሉ ነው ለቻይናዎች፤ በተለይ ለኔፓል እና ቲቤት ደገኞች አሳልፈን እንሰጣቸዋለን፤ እነርሱ የተሻሉ ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ አይቀሩም…” ማለቴን አልረሳውም።
❖ ቲቤት ❖ ትግራይ ❖ ተራራ ❖ተዋሕዶ
የቲቤት ሰዎች ምንም እንኳን በይፋ ቡድሃዎች እንጅ ክርስቲያኖች ባይሆኑም ቅሉ በብዙ ነገሮቻቸው ግን ከተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን ጋር በጣም ይመሳሰላሉ፤
❖ መስቀሎቹ
❖ አሰጋገዳቸው
❖ ደወሉ
❖ የጸሎት ባንዲራ ቀለማቱ
በዓለም ከፍተኛው ገዳም ፭ሺ/5150 ሜትር ከፍታ(ዋው! ከኢትዮጵያ እስከ ቲቤቴም ልክ የ፭ሺ፭፻/5500 ኪሎሜትር ርቀት አለ) የሚገኘው በቲቤት ነው። ደገኞቹ የቲቤት ሰዎች በመንፈሳዊነታቸው በሚቀናባቸው በቻይናው ኮሙኒስታዊ ማሕበረሰብ ዘንድ ብዙ አድሎ ይፈጸምባቸዋል። ይህም ደገኞቹ የመንፈስ ማንነትና ምንነት ያላቸው የትግራይ ሰዎች ዛሬ ቆላማዎቹ የስጋ ማንነትና ምንነት ያላቸው ኢትዮጵያ ዘ–ስጋ ከሚፈጽሙባቸው አድሎ ጋር በጣም ተመሳሳይነት አለው።
ውጊያው መንፈሳዊ ውጊያ ነው፤ ውጊያው በእግዚአብሔርና በዲያብሎስ፣ በክርስቶስና በክርስቶስ ተቃዋሚው፣ በደጋማው ሰሜንና በቆላማው ደቡብ እንዲሁም የመንፈስ ማንነትና ምንነት ባላቸውና የስጋ ማንነትና ምንነት ባላቸው ሕዝቦች መካከል ነው። ይህን በሃገራችን በግልጽ እያየነው ነው።
የሰሜን ሰዎች ከዚህ ክስተት መማር ይኖርብናል፤ በተለይ አሁን የትግራይ ወገኖቼ የኮሙኒስት ቻይናን ባንዲራ ማውለብለብ አቁመው የቲቤት የጸሎት ባንዲራዎች የሚያሳዩአቸውን ከአባታችን ኖኽ የማርያም መቀነት የተገኙትን ክቡር ቀለማት “የኔ ናቸው” በማለት መንፈሳዊ ንብረተኛነቱን ማረጋገጥ አለባቸው። መያዝ የማይገባቸው ይዘውታልና!
ይህን በምጽፍበት ወቅት ሰማይ ላይ የታየኝን ሌላ አስገራሚ ክስተት በቀጣዩ ቪዲዮ አቀርበዋለሁ። ጽሑፉን አቋርጬ ነው በፍጠንት ያነሳሁት። ባትሪ እየሞላሁ ነው።
ተዓምር በደመናው ላይ! ኢትዮጵያ + አቡዬ
፭ መጋቢት ፪ሺ፲፫ /14 ማርች 2021 ዓ.ም ❖❖❖ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቡዬ) ❖❖❖ ስለ ቲቤት መነኮሳት ቪዲዮውን ስሠራና ስጽፍ ሰማይ ላይ የታየኝን ሌላ አስገራሚ ክስተት ይህ ነው። ጽሑፌን አቋርጬ በፍጥነት ያነሳሁት ነው።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን እንጂ የሰጣቸው፤ “ወልቃይት እርስቴ!” “ሐረር ኬኛ” ቅብርጥሴ አያውቅም! ኢትዮጵያ ዘ-ስጋ የዋቄዮ-አላህ-አቴቴ አርበኞች ወዮላችሁ!
___________________________________
Leave a Reply