ለኢሳያስና አብዮት ምርኮኛ ወታደሮች ርህራሄ ያሳዩት ትክክለኛዎቹ የአድዋ ኢትዮጵያውያን እነዚህ ናቸው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 2, 2021
☆ ግራኝ አደዋን ለባዕድ ወራሪ ኃይል ሰጥቶ እያስጨፈጨፋት ነው
☆ ግራኝ ሱዳን ወደ ጎንደር እንድተገሰስ በአደዋ ክብረ በዓል ዕለት ፈቀደላት
☆ አሜሪካ በአደዋ ክብረ በዓል ዕለት በግራኝ ላይ ግፊት አደረገች
👉 ልዩነቱ ይህ ነው፤
በትግራይ ሰራዊት የተማርኩትን የኢሳያስና አብዮት ቅጥረኛ ወታደሮች (ስንት እናት ልጇን እየጠበቀች ታለቅስ ይሆን?) እንዳይገሏቸው የአደዋ ልጆች መቀየሪያ ልብስ ሰጥተው ሲደብቋቸው። ይህን ሊያደርጉ እንደሚችሉ አምናቸዋለሁ።
“የአባይ ግድብ ሁለተኛ አድዋችን ነው!” ምናምን የሚል መፈክር ዛሬ በተከበረው በዓል ላይ አይቼ ነበር። እውነቱ ግን የዓድዋ ድል እና የኣባይ ግድብ የሚያመሳስላቸው ሰሪው የአድዋ ልጅ አክባሪው ከሃዲው ትውልድ መሆኑ ነው።
የአድዋን ህዝብ እየጨፈጨፉ፣ አደዋን ለባዕድ የአህዛብና ጣልያን ቅጥረኛ አስረክቦ፣ ሆን ብሎ በዛሬው ዕለት ሱዳንን ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ጠልቃ እንድትገባ ት ዕዛዝ ሰጥቶ የአድዋ ድል እናከብራለን ብሎ በግብዝነት ሲወጣ እንደማየት የሚያሳፍርና የሚያስቆጣ ነገር አይኖርም።
እንዲያውም ከደቂቃዎች በፊት ልክ በዚሁ በአደዋው ድል የቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንኬን ማክሰኞ በትግራይ ክልል የተካሄደውን ጦርነት ለማቆም በአረመኔው ግራኝ አብዮት አህመድ ላይ ጠበቅ ያለ ግፊት አደረጉ ፣ “የጭካኔ ድርጊቶች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና የመብት ጥሰቶች የሚታመኑ ዘገባዎች አሉን”በማለት ጠቅሰዋል፡፡ የአድዋው ድል በሚከበርበት ዕለት ይህ ማስጠንቀቂያ ከባዕድ ሃገር መምጣቱ እራሱ ኢትዮጵያ ምን ያህል እንደተዋረደች ነው የሚጠቁመን። የህልመኛው ግራኝ ተልዕኮ ኢትዮጵያን አዋርዶና ፈረካክሶ የኦሮሚያ ኩሽ ሪፐብሊክን መመስረት አይደል። ማለም ይፈቀዳል፤ ግን ይህ ቆሻሻ ከእነ ዘር ማንዘሩ በቅርቡ በእሳት እንደሚጠረግ እርግጠኛ ነኝ!
____________________________
Leave a Reply