Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

የአድዋው ድል የአክሱም ጽዮን ነው ፥ ኮከቧም ጀግናው ራስ አሉላ ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 1, 2021

👉 ከአድዋው ድል በጥቂቱ ፹፭%/85% የሚሆነውን ድርሻ የሚወስደው ብዙ ያልተባለለትና ያልተዜመለት የትግራይ ሕዝብ እንደሆነ ዛሬ በግልጽ እያየነው ነው። ለመላው የዓለማችን ጥቁር ሕዝቦች ተስፋ እና ኩራት የሆነችው የአደዋ ከተማ በኢትዮጵያ ጠላት፣ በጥቁር ሕዝቦች ጠላት፣ በትግራይ ሕዝብ ጠላት፣ በተዋሕዶ ክርስትና ጠላት በአረመኔው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ተደበደበች። ለወንጀሉ በጣም አሳሳቢ በሆነ መልክ ክብደት የሚሰጠው፤ አደዋ ዛሬ ድብደባውና ጭፍጨፋው የጣልያን ቅኝ በነበረችው ኤርትራ አማካኝነት መካሄዱ ነው። ከግራኝ አህመድ የከፋ አረመኔ አራት ኪሎ ቤተ መንግስት ውስጥ ተቀምጧል፤ ከበስተጀርባውም ቀላል ነው የማይባል ቁጥር ያለው “ኢትዮጵያዊ ነኝ” ባይ ከሃዲ የኢትዮጵያ ጠላት ለድጋፍ መቆሙ ነው። ለመላው የጥቁር ሕዝቦች ተስፋና ኩራት የሆነችውን የአደዋን ከተማ እና ነዋሪዎቿን ለማጥፋት። እጅግ በጣም አስገራሚ ነው! እነ አሉላ አባ ነጋ እጅግ በጣም እያዘኑ ነው፤ እነ ቤኒቶ ሙስሎሊኒ ጮቤ እየረገጡ ነው።

ጠላት ልክ ከዘጠና፣ ከሃምሳና ከሰላሳ ዓመታት በፊት በዋቄዮ-አላህ የባርነትና ሞት ሥርዓትና አመራር ውስጥ የወደቀችዋ ምስኪኗ ኢትዮጵያ ሃገራችንን ወደ ገደል ሲመሯት እንደነበረው ዛሬም ወደ ጥልቁ ገደል የሚመሯት ከሃዲዎችም ጦርነቱን ወደ አክሱም/አደዋ በመውሰድ ልክ እንደ ያኔው ሕዝቡን ለመጨረስ፣ ተፈጥሮውን፤ ማለትም ውሃውን፣ ዛፉንና ሰብሉን ሁሉ በማጥፋትና በመበከል ላይ ናቸው፤ ገና ብዙ ሌላም ዲያብሎሳዊ ዕቅድ አላቸው። ግን፤ እነዚህ አረመኔዎች እራሳቸው አንድ በአንድ ያልቋታል እንጅ ህልማቸው ሁሉ በጭራሽ አይሳካላቸውም።

አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ናት፤ ነገር ግን ለኢትዮጵያ በጣም ብዙ ባለውለታዎች የሆኑት ጀግናዎቹ አፄ ዮሐንስ እና ራስ አሉላ የመታሰቢያ ኃውልት፣ ቦታ፣ ትምህርት ቤት፣ ተቋም ወይንም መንገድና አደባባይ እንኳን አልተሰራላቸውም/አልተሰየመላቸውም። ቅዱሱ አባታችን ያሬድ እንኳን አንዲት ቤተ ክርስቲያን እና የሙዚቃ ትምህርት ቤት ብቻ ነው ያለው። ይህን እግዚአብሔር የሚያየው ነው፤ ሌላ ምንም። እነ ቦብ ማርሌ፣ ጆሞ ኬኒያታ፣ ካርል ሃይንስ ቡም፣ ዊንስተን ቸርችል፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን፣ ጀርመን ወዘተ ሳይቀሩ የከተማዋን ቦታዎች ሁሉ አሸብርቀውባታል። ከሃዲ ትውልድ!

👉 እስከ ጥቅምት ፳፬/፪ሺ፲፫ ድረስ አድዋ፤ የጥቁር ህዝብ ኩራት ነበር

ትናንትና አድዋን ለማክበር ወደ አድዋ የሄዱትን ሁሉ እግራቸውን ያጠቡትን እናቶች እግራቸውን የቆረጠ፣ እንጀራ የስጡትን እናቶች እጃቸውን የቆረጠ ትውልድ እውነት ዛሬ አድዋን ሊያከብር ይገባዋልን? በጭራሽ!

👉 ሐቋን ዋጥ እናድርጋትና የዚህ ሁሉ አሳዛኝና አሳሳቢ ክስተት መንስዔ የሚከተለው ነው፦

[ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ ፴፪፥፮፡፳፫]

“ደንቆሮ ብልሃተኛም ያልሆንህ ሕዝብ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ይህንን ትመልሳለህ? የገዛህ አባትህ አይደለምን? የፈጠረህና ያጸናህ እርሱ ነው።

የዱሮውን ዘመን አስብ፥ የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል፤ አባትህን ጠይቅ፥ ያስታውቅህማል፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ ይነግሩህማል።

ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን ባወረሰ ጊዜ፥ የአዳምን ልጆች በለየ ጊዜ፥ እንደ እስራኤል ልጆች ቍጥር የአሕዛብን ድንበር አቆመ።

የእግዚአብሔር እድል ፈንታ ሕዝቡ ነው፤ ያዕቆብም የርስቱ ገምድ ነው።

በምድረ በዳ በጥማት፥ የነፋስ ጩኸትም በሞላበት ውድማ አገኘው፤ ከበበው ተጠነቀቀለትም፤ እንደ ዓይን ብሌን ጠበቀው።

ንስር ጫጩቶቹን እንደሚያወጣ፥ በእነርሱም ላይ እንደሚሰፍፍ፥ ክንፎቹን ዘርግቶ ወሰዳቸው፥ በክንፎቹም አዘላቸው።

እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም።

በምድር ከፍታ ላይ አወጣው፤ የእርሻውን ፍሬ በላ፤ ከዓለትም ድንጋይ በሚገኝ ማር፥ ከጭንጫውም ድንጋይ በሚገኝ ዘይት አጠባው፤

የላሙንም ቅቤ፥ የመንጋውም ወተት፥ ከጠቦት ስብ ጋር፥ የባሳንንም አውራ በግ፥ ፍየሉንም፥ ከስንዴ እሸት ጋር በላህ፤ ከወይኑም ደም ያለውን ጠጅ ጠጣህ።

ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤ የፈጠረውንም እግዚአብሔርን ተወ፤ የመድኃኒቱንም አምላክ ናቀ።

በሌሎች አማልክት አስቀኑት፥ በርኵሰታቸውም አስቈጡት።

እግዚአብሔር ላልሆኑ አጋንንት፥ ለማያውቋቸውም አማልክት፥ በቅርብ ጊዜ ለተነሡ ለአዲሶች አባቶቻቸውም ላልፈሩአቸው አማልክት ሠዉ።

የወለደህን አምላክ ተውህ፥ ያሳደገህን እግዚአብሔርን ረሳህ።

ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ስላስቈጡት እግዚአብሔር አይቶ ጣላቸው።

እርሱም አለ። ፊቴን እሰውርባቸዋለሁ፤ ፍጻሜያቸው ምን እንደ ሆነ አያለሁ፤ ጠማማ ትውልድ፥ ያልታመኑም ልጆች ናቸው።

አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ 3 ቍ.15፤ በዕብራይስጥ ይሹሩን የሚለውን ግዕዙ ያዕቆብ ይለዋል። በምናምንቴዎቻቸውም አስቈጡኝ፤ እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤ በማያስተውል ሕዝብ አስቈጣቸዋለሁ።

እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፥ ምድርንም ከፍሬዋ ጋር ትበላለች፥ የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች።

መከራን እጨምርባቸዋለሁ፤ በፍላጾቼም እወጋቸዋለሁ።”

ይህ ከብዙ ዘመናት በፊት የእስራኤል ልጆች ለእግዚአብሔር የተለዩና የተቀደሱ ተብለው የእርሱን ስምና ክብር የወረሱበት የህይወት ህግና ሥርዓት አሁን ላለን ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የሚያስተላልፍልን መለኮታዊ ሀሳብ፤ እግዚአብሔር አምላክ እንደ እስራኤል ልጆች ሁሉ ኢትዮጵያውያንንም የ”እኔ” ብሎ “ልጆቼ” ያላቸው በምድር አፈር በኩል በተግለጠው ህግና ሥርዓት በኩል ነበር።

ኢትዮጵያውያን ልክ እንደ እስራኤል ልጆች ሁሉ ይህን “እግዚአብሔር” ብለው የወረሱትን የተፈጥሮ ህግ ካፈረሱና ከጣሱ እንዲሁም ለእነርሱ ያልሆኑት የአህዛብን አማልክት በምድሪቱ ውስጥ ሲያጥኑና ሲያመልኩ ከተገኙ እነርሱም ለእስራኤል ልጆች እንደተነገራቸው ቃል ሁሉ በሞትና በባርነት ፍርድ ከተቀደሰችው ምድር ይነቀላሉ። እግዚአብሔር አምላክ የእስራኤልን ልጆች በተናገረበት ቃል ሁሉ ደግሞ ኢትዮጵያውያንን ተናግሯልና።

በዚህም መለኮታዊ ቃል መጠን የተገለጠውና ለተቀደሰችው ምድር ለኢትዮጵያ ጥፋትና ሞት የሆነው ትውልድ ደግሞ የአፄ ምኒልክ ትውልድ ይሆናል ማለት ነው። ለዚህ ታላቅ የሕይወትና የነጻነት የበረከትና የገዥነት ኪዳን መፍረስ ዋናው ተጠያቂው ይህ ደካማ ትውልድ ነው። ያን ታላቅና ሊነገር የማይችል ፅኑ ፍቅር በብዙ ተዓምራቶችና በብዙ ድንቆች ያየና የተመለከተ ህዝብ ነው ያን የሕይወት ኪዳን ሽሮ የሊሎችን/የአህዛብን አማልክት ለመተልና ለማምለክ ወደ ኋላው የተመለሰው። የአድዋ የነፃነት ተጋድሎ ብቻ ስለዚህ የህወትና የነጻነት የገዥነትና የበረከት ኪዳን ኃይልና ስልጣን እጅግ ብዙ ነገር ነበረው። አሸናፊ፣ አዳኝ፣ ገዥ እንዳልሆነ በዚያም የጥፋ ህግ ምንም ዓይነት በረከትም ይሁን የነጻነትና ህይወት እንደሌለ እግዚአብሔር አምላክ ሊዋሽ በማይችል ምስክር በዓለም ሁሉ ፊት በምድርና በሰማይ በዚህ ህዝብ ላይ አስመስሮበታል። ይሁን እንጅ ለመመለስ የተጸጸተ ትውልድ አልነበረም።

በኢትዮጵያ ታሪክ ባልታየውና እጅት ታላቅ በተባለለት በዛ ጽኑ የረሀብ ዘመን ኢትዮጵያውያን የሚላስና የሚቀመስ አጥተው ሲቅበዘበዙ ምግብና መጠጥ ሆኖ ያዳናቸውን፣ በምድረ በዳም ተዘግተው በቅኝ ግዛት ሊገዛቸው በፊታቸው ከተገለጠው እጅግ አስፈሪ የሞትና የጥፋት መንግስት የተነሳ የሚታደጋቸው አንድ ሰው አጥተው በሞት ፍርሀት ታስረው ሲታወኩና ሲጨነቁ ሳሉ በሚደነቅ ምህረት በብዙ ፍቅር በመካከላቸው ተገኝቶ ያጽናናቸውን፣ በዘመናዊ የጦር መሳሪያ በእጅጉ የተደራጀውን በወታደራዊ ዕውቀትና ጥበብም የተካነውንና ሊሸነፍ አይችልም የተባለውን ግዙፉን የኢጣልያንን ጦር በተዘረጋች ክንድ በበረታችም እጅግ ፅኑ እጅ ስብርብሩን አውጥቶ በፊታቸው ያባረረላቸውን፣ ገዳዩን ገድሎ፣ አሳሪውን አስሮ ፣ አጥፊውን አጥፍቶ ፣ በዓለም ሁሉ ላይ እጅግ የገነነውን ሁሉን ገዥ ስምና ክብር የሰጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ የሰራዊት ሁሉ ጌታ እግዚአብሔርን ያ ትውልድ በአይኑ አይቷል፤ ተመልክቷልም። ኢትዮጵያውያንም ብቻ ሳይሆኑ ዓለም ሁሉ አይቶታል ተመልክቶታል። ያ የእግዚአብሔር ድንቅ ፍቅር የቀመሰ ትውልድ ነው እንግዲህ የእግዚአብሔርን ኪዳን አፍርሶ ለእርሱ ላልሆኑ ለአህዛብ አማልክት ሊያጥንና ሊሰግድ ራሱን ለሞትና ለባርነት አሳልፎ የሰጠው። ምንም እንኳ በተደጋጋሚ ቢናገራቸውም መልሰው ለኃጢአት ባሪያ እንደሚሆኑት እንደ እስራኤል ልጆች ሁሉ ኢትዮጵያውያንም የእግዚአብሔርን እጅግ ታላቅ ውለታና ፍቅር ረስተውና አቅልለው በፊቱ ታላቅ ርኩሰትን አደረጉ።

የእግዚአብሔር ቃል ለዚህ ታላቅ ቅሌትና አመጻ ተጠያቂ ያደረገው ደግሞ በዋናነት “ይሹሩን” በማለት የገለጸውን በዚያ ህዝብና መንግስት ላይ ኃይልና ስልጣን ያላውን አለቃ ወይም መሪ ነው። ይሹሩን በማለት ሙሴ የገለጸው በእርግጥ ለአስራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል አባትና አለቃ የሆነውን ያዕቆብን ነው። አስራ ሁለቱ ነገዶች እንደመንግስታን እንደ ሀገር የተመሰረቱት በአባታቸው በያዕቆብ እስራኤል በሚለው ስምና ክብር ነበርና። ይሹሩን የያዕቆብ ሌላው ስም ነው። እንደ ሙሴ አገላለጽም ይሁን እንደ ህጉ አንድ ለእግዚአብሔር ስምና ክብር የተመረጠ ህዝብ ለጥፋት በሚሆን የሞትና የባርነት ህግ የሚያዘው በዚያ ህዝብ ላይ ኃይልና ስልጣን ባለው አንድ ሰው አለመታዘዝ ምክኒያት ነው። የዛ ህዝብ ማንነትና ምንነት በመሪው ማንነትና ምንነት የሚገለጽ ስለሆነ የመሪው ጥፋት ማለት በሌላ አባባል የዚያ ትውልድ/ህዝብ ጥፋት ማለት ይሆናል። ልክ ዛሬ እንደምናየው!

ለተቀደሰችው ምድር ርኩሰት፣ ለታላቋና ለገናናዋ ሀገር ለኢትዮጵያ ጥፋትና ውድቀት በዋናነት ተጠያቂ የሚሆኑት በእግዚአብሔር ስምና ክብር ተመርጠው “ሞዓ አንበሳ እም ዘነገደ ይሁዳ ምኒልክ ስዩመ እግዚአብሔር ንጉሰ ነገስት ዘ-ኢትዮጵያ” ተብለው የነገሱት አፄ ምኒልክ ናቸው። (ልብ እንበል! አፄ ምኒልክ በአክሱም ጽዮን ተቀብተው ያልነገሱ ብቸኛው የኢትዮጵያ ንጉሥ ናቸው)። አፄ ምኒልክ ከአደዋው ድል በኋላ ለድሉ ያበቃቸውን አምላካቸውንና ጽዮን ማርያምን በመካድ ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸውን የህይወት ኪዳን አፍርሰው የጥፋትና የሞት የባርነት አማልክት ማንነትና ምንነት በመትከላቸው ለኢትዮጵያ ጥፋትንና ውድቀትን አስከትለዋል። ውጤቱን ዛሬ እያየነው ነው!

❖❖❖ራስ አሉላ እንግዳ ( አሉላ አባ ነጋ)❖❖❖

👉 ” አባ ነጋ አሉላ ካሥመራ ቢነሳ

እንዳንበሳ ሆኖ እሳት እያገሳ

የችግር ምስጋና ባይነሳ

ቢቸግረው ጣሊያን አለ ፎርሳ ፎርሳ”

ራስ አሉላ በ፲፰፻፵፯/1847 በተምቤን ዙቁሊ ሚካኤል እንደተወለዱ ማሞ ውድነህ በ፲፱፻፹፯/1987 የዶጋሊ ጦርነትን 100ኛ ዓመት በማስመልከት በተዘጋጀው ልዩ የመታሰቢያ ታሪካዊ ጉባዔ ላይ ባቀረቡት ጽሁፍ ይገልፃሉ፡፡ በጊዜዉ የሚሠጠዉን ትምህርትም በዙቁሊ ሚካኤልም ከመምህር ወልደጊዮርጊስ እንደተማሩ ማሞ በጽሁፋቸዉ ገልፀዋል፡፡

አሉላ ወዲ ቁቢ የጉርምስና ጊዜያቸዉን በአጼ ዮሐንስ አጎት በራስ አርአያ ድምፁ ቤት አሽከር በመሆን እንደጀመሩ ንጉሴ አየለ (ፕ/ር)“Ras Alula and Ethiopia’s Struggle Against Expansionism and Colonialism ፲፰፻፯፪፲፰፻፺፯/1872-1897” በተሰኘ መጣጥፋቸው ገልጸዋል፡፡ እንደ ፕ/ር ንጉሴ ገለፃ ራስ አሉላ በስተኋላ ወደ ደጃዝማች በዝብዝ ካሳ (ኋላ አፄ ዮሐንስ ፬ተኛ) ቤት ከተዛወሩ በኋላ ሹመትን በሹመት በመደረብ ወደፊት ገሰገሱ፡፡ በመጀመሪያ እልፍኝ አስከልካይ ቀጥሎም አጋፋሪነትን ተሾሙ፡፡ በ፲፰፻፸፫/1873 ደጃዝማች ካሳ ንጉሰ ነገስት አጼ ዮሐንስ አራተኛ ሲባሉ አሉላ የሻለቅነትን ማዕረግና የንጉሱ ሊጋባነት ማዕረግን ደርበው ያዙ፡፡

አሉላ ወዲ ቁቢ ሁለንተናቸው ስሁል፣ ንቁ እና አርቆ አሳቢ እንደነበሩ ብዙ ጸሐፊዎች፣በጦር ሜዳ ውሎ የሚያውቋቸው፣ በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚውቋቸው ሁሉ ይመሰክራሉ፡፡ ዛሬ ላይ ሆነው ነገን የሚመረምሩ ከራስ በላይ ሀገርን የሚስቀድሙ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነበሩ አሉላ ወዲ ቁቢ፡፡ መርዕድ ወልደ አረጋይ (ፕ/ር) “Alula, Dogali and Ethiopian Unity” በሚል ጽሁፋቸው ከአሳዛኙ የአፄ ቴዎድሮስ የመቅደላ ፍፃሜ በፊትም ሆነ በኋላ አፄ ቴዎድሮስን የመሰለ አንድ ሰው ቢኖር አሉላ አባ ነጋ ብቻ ናቸው ይላሉ፡፡ እንደ ፕ/ር መርዕድ ገለፃ ከሆነ ራስ አሉላ ከአጼ ቴዎድሮስ ጋር በተክለ ሰውነት መመሳሰል ባለፈ በሰብዕና እና በአመለካከት እንዲሁም በአርቆ አሰተዋይነት እና በመንፈሳዊ ልዕልና ይመሳሰላሉ፡፡ ግብርን ለሀገር ጥንካሬ ከማዋል ባለፈ አንድ የጦር መሪ ከተራው ወታደር የተለየ መብላት እና መልበስ እንደሌለበትም ሁሉቱ የኢትዮጵያ ጅግኖች ተመሳስሎ እንደሆነ ፕ/ር መርዕድ ያስረዳሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ማሞ ውድነህ “The Life and Works of Alula Aba Nega” በሚለው መጣጥፋቸው አሉላ ወዲ ቁቢ በ፲፰፻፵፯/1847 እንደመወለዳቸው ስለ አፄ ቴዎድሮስ ጀግንነት እና ትልቅነት እየሰሙ ማደጋቸውን ያብራራሉ፡፡

ራስ አሉላ ከነበራቸው የጦር ብልሀት እና እንዲሁም ደግሞ የተዋጣለት ዲፕሎማት መሆን የተነሳ በአፄ ዮሐንስ ፊት ሞገስ እና ክብር ነበራቸው፡፡ ለዛም ነው ከአሽከርነት እስከ ራስነት ሹመት የደረሱት፡፡ በታሪክ ዘመናቸው በዋናነት ለአፄ ዮሐንስ የቀኝ እጅ በመሆን በወቅቱ ንጉሱን ከገጠማቸው የስልጣን ሽኩቻ በተለይ ከጎጃም እና ከሸዋ ከማደላደል ባሻገር ከሶስት ዋና ዋና የኢትዮጵያ የወቅቱ ጠላቶች ጋር ተዋግተዋል፡፡

ከህዳር ፲፮/16 ቀን ፲፰፻፸፭/1875 ከተደረገው የጉንደት ጦርነት እስከ የካቲት ፳፫/23 ቀን ፲፰፻፹፰/1888 ዓ/ም እስከተደረገው የዓድዋ ጦርነት ድረስ ራስ አሉላ አባ ነጋ አስራ ሁለት ጦርነቶችን ከውጭ ወራሪ ኃይሎች ጋር የተዋጉ ሲሆን በዋናነትም ከኦቶማን ግብጽ ተስፋፊዎች፣ ከማህዲስት የድርቡሽ ወራሪዎች እና ከጣሊያን ቅኝ ገዥዎች ጋር ያደረጓቸው ናቸው፡፡

ስለ ራስ አሉላ አባ ነጋ ጀግንነት በርካታ ጸሐፍት ብዙ ብለዋል። ከነዚህ መካከል ኢጣሊያዊው ተርጋሊኖ ጋንዶልዬ ጽፎት በማሞ ውድነህ በተተረጎመው ” አሉላ አባ ነጋና የኢጣሊያ ሰላዮች” በተሰኘው ፅሁፍ ይህን ማራኪ የራስ አሉላ ቃል እናገኛለን…

” የኢትዮጵያን ወታደሮች አታውቃቸውም? እንደ ወፍ ይበራሉ! እንደሰስ ይሮጣሉ ወደ ጠላታቸው ምሽግ ለመገስገስ ከቶ አያመነቱም። እውነተኛውን የጀግንነት ሙያ በእውነተኛው ቦታ ላይ ያሳያሉ፤ ያስመሰክራሉ። ተራራና ገደል ወንዝና አሸዋ አያግዳቸውም። በመሬት ላይ ምን ቢሆን የእነርሱን ብርታት የሚፈታ ችግር የለም….”

አሉላ አባ ነጋው በ፲፰፻፹፱/1889 ዓ.ም በተወለዱ በሰባ አመታቸው አርፈው ዓድዋ በሚገኘው በዚህ የአባ ገሪማ ገዳም ተቀበሩ። የጣሊያን ጋዜጣም “ጎራዴውን ወደ እኛ እንደመዘዘ ወደአፎቱ ሳይመልሰው አሉላ ሞተ” ብሎ ዘገበ።

💭 ከእረፍታቸው በኋላም ህዝብ እንዲህ ሲል አንጎራጉሯል፤

እነዚህ ጣልያኖች እጅግ ተደሰቱ

የአሉላ ጎራዴ ሲበርድ ስለቱ

በሮም አደባባይ መድፍ ተተኮሰ

ምጽዋም ተሰምቶ መድፍ ተተኮሰ

አሥመራም ተሰምቶ መድፍ ተተኮሰ

የተደአሊ ደሙን ብድሩን መለሰ

ዓድዋ ያረረውን አንጀቱን አራሰ

አሉላ አባነጋ ክንዱን ተንተራሰ

ጣልያን እልል አለ የልቡ ደረሰ።

_________________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: