ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን | መዝሙረ ዳዊት ፻፴፯
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 28, 2021
👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም
የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው። ጦርነት ይሽራል። ቀስትን ይሰብራል፥ በእሳትም ጋሻን ያቃጥላል። እጅህ አሕዛብን አጠፋች፥ እነርሱንም ተከልህ፤ አሕዛብን ሣቀይኻቸው አሳደድኻቸውም። በሰይፋቸው ምድርን አልወረሱም ክንዳቸውም አላዳናቸው፤ ቀኝህና ክንድህ የፊትህም ብርሃን ነው እንጂ ወድደሃቸዋልና።
የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው። የእግዚአብሔርን ሥራ፥ በምድር ያደረገውንም ተኣምራት እንድታዩ ኑ። እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ጦርነት ይሽራል። ቀስትን ይሰብራል፥ ጦርንም ይቈርጣል በእሳትም ጋሻን ያቃጥላል። ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።
[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፵፫]
፩ አቤቱ፥ ፍረድልኝ፥ ከጽድቅ ከራቁ ሕዝብም ክርክሬን ተከራከር፤ ከሸንጋይና ከግፈኛ ሰው አድነኝ።
፪ አንተ አምላኬ ኃይሌም፥ ለምን ትተውኛለህ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመላለሳለሁ?
፫ ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ።
፬ ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ፥ ጕልማስነቴንም ደስ ወዳሰኛት ወደ አምላኬ እገባለሁ፤ አቤቱ አምላኬ፥ በበገና አመሰግንሃለሁ።
፭ ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።
[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፵፭]
፩ አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።
፪ ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም።
፫ ውኆቻቸው ጮኹ ተናወጡም፥ ተራሮችም ከኃይሉ የተነሣ ተናወጡ።
፬ የወንዝ ፈሳሾች የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሰኛሉ፤ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ።
፭ እግዚአሔር በመካከልዋ ነው አትናወጥም፥ እግዚአብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል።
፮ አሕዛብ ተናወጡ መንግሥታትም ተመለሱ፤ እርሱ ቃሉን ሰጠ፥ ምድርም ተንቀጠቀጠች።
፯ የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።
፰ የእግዚአብሔርን ሥራ፥ በምድር ያደረገውንም ተኣምራት እንድታዩ ኑ።
፱ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ጦርነት ይሽራል። ቀስትን ይሰብራል፥ ጦርንም ይቈርጣል በእሳትም ጋሻን ያቃጥላል።
፲ ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።
፲፩ የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።
❖❖❖በጥንታዊው ደንገላት ቅድስት ማርያም ገዳም የተገደሉት ፵፱/49 የዘመኑ ሰማዕታት ስም ዝርዝር❖❖❖
👉 በወረዳ ሳዕሲዕ ❖ ጣብያ በለሶ ❖ በጥንታዊው ደንገላት ቅድስት ማርያም ገዳም❖
በ ሕዳር ፳፩/21 ፪ሺ፲፫ ዓ.ም ፵፱/49 ቀሳውስት እና ምዕመናን በኢሳያስ አፈቆርኪ እና ግራኝ አብዮት አህመድ ፋሺስታዊ ሠራዊቶች ጂኒው ብርሃኑ ጁላ እንዳቀደው ልክ በቅድስት ማርያም ዕለት ተገደሉ፤ ግን አልሞቱም፤ አራት መቶ ዘጠኝ ሚሊየን በጥይትና በሜንጫ የማይመቱ ኃያላን መናፍስት ሆነው በመመለስ ገዳዮቻቸውንና አጋሮቻቸውን የሲዖል በር እስከሚከፍትላቸው ዕለት ድረስ እንቅልፍ ይነሷቸዋል።
👉 የስም ዝርዝሩን በ PDF ለማየት ወደ ጦማሬ ይግቡ፦ https://wp.me/piMJL-5Bh
____________________________
Leave a Reply