Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • February 2021
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

በራዕይ የታየው ትግራዋይ ኢትዮጵያዊ | የአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያንን በጽዮን ቀለማት ቀባ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 22, 2021

❖ ❖ ❖ አባታችን አቡነ አረጋዊ ድንቅ አባት ናቸው።

👉 በቪዲዮው፤

❖ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን(አዲስ አበባ-ሳሪስ)

መስከረም ፪ሺ፯/2007 ዓ.ም(ያለ ጽዮን ማርያም ቀለማት)

አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን (አዲስ አበባ-ሳሪስ)

❖ መስከረም ፪ሺ፲፩/2011 ዓ.ም (ከጽዮን ማርያም ቀለማት ጋር)

አንድ ባካባቢው የሚኖርና እንጀራ በመሸጥ የሚተዳደር ትግራዋይ ወጣት የቤተ ክርስቲያኗን ጣራ በአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማት እንዲያስቀባ በታየው ራዕይ በመታዘዙ በራሱ ወጭ እንዲህ አሳምሮ አስቀብቶታል። (ድንቅ ነው!)

👉 በትናንትናው የአቡነ አረጋዊ ዕለት፤ የነነዌ ጾም በሚገባበት ወቅት፤ የአህዛብ የጥፋት (ሰ)አራዊት በትግራይ ላይ የመጨረሻ የሚሆነውን ጭፍጨፋውን ማጧጧፉና ወደ ተከዜ ግድብ ማምራቱም በደንብ ታስቦበት ነው።

በአቡነ ተክለ ሐይማኖት ዕለት በትግራይ ላይ የክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች የጀመሩት ስጋዊ ጥቃት ለምን አክሱም ጽዮንን፣ ደብረ አባይን እና ደብረ ዳሞ ገዳማትን አስቀድመው ማጥቃት እንዳስፈለጋቸው ሁላችንም እያየነው ነው። ይህ ከዚህ በፊት በሺህ አራት መቶ ዓመታት ውስጥ ያልታየ ክስተት እንደሆነ ልብ እንበለው።

ዘንድሮ በትግራይ ላይ የተከፈተው ጥቃት ከመቶ ሰላሳ ዓመታት በፊት ኤዶማውያኑ አውሮፓውያንና እስማኤላውያኑ አረቦች በአፄ ምኒሊክ በኩል የጀመሩትን ጥቃት አጠናክሮ የቀጠለ ነው። በተለይ ኤርትራ እና ጂቡቲ በክርስቶስ ተቃዋሚው ኃይል ቁጥጥር ውስጥ እንዲገቡ ሲደረጉ ልክ ዛሬ አህዛብ መናፍቃኑ ግራኝ አብዮት አህመድ እና ኢሳያስ አፈቆርኪ ተግተው በስኬት እየሠሩት እንዳሉት ፥ ዋናው ዓላማቸው፤

፩ኛ. ኢትዮጵያዊነትን

፪ኛ. አክሱም ጽዮንን(ጽላተ ሙሴን)

፫ኛ. አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ሰንደቁን

፬ኛ. ተዋሕዶ ክርስትናን

❖ የኢትዮጵያና ተዋሕዶ ክርስትና የጀርባ አጥንት ከሆኑት ከትግራውያን መንጠቅ ነው።

👉 በዚህም ተጠቃሚዎቹ፤

፩ኛ. ኢትዮጵያ/እስራኤል ዘ-ስጋ

፪ኛ. አህዛብ የዋቄዮ-አላህ ልጆች

፫ኛ. መናፍቃን

፬ኛ. ኢ-አማንያን

፭ኛ. ሰዶምና ገሞራ(ግብረ-ሰዶማውያን)

👉 ሁሉም ኢ-አማንያን 666 የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ናቸው።

ጽላተ ሙሴን የአክሱም ጽዮን ልጆች ውስጥ እንደተቀበረ አድርገን እንውሰደው። ምዕራባውያኑ የቴክኖሎጂው ባለቤቶች የጽላቱን ‘ጨረር’ እያንዳንዱ ያልተበከለ የአክሱም ጽዮን ልጅ ውስጥ እንዳለ የመለካት/የማየት ችሎታው/አጋጣሚው አላቸው። ይህንንም ጨረር ከግለሰቦቹ ፈልቅቀው ለማውጣት (ጽላተ ሙሴን ለመስረቅ) እንደማይቻላቸው አይተዋል። ስለዚህ ልክ የአውሬውን 666 ምልክት በፈቃዱ ግንባሩና እጁ ላይ ለማስቀበር እንደሚሻው የወደቀ ሰው እያንዳንዱ የጽላተ ሙሴ ‘ተሸካሚ’ የአክሱም ጽዮን ልጅም ኢትዮጵያዊ መልኩን፣ ተዋሕዶ እምነቱንና ሰንደቁን በፈቃዱ እንዲያስረክብ የተለያዩ ፈተናዎችን እያቀረቡለት ነው። ዛሬ በትግራይ ላይ የተከፈተው ጦርነት ከመቶ ሰላሳ ዓመታት በፊትም በትግራይ ላይ የተከፈተው ጦርነት(አደዋ)ቀጣይ ደረጃ ነው። ያኔ አባቶቻችን እና እናቶቻችን ኢትዮጵያዊነታቸውን፣ ተዋሕዶ እምነታቸውንና ጽዮን ማርያም እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ያስዋቡትን ሰንደቃቸውን ለጥያቄ እንኳን አቅርበዋቸው አልነበረም፤ በዚህም እስካፍንጫው የታጠቀውን ወራሪ የዔዶማውያን ኃይል ድል ሊያደርጉት ተችሏቸው ነበር።

ይህ ትውልድም እራሳቸውን ለአውሬው አሳልፈው በሸጡ ደካሞች ተንኮል ሳይታለልና ሳይሸነፍ “እምብዬው ማንነቴንና ምንነቴን አሳልፌ አልሰጥም!” ማለት አለበት። አልያ ከኢርትራውያን የከፋ ዕጣ ፈንታ ነው የሚደርሰው።

ከአድዋው ድል በኋላ የስጋ ማንነትና ምንነት ያላቸው ደቡባውያን(ጋላማሮች)ኢትዮጵያን መረከብ እንደጀመሩ የአደዋውን ድል የመንፈስ ማንነትና ምንነት ያላቸው የአክሱም ጽዮን ልጆች እንዳስገኙት በመገንዘባቸውና እነርሱንም/ይህንም ለመዋጋት በክህደት ወደ አህዛብ እውቀትና ጥበብ በመዞር በተለይ ኤዶማውያኑን አውሮፓውያኑን በጣም ማስጠጋት ጀመሩ። በመጀመሪያ ያኔም አፄ ምንሊክ ኤርትራንና ጂቡቲን ለአውሮፓውያኑ አሳልፈው በመስጠት የሞትና ባርነቱን መንፈስ ወደ አክሱም ጽዮን ለማምጣት ከኤዶማውያኑ ጋር አስቀድመው ተፈራረሙ፤ በስምምነቱም ጦርነቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ሳይሆን ልክ እንደ ዛሬው በአክሱም/አደዋ እንዲካሄድና የአክሱም ጽዮን ልጆች ጦርነቱን ተከትሎ በሚመጣው ጥፋትና ውድመት ለዘመናት ተቸግረውና ተጎሳቁለው እንዲኖሩ ተደረጉ።

ከአርባ ዓመታት በኋላም ፋሺስቱ ሙሶሊኒ በተመሳሳይ መልክ ወደ አክሱም ጽዮን ተመልሶ ተምቤንና አካባቢዋን በኬሚካል ቦምብ ጨፈጨፋቸው።

ዛሬም ፋሺስቶቹ ግራኝ አብዮት አህመድና ኢሳያስ አፈቆርኪ የኤዶማውያኑን ተልዕኮ ለማስፈጸም በደቡብ ኢትዮጵያ ሳይሆን አሁንም በአክሱም ጽዮን ላይ ጭፍጨፋውን ተያይዞታል። አረመኔው ግራኝ አብዮት አህመድ በትግራይ ሕዝብ ላይ በጣም አደገኛ ኬሚካሎችንና ራዲዮ አክቲቭ ዝናቦችን በኤሚራቶች ድሮኖች አውርዶባቸዋል፤ ኤሚራቶች ከአሰብ ተጣድፈው የወጡት ለዚህ ነው! ገለልተኛ መርማሪዎችንም የማያስገባው ይህ እጅግ በጣም አስከፊ ወንጀል ስላስደነገጠው ነው። በእኔ በኩል ገና ከዓመት በፊት ግራኝ የኑክሌር ወይንም የኬሚካል መሳሪያዎችን ካገኘ ሰሜን ኢትዮጵያን ላይ እንደሚጠቀምባቸው በደንብ ታይቶኝ ነበር። ይህ አውሬ እጅግ በጣም አረመኔ እንደሆነ ገና ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳየሁት ነበር የተገለጸለኝ።

👉 “አለም (ዲያብሎስ) “ማየት ማመን ነው” ይለናል | እግዚአብሔር ደግሞ “ማመን ማየት ነው” ብሎ ያስተምረናል”

ኃይለኛ ጦርነት ላይ ነን!!!

❖ “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።” [ኤፌሶን ፮፡፲፪]

👉 ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም – (ተክለሃይማኖት ነው) ሰበታ የሚገኘው የአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን በእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ወደመ።

👉 ጥር ፲፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም – ስለዚህ ቆሼ አስከፊ ቆሻሻ ሽታ እንዲሁም አካባቢው በመስጊድ ጩኽት ስለመበከሉ፤ ብሎም ዲያብሎስ እንደዚህን በመሳሰሉት መሰናክሎች በኩል ምዕመናኑን እየተዋጋ ከቤተክርስቲያን በማራቅ ከክርስቶስ ለመለየት እነደሚሞከር አወሳን።

👉 መጋቢት ፪ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም – በተለምዶ ቆሼ ሚባለው ስፍራ የተከሰተው አሳዛኝና አስደንጋጭ ዜና በመላው ዓለም መነጋገሪያ ለመሆን በቃ።

በሰበታ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን በእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ስትወድም ጽላቶቹ ግን በተአምር አንዳችም ጉዳት ሳይደርስባቸው ተገኝተዋል

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይግቡ፦ (ቪዲዮዎቹን ሌላ ጊዜ እንደገና አቀርባቸዋለሁ)

❖ ❖ ❖ የሰኞ ሰፈ ሥላሴ ተአምር ❖ ❖ ❖

ይቅርታቸውና ሀብተ ረድኤታቸው ለአገልጋያቸውይደረግለትና የሥላሴ ተአምራታቸው ይህ ነው።

ጦሮዓዳ በሚባል አገር የፋርስ ንጉሥ ጭፍራ የሆነ አንድ ሰው ነበረ ፤ ይህም ሰው ከዕለታት ባንድ ቀን የክርስቲያንን ሀገር ለማጥፋት ሰንጋ ፈረሱን ጭኖ ከቤቱ ወጣ።

በዚህም አገር ውስጥ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ሥዕል ያለበት የተቀደሰ ቦታ ነበር። ከዚያም ንዋያተ ቅድሳቱን ለመመዝበር ወደ አማረውና ወደ ተጌጠው አዳርሽ በገባ ጊዜ የሥሉስ ቅዱስ ሥዕል ካለበት ቦታ ደረሰ።

ይህም ወታደር የሥላሴን ሥዕል በእሳት ሰይፍ ታጥሮ ባየው ጊዜ በዚያ የነበሩትን ሰዎች ወንድሞቼ ሆይ ይህ እንደ ነደ እሳት የሚያንፀባርቅ ሥዕል ምንድን ነው አርኣያው እጅግ አስፈራኝ ወደ እሱ ቀርቤም ሁኔታውን ለመረዳት ተሳነኝ አላቸው።

እነዚያም የክርስቲያን ወገኖች አንተ ወታደር ፈጥነህ በምድር ላይ ወድቀህ ስገድ ይህ ስ ዕል የሥላኤ አርኣያ ገጽ ነውና አሉት። በዚያ ጊዜ ፈጥኖ በጉለበቱ ተንበርክኮ ሰገደ እጁንም ወደ ሰማይ በመዘርጋት እኔ ለጌቶቼ ለሥላሴ ሥዕል እሰግዳለሁ እያለ ማለደ።

ከአረማውያን ሀገር አውጥታችሁ ከክርስቲያኖች አገር አድርሳችሁኛልና ስለዚህም ምስጋና ላቀርብላችሁ እገደዳለሁ አለ። እንዲህም እያለ ሲጸልይ የእግዚአብሔር የጌትነቱ ብርሃን በዚያ ቤት ውስጥ መላ።

በዚህም ጊዜ አንተ የንጉሥ ወታደር ሆይ መንግሥተ ሰማያት ትገባ ዘንድ ሥሉስ ቅዱስ ጠርተውሃል የሚል ቃል ከሰማይ መጣ። ይህንንም ከመስማቱ የእግዚአብሔር መልአክ መጋቤ ብርሃናት ራጉኤል በቅጽበት ወደሱ መጥቶ ወደ ሰማይ አሣረገውና በሥላሴ ፊት አቆመው።

ሥላሴም ከሌሎቹ የንጉሥ ሠራዊት ተመርጠሽ ወደዚህ የመጣሽ ምርጥ ነፍስ ሆይ ወልድ በአባቱ ጌትነትና በመንፈስ ቅዱስ ክብር እስኪመጣ ድረስ በሕያዋን አገር ገብተሽ በዚያ ትቀመጭ ዘንድ ፈቅደንልሻል አሏት። ይህንንም ካሏት በኋላ ወደዚያ አገር አስገቧትና በዚያ ተቀመጠች።

ይቅርታቸውና ሀብተ ረድኤታቸው ከወዳጃቸው ከ .…ጋር ለዘላለሙ ይኑር፤ በዕውነት አሜን።

🔥 አክሱም ጽዮን ገብተው ካህናትን፣ ቀሳውስትና ም ዕመናንን በመጨፍጨፍና ዓብያተ ክርስቲያናቱን በማፈራረስ ላይ ያለው የሰባተኛው ንጉሥ የግራኝ አብዮት አህመድና የ (ሰ)አራዊቱ ዓባላት ነፍሳት ወደ ገሃነም እሳት ይገባሉ።🔥

____________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: