ኦርቶዶክስ ሮማኒያ ስለ አክሱም የጅምላ ጭፍጨፋ | ቤተ ክህትነት ግን ዛሬም ስለ ጽዮን ዝም ብላለች
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 19, 2021
❖❖❖ኦርቶዶክስ ሮማኒያ ስለ ጽዮን ዝም አላለችም❖❖❖
👉 ስለ አክሱም ጽዮን የጅምላ ጭፍጨፋ የሮማኒያ ቴሌቪዥን
❖ ኢትዮጵያዊቷ(ጥቁሯ)ወላዲተ አምላክ በሮማኒያ በጣም ተወዳጅ ናት።
❖ ሮማኒያውያንን ወላዲተ አምላክ ናት ከቱርኮች እና ኮሙኒዝም የባረንት ቀንበር ነፃ ያወጣቻቸው።
❖ ሮማኒያ ብዙውን ጊዜ ‘የእግዚአብሔር እናት የአትክልት ስፍራ’ ትባላለች።
❖ ፹፪/82% ሮማኒያውያን ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ናቸው።
የሠራችላቸውን እጅግ በጣም ከፍተኛ ውለታ ተከትሎ ለኢትዮጵያዊቷ(ጥቁሯ)ወላዲተ አምላክ ከፍተኛ ፍቅር ካላቸው ሕዝቦች መካከል ፖላንድና ሮማኒያ ይገኙበታል።
ስለ ፖላንድ ባለፈው ጊዜ ይህን አውስተን ነበር፦
👉“Poland Condemns Perpetrators of Massacre In Axum Ethiopia as ‘Barbaric’”
👉 የፖላንድ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአክሱም የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ‘አረመኔያዊ’ ሲል አወገዘ፡፡
👉 በፖላንድ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
❖ በአክሱም ጽዮን ብቻ ሺህ የሚሆኑ ምዕመናን በአሰቃቂ ሁኔታ ጨፍጨፈው የውጭ ሃገራት መሪዎችና ሜዲያዎች በየቀኑ አክሱምን ያስታውሷታል የኢትዮጵያ ናቸው የሚባሉት፤
☆ ፖለቲከኞችና ባለሥልጣናት
☆ የሃይማኖት አባቶች
☆ ሜዲያዎች
☆ ከትግራይ ውጭ ያሉ ዜጎች
☆ በውጭ ያሉና ትግሬ ያልሆኑ ሐሰተኛ ኢትዮጵያውያን ግን በህብረት ጸጥ፣ ጭጭ ብለዋል፤ ጽንፈኛ ድርጊቱን ይደግፉታልን?
የሚገርም ነው፤ በትናንትናው የአቡነ አረጋዊ ዕለት ጸሎት የማደርስበት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንዲት አረጋዊት ፖላንዳዊት ወደኔ ቀርባ በመምጣት የቦታ አድራሻ ከጠየቀችኝ በኋላ ለአንድ ሰዓት ያህል ሳዋራት ነበር። ፖላንዶች ለጽዮን እመቤታችን ከፍተኛ ፍቅር አላቸው። ሆላንድ እና ፖላንድ እንዳይምታታብንና አምና ላይ ይህን ቪዲዮና ጽሑፍ አቅርቤ ነበር፦
👉 “ሆላንድ | የጥቁሯን “ኢትዮጵያዊት” ማርያም ቅዱስ ሥዕልን በጥቁሮች መፈክር አበላሹት”
እ.አ.አ በ1656 ዓ.ም በፖላንድ ላይ ተቃጥቶ የነበረውን የስዊድኖች የጥቃት ወረራ በጥቁሯ ማርያም እርዳታ ሲከሽፍ የፖላንድ ንጉሥ ካዚሚሬስ ጥቁሯን እመቤታችንን የፖላንድ ንግሥት እንድትሆን ወሰነ። ብልሕ ንጉሥ!
እ.አ.አ በ1944 ዓ.ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ክፉኛ የደቀቁት (1/5ኛው ሕዝቧ፤ 6ሚሊየን ፕላንዳውያን አልቀዋል ) ፖላንዳውያኑ የጥቁሯን/ኢትዮጵያውያን እመቤታችንን ስዕል ተሸክመው እስከ ኔዘርላንድስ/ሆላንድ ድርሰ ዘልቀው በመግባት ቪዲዮው ላይ የምትታየውን የብሬዳ ከተማን ነፃ ለማውጣት በቅተዋል። ድንቅ ተዓምር!
ጥቁሯ ማርያም (Black Madonna of Czestochowa) እ.አ.አ በ1944 ዓ.ም የኔዘርላንድሷን(ሆላንድ) ከተማ ብሬዳን ከናዚዎች ነፃ ላወጧት የፖላንድ ወታደሮች በ1954 ዓ.ም የተሠራ መታሰቢያ ላይ ሰሞኑን በመላው ዓለም በመካሄድ ካለው ከፀረ-ዘረኝነት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ያልታወቁ ሰዎች “BLM“ ( Black Lives Matter – BLM “የጥቁርም ሕይወት ይገባዋል”) በሚል ትልቅ ጽሑፍ ለማበላሸት ደፍረዋል። ትልቅ ቅሌት!
ለእናታችን ትልቅ ፍቅር ያላቸው ፖላንዳውያን የሚያሳዩት የእመቤታችን ቅዱስ ሥዕል ነጭ ሳይሆን እንዲህ ይመስላል። የእናት እና ልጇ ውበት ልብን ያሞቃል!
ለመሆኑ የጥቁሯ ማርያም ስዕልን የሚቃወም የጥቁሮች እንቅስቃሴ አለ እንዴ? ይህን ጽንፈኛ ተግባር ሊፈጸም የሚችለውስ በማን ይሆን? በኮሙኒስቶች? በፌሚኒስቶች? በግብረ–ሰዶማውያን? በመሀመዳውያን?። ሁሉም የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ናቸውን አያደርጉትም አይባሉም።
እንቅስቃሴው ቀስ በቀስ በዘረኞች፣ በኮሙኒስቶች፣ በግብረ-ሰዶማውያን እና በአህዛብ እይተጠለፈ ነው። የጥቁር ሕዝቦች ለነፃነትና ህይወት የሚያደርጉትን ትግል ሁሌ የሚጠልፉት እነዚህ ቡድኖች ናቸው። ለዚህ ነው ጥቁሮች ተገቢውን የነፃነት ዒላማ ከመምታት መንገድ ላይ የሚቀሩት። በሃገራችንም ተመሳሳይ ክስተት ይታያል፤ የኢትዮጵያ ብሔርተኛውን አጀንዳ ዘውገኞቹ ኦሮሞዎችና አህዛብ በሁሉም መስክ ጠልፈው እየወሰዱት ነው።
አሁን አጋጣሚውን በመጠቀም ግራኞች፣ ኮሙኒስቶች፣ ፌሚንስቶች እና ሰዶማውያን ከመሀመድ አርበኞች ጋር በማበር በዓብያተ ክርስቲያናት ላይ በመላው አውሮፓ እና አሜሪካ ጥቃት በመፈጸም ላይ ናቸው። አጋንንት የተለቀቁበት ዘመን ላይ ነንና ግድ የለም እራሳቸውን እንዲህ ያጋልጡ፣ ይታዩን፤ ጊዚያቸው በጣም አጭር ነው!
ለማንኛውም እንደ ፖላንድ፣ ሩሲያ፣ ሩማኒያ፣ ፈረንሳይ፣ ስፔይን ወዘተ ላሉ አውሮፓውያን ሃገራት እኛ ኢትዮጵያውያን በድንቁርናችን ነጭ የቆዳ ቀለም እና ሰማያዊ ዓይኖች እያለበስን ያመጣናት ጥቁሯ/ ኢትዮጵያዊቷ ቅድስት ማርያም በታሪካቸው በጣም ብዙ የሆኑ ተዓምራትንና ድሎችን አሳይታቸዋለች።
በተለይ በምስራቅ አውሮፓ በኮሙኒዝም እና ኦቶማን ቱርክ ዘመን አስከፊ ልምዱ ላላቸው ለምስራቅ አውሮፓውያን በጥቁሯ/ኢትዮጵያዊቷ ቅድስት ማርያም ጉዳይ ምንም ድርድር የለም። በዘመነ ኮሮና በእነዚህ አገራት ከተሞች ጎዳናዎች ላይ በእጣን ታጅበው እንዲወጡ የተደረጉት የእናታችን የጥቁሯ ማርያም ስዕላት ናቸው። (በሌላ ቪዲዮ አቀርበዋለሁ)
ዝነኛው የፖላንድ ጥቁሯ ማርያም (Black Madonna of Czestochowa) ቅዱስ ሥዕል

ሥዕል = ጽሑፍ
አስገራሚ የሆነው የቼስቶኮቫ ጥቁር ቅድስት ድንግል ማርያም አይከን/ሥዕል/ጽሑፍ ቅዱስ ሐዋርያው እና ወንጌላዊ ሉቃስ ከሣላቸው/ከጻፋቸው ሰባ ቅዱሳት ሥዕላት/ጽሑፎች መካከል አንዱ እንደሆነ ይታመናል።
ሮማውያን በ 66 ዓ.ም. ከተማዋን ድል ባደረጉበት ጊዜ ምስሉ ከኢየሩሳሌም ተወስዶ ነበር። እናም ፔላ አቅራቢያ ባለ ዋሻ ውስጥ ተደብቆ ነበር። ስዕሉ ለቅድስት ሔለን (እ.ኤ.አ. ግንቦት 21/ 326 ዓ.ም) ቅድስት አገር ስትጎበኝ ተሰጣት፤ ከዚያም ቅድስት ሔለን ወደ ቁስጥንጥንያ አመጣችው።
ይህ ተዓምረኛ ሥዕል ከስምንተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በመላው አውሮፓ በኦሮቶዶክሳውያን እና ካቶሊኮች ዘንድ ብዙ ተዓምራትን ካሳየ በኋላ ከአስራ አራተኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ያስና ጎራ/ ቺስታኮቫ በተባለው የፖላንድ አውራጃ ይገኛል። ድንቅ ተዓምራት የሚታዩበት ይህ ቦታ በብዙ ጎብኞዎች ይዘወተራል። አረመኔው አዶልፍ ሂትለር ያስና ጎራን/ ቺስታኮቫን ለጎብኝዎች ዝግ እንዲሆን አድርጎ ነበር።
እኛስ ይህን እያየን እመቤታችንን አላግባብ ፈረንጅ ስናደርጋት ሊያሳስበንና ሊያሳፍረን አይገባምን?
ሮማውያኑ “እየሱሳውያን”፤ የጌታችን እና ቅዱሳኑ መልአክቱ ስዕላትንና ኃውልቶችን በነጮች ምሳሌ እንደሚስሏቸውና እንደሚሠሯቸው “ጥቁሯን” / ኢትዮጵያዊቷን” ማርያምንም በተንኮል ነጭ አድርገው በመሳል ወደ ኢትዮጵያ መላካቸውን ስንቶቻችን ነን የምናውቀው?
አሁን ኢትዮጵያውያን ወደ ጥንታውያኑ እና እውነተኞቹ የእመቤታችን ስዕላት መመለስ ይኖርብናል። ቤተ ክሕነትና ማሕበራቱ እንዲሁም ግለሰቦች ለጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት መስጠት አለባቸው። በዚህ ላይ ቁጥጥር የሚያደርግ አካል መኖር አለበት። ይህ በቸልታ የሚታለፍ ቀላል ነገር እንዳይመስለን። ይህን አስመልክቶ ኢትዮጵያውያን ልሂቃን ብዙ ሥራዎችን መስራት ይጠበቅብናል።
___________________________
Leave a Reply