Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

የአማራ ቃኤላውያን መቅበዝበዝ | ትናንትና ሓውዜን ዛሬ ማይካድራ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 16, 2021

የማይካድራ ጭፍጨፋ በማይካድራ ነዋሪዎች፤ እርቅ የተፈለገው ለምን ይሆን?

“ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ ተዋሕዶ ነኝ”የሚለው አማራ ቃኤል ማህተብ ያሠረውን አቤል ወንድሙን ለመግደል ከአህዛብ የዋቄዮ-አላህ ልጆች እንዲሁም ከሶማሌዎችና አረቦች ጎን ተሰልፎ “ያዘው! በለው! ግደለው!” እያለ ዘመተ። እስኪ እናስበው አንድ “ክርስቲያን ነኝ” የሚል ሰው ከክርስቶስ ተቃዋሚዎች ጋር አብሮ ክርስቲያን ወንድሙን ሲገድለው። ዋይ!ዋይ!ዋይ! ደግሞ እኮ ይህ አልበቃውም “አመልከዋለሁ” በሚለው እግዚአብሔር አምላክ ፊት ቆሞ በተእቢት፤ “ሌላውን አላውቅም! እኔ ነኝ የተገደልኩት፤ ወንድሜ አቤል ነው እኔን የገደለኝ” ብሎ በሐሰት በመመሰከር በአቤል ልጆች ላይ ግድያውንና ጭፍጨፋውን ቀጥለ። በጎን በኩል ደግሞ ሰላምና እርቅ እያለ አቤልን ወደገደለበት ቤት ኤልዛቤላውያኑን ለሽንገላ ላካቸው። ገና ለንስሐ ሳይበቃ።

የኢትዮ360 ግብዝ ‘ተንታኞች’ የአጋንንትን ቋንቋ ተጠቅመው እንዲህ እያሉ ሲፎርክቱ ሰምተናቸዋል፤ “ከጁናታው(ትግሬ) ጋር ለሰላምና እርቅ ከምንሰለፍ ከሰይጣን ጋርም ቢሆን አብረን እነርሱን መዋጋቱን እንመርጣለን!”። ቪዲዮው ላይ የሚሰሙትና የሚታዩት ወጣቶች ከእነዚህ ግብዞች በተሻለ የፈሪሃ እግዚአብሔር ማንነት እንዳላቸው በግልጽ ይታያሉ።

እንግዲህ ይህን ሁሉ ድፍረት፣ ትዕቢት፣ ትምክህትና ጥላቻ” እያሳዩ ያሉ በእግዚአብሔር አምላክ ፊት ነው።

👉 ሐሰተኛ ሰላም በውሸት የሚገኝ ምናባዊ ሰላም ነው፡፡

.ሰላም አለመኖሩ እየታወቀ “ሰላም አለ” እየተባለ የሚነገርለት ነው፡፡

.ሐሰተኛነት ባሪያ ያደረጋቸው ሰዎች ሰላም በሌለበት መካከል “ሰላም አለ” እያሉ ሕዝቡን ያታልላሉ፡፡

.ይህ እነርሱ አለ የሚሉት ሰላም የውሸት ነው፡፡

እነዚህ ሰዎችን ነቢዩ ኤርምያስ “ሰላም ሳይሆን ሰላም ሰላም ይላሉ” [ኤር ፮÷፲፬] በማለት ይገልጻል፡፡

.እንዲህ አይነቱ ሰላም ምናባዊ ነው፤ የሚታይ፣ የሚዳሰስ፣ የሚጨበጥ አይደለም፡፡

መዳብን ወርቅ በስሱ ቀብተው ያብረቀርቁታል በወርቅ ዋጋም ይሸጡታል፤ ገዥዎች ለጊዜው ወርቅ የገዙ ይመስላቸዋል፡፡

የተወሰነ ጊዜ ከተጠቀሙበት በኋላ ማንነቱን ይገልጥላቸዋል፡፡

የወርቁና የመዳቡ ጓደኝነት ጊዜያዊ ነው፡፡

የዚያን ጊዜ ወርቅ ሳይሆን መዳብ እንደገዙ ይረዳሉ፤ እጅግም ያዝናሉ ይተክማል፡፡

ይህ ውሸተኛ ሰላም እንዲህ ያለ ነው፡፡

ለጊዜው ሰላም ይመስለናል እንጨብጠዋለን ከጨበጥነው በኋላ ግን መርዝ ያለበት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

.ሰው ኃጢአትን የሚሠራው ሰላም አገኝበት መስሎት ነው፡፡

በኋላ ግን ኅሊናው መሸከም የማይችለውን ዕዳ ያሸክመውና ሰላሙን ያጣል፡፡

እንቁላል ላይ ላዩን ሲያዩት ጠንካራ ወድቆ የማይሰበር ይመስላል፡፡

ነገር ግን ያ ጠንካራ የመሰለው ቅርፊት በውስጡ ፈሳሽ የያዘ ነው፡፡

ውሸተኛ ሰላም እንዲህ አይነት ነው፡፡

.ንጉሥ አክዓብና ኤልዛቤል የናቡቴን ርስት ለመውረስ ናቡቴን መግደል በቂ ሰላም የሚፈጥርላቸው መስሏቸው ነበር፡፡

ነገር ግን ናቡቴን በመግደላቸው ሰላማቸውን አጡ፡፡[፩ኛ ነገ፳÷፩፡፲፯]

ይህ አይነቱ ሰላም በማር የተለወሰ መርዝ ነው፡፡

ስትበላው ማር ስለሆነ ሊጣፍጥህ ቢችልም መርዝ ስላለበት ደግሞ በስተጀርባው ሞት ያመጣል፡፡

ከሰዎች እና ከዓለም የምታገኘው ሰላም እንዲህ ያለ ሰላም ነው፡፡

.ቃየን መልከ መልካሟን ሉድ ለማግባትና በሰላም ለመኖር ነበር ወንድሙ አቤልን የገደለው፡፡

ነገር ግን በፊት ያሰበውን ሰላም ማግኘት አልቻለም፡፡ በአንጻሩ በምድር ላይ ኮብላይና ተቅበዝባዥ ሆነ፡፡

.ሰው የሰውን ልጅ ሲገድል ማንም ሳያውቅበት በሰላም ለመኖር አስቦ ነው፡፡

ነገር ግን ከእግዚአብሔር የሚሠወር ነገር የለምና ያንን ኃጢአት መፈጸሙ ታውቆ ወደ ወኅኒ ቤት ሲወርድ ሰላሙ ይደፈርሳል፡፡

ያፈሰሰው ደም ኅሊናውን ያስጨንቀዋል፤ በእግዚአብሔር ፊትም ይከስሰዋል፡፡ በፊት ያሰበውን ሰላም ሳይሆን ጭንቀትን ይለብሳል፡፡

❖[ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፬፥፰፡፲፩]

ቃየልም ወንድሙን አቤልን። ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየል በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፥ ገደለውም። እግዚአብሔርም ቃየልን አለው። ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? እርሱም አለ። አላውቅም፤ የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን? አለውም። ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ።

❖[፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፬፥፳]

ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?

❖ [ወደ ዕብራውያን ምዕራፍ ፲፫፥፩፡፫]“

የወንድማማች መዋደድ ይኑር። እንግዶችን መቀበል አትርሱ፤ በዚህ አንዳንዶች ሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልናከእነርሱ ጋር እንደ ታሰረ ሆናችሁ እስሮችን አስቡ፥ የተጨነቁትንም ራሳችሁ ደግሞ በሥጋ እንዳለ ሆናችሁ አስቡ።”


___________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: