መከላከያ ‘ሰራዊቱ’ ኢትዮጵያዊ ከሆነ አብይ አህመድን እና ብርሃኑ ጁላን ባፋጣኝ ማሰር አለበት
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 3, 2021
ጥሩ መልዕክት ነው፤ ነገር ግን ትንሽ የዘገየ መሰለኝ። ሠራዊቱ መፈንቅለ-መንግስት እንዲያካሂድና የሽግግር መንግስት እንዲያቋቁም ከዓመት በፊት ተመሳሳይ ጥሪ ስናደርግ ነበር፤ እባቡ አብዮት አህመድ ግን ቀደመን፤ ልክ ትናንትና በምያንማር በኖቤል ሰላም ተሸላሚዋ ጠቅላይ ሚንስትር ላይ የተደረገው የሰራዊቱ መፈንቅለ መንግስት በእርሱ ላይ እንዳይደረግ ሰራዊት ተብዬውን ወደ ትግራይ ልኮ ሕዝቡንም እራሱንም ወታደሮቹንም ክፉኛ አስጨፈጨፋቸው።
አሁን ሁሉም ነገር የዘገየ መሰለኝ፤ በትግራይ ሕዝብ ላይ የተሰራው ግፍና ወንጀል ለብዙ ሺህ ዓመታት የማይረሳ ነው። ሃምሳ ሺህ ንፁሐን ተገድለዋል ተብሎ በይፋ በሚነገርባት ሃገር በሃዘንና ለቅሶ ፋንታ ጎንደር ላይ የኤርትራን ባንዲራ ይዘው ጥምቀትን በጭፈራ ሲያከብሩ፣ ጅማ ላይ ጨፍጫፊውን ግራኝን ለመደገፍ ስልፍ ሲወጡ በምን ተዓምር ነው ከእነዚህ አረመኔ ሳዲስቶች ጋር እርቅ ሊኖር የሚችለው? በፍጹም! መላው(ሰ)አራዊት በጦር ወንጀለኝነት የሚከሰስበት ቀን ሩቅ አይደለም።
________________________________
Leave a Reply