Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for January 15th, 2021

የጦር ወንጀል | The European Union Says ‘Possible War Crimes’ In Ethiopia’s Tigray

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 15, 2021

The European Union’s Joseph Borrell Says ‘Possible War Crimes’ In Ethiopia’s Tigray

የአውሮፓው ህብረት ዮሴፍ ቦረል በኢትዮጵያ ትግራይ ውስጥ “ሊሆኑ የሚችሉ የጦር ወንጀሎች ተፈጽመዋል” ብለዋል

ከሁለት ወራት በፊት የተባበሩት መንግስታት ተመሳሳይ መገለጫ አውጥቶ ነበር፤ ጭፍጨፋውና ስደቱ ግን እየከፋ እየከፋ ነው የመጣው። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ለአምስት አሜሪካውያን ሞት ተጠያቂ ተደርገው አንድም ቀን እንኳን ሥልጣን ላይ እንዳይቆዩና ከስልጣንም እንዲወርዱ ኮንግረሱ በዚህ ሳምንት ድምጹን ሰጠ፥ በኢትዮጵያ ግን አረመኔው ግራኝ አህመድ አሊ በሦስት ዓመታት ብቻ ከመቶ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን አስጨፍጭፎና ስድስት ሚሊየን ትግራዋያን በረሃብ ሊቀጣ በመወሰኑ የኖቤል ሰላም ሽልማት ተበረከተለት፤ ከንቱው የአገራችንም ሰው “በለው! ግደለው!” እያለ ድጋፉን ሰጠው። በጣም ደም የሚያፈላ አሳዛኝ ሁኔታ ነው።

👉 EU suspends aid to Ethiopia over Tigray conflict

👉 የአውሮፓ ሕብረት በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የሚሰጠውን የበጀት ድጋፍ አገደ

The European Union says it is getting consistent reports of ethnic-targeted killings and possible war crimes in Ethiopia’s northern region of Tigray.

The defence forces entered Tigray early in November to oust the region’s ruling party after its troops had captured federal military bases.

The government declared victory by the end of that month, but the EU says the situation remains dire.

The conflict threatens the stability of the entire region, the European Union says.

“The situation on the ground goes well beyond a purely internal ‘law and order’ operation,” EU foreign affairs chief Josep Borrell said in a statement.

“We receive consistent reports of ethnic-targeted violence, killings, massive looting, rapes, forceful returns of refugees [to Eritrea] and possible war crimes,” he said.

With more than two million forced to flee their homes, people in Tigray were in desperate need of aid but access to the region remains limited, he added.

How does the crisis involve Ethiopia’s neighbours?

Mr Borrell said that Eritrean troops were involved in military operations in Tigray, something both the Ethiopian and Eritrean governments deny.

They are accused of forcibly taking back Eritrean refugees who lived in the UN-run camps in Tigray, before the conflict there broke out.

Nearly 100,000 Eritreans lived in four camps in Tigray after fleeing political persecution and military conscription in the one-party state.

His comments come a day after UN High Commissioner for Refugees Filippo Grandi said the UNHCR had not been given access to the Shimelba and Hitsats refugee camps since early November.

“Reports of additional military incursions over the last 10 days are consistent with open source satellite imagery showing new fires burning and other fresh signs of destruction at the two camps,” he said.

ምንጭ/Source

_________________________

Posted in Ethiopia, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጽላተ ሙሴን ከአክሱም ወደ አዲስ አበባ? | ፒያሳ መዘጋጃ ቤት አካባቢ ፮ የቦንብ ፍንዳታዎች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 15, 2021

ከአራት እስከ ስድስት ፍርንዳታዎችና የተኩስ ልውውጦች ተሰምተዋል።

በወንድሞቹ ላይ ጦርነት ያወጀ ገና የከፋ ሽብር እና እሳት ነው የሚጠብቀው፤

ጽላተ ሙሴን ለመስረቅ በተነሳው ግብግብ በአክሱም ጽዮን ከሰባት መቶ በላይ ምዕመናን ተገድለው ዝም ያለ ሕዝብ ክርስቲያንም ኢትዮጵያዊም ሰብዓዊም ሊሆን አይችልምና መጠረግ አለበት። ይህ እነ ግራኝ የሚያካሂዱት የሽብርና የሙቀት መለኪያ ተግባር ነው።

ሰባተኛው እብድ ንጉሥ ግራኝ አህመድ አሊ የሰሜን ሰዎችን እርስበርስ አባልቶ ካደቀቀቃቸውና ካዳካማቸው በኋላ ለሰላሳ ሦስተኛ ዙር የሰለጠነውን የዋቂዮአላህ ቄሮ ሠራዊት መጀመሪያ ወደ ቤኒሻንጉል፣ ቀጥሎ ወደ አማራ ክልል ከዚያም ወደ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ ወደ መቀሌና አስመራ ጎራ የማለት ዕቅድ ነው ያለው፤ አባገዳ የተባሉትን የአቴቴ መተተኞች ወደ መቀሌ የላካቸው ለዚህ ዕቅዱ ነው።

ወራሪዎቹ ጋሎች ከአምስት መቶ ዓመታት መስፋፋት የበቁት እነ ግራኝ አህመድ ቀዳማዊ ከቱርክ፣ ግብጽና ሱዳን ጋር ሆነው ሰሜን ኢትዮጵያውያን ካዳከሟቸው በኋላ ነበር። ዛሬም ተመሳሳይ ነገር ነው እያየን ያለነው። ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ትግሬን ከኤርትራ ትግሬ እና ከአማራው ጋር እያናከሰ በማዳከም ላይ ይገኛል፤ ወደ ትግራይ የላከው ሠራዊት በኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ውስጥ የቀረውና እኛ አምና ላይ “መፈንቅለ መንግስት ማድረግ አለበት” ስንል የነበረው በብዛት አማራዎች የሚሳተፉበትን ሠራዊትና ሶማሌዎችን ነው። ምን ችገረው፤ የእርሱ ጋሎች እስካልተነኩ ድረስ እዚያ ቢያልቁለት ምኞቹትና ደስታው ነው። ግራኝ ጎን ለጎን፤ “ወላሂ! ወላሂ! ግብጽን አልጎዳም!” ብሎ ለአል-ሲሲ ቃል በገባው መሠረት ከግብጽ እና ሱዳን ጋር ሆኖ አማራና ቤኒሻንጉል የተባሉትን ክልሎች እንዲወረሩ በማድረግ ላይ ነው። ከታች በደቡብ እና በምስራቅ ግንባር በኬኒያ አስፈላጊውን ወታደራዊ ዝግጅት በማድረግ ላይ ያሉትን የኦነግ ሠራዊቶች በሶማሊያ እና ደቡብ ክልሎች ላይ እንዲዛምቱ አዝዟቸዋል፤ በሰሜን እና በምዕራብ ግንባር ደግሞ ለሰላሳ ሶስተኛ ዙር የሰለጠነውን የዋቄዮ-አላህ ሠራዊት ቀስበቀስ ወደ ቤኒ ሻንጉል እና አማራ ክልሎች በማስገባት ላይ ይገኛል። አዎ! ይህ ሠራዊት ወደ ትግራይ አልተላከም፤ እዚያ ሄዶ ማለቅ የለበትም፤ ለጊዜው የአረቦች ፔትሮ ዶላር እየተከፈለው ያለው የኢሳያስ አፈቆርኪ ቅጥረኛ ሠራዊት እራሱ እስኪዳከም ድረስ እዚያ ስራውን እንዲሠራለት አስቀድሞ ተፈራርሟል።

የሶማሌው አል-ሸባብ ከፊል የሶማሌ ክልል በመቆጣጠር ላይ እንደሆነ ተነግሯል። እንግዲህ ለአዲስ አበባ ሽብር የተመደበው አል-ሸባብ ነው፤ በአዲስ አበባ ደግሞ ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ይህን አነቺ ወቅት በመጠባበቅ ላይ ያሉ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሶማሌዎች አሉ። እኔ እራሴ በቦሌ ሚካኤል የታዘብኩት ይህን ነው።

እራሳቸውን ለማጥፋት በአንገታቸው ላይ እባብ በመጠምጠም ላይ ያሉት የሰሜን ኢትዮጵያውያን ሞኝነት፣ ድንቁርና፣ ከንቱነትና አልማር-ባይነት ያናድደኛል!!!

_________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የእኛ የሆነውን የሚነጥቀንን ዲያቢሎስ በሰይፈ ሥላሴ ጸሎት ልናርቀው እና ልንርቀው ይገባል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 15, 2021

❖❖❖ ስብሐት ለአብ ፡ ስብሐት ለወልድ ፡ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ፤ አሜን! () ❖❖❖

ሰይፈ ሥላሴ በተለይ በረቂቅ የሚዋጉንን አጋንንት በረቂቅ የጸሎቱ ሰይፍ ስለሚቆርጥልን አጋንንት ወደ እኛ እንዳይቀርቡ ያደርግልናል፡፡ ሰይፈ ሥላሴን ዘወትር የሚጸልየው ሰው አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ በረድኤት፣በመለኮታዊ ጥበቃነት አይለዩትም፡፡ ከቤቱ የሥላሴ በረከት አይታጣም፡፡ ጠላት አይበረታበትም፡፡ አጥር አፍርሶ፣ድንበር ጥሶ የሚመጣን ግልጽም ይሁን ስውር ጠላትን ያርቃል፣ይሰውራል፡፡

በተለይ ዓይነ ጥላ፣ መተት ድግም፣ዛር ወዘተ ያለበት ሰው ሰይፈ ሥላሴን ያለመሰልቸት፣ያለ መታከት አዘውትሮ ቢጸልየው በላዩ ላያ ያደረበት መንፈስ እድሜው እያጠረ፣እንደ ጢስ እየበነነ እንደ ጉም እየተበተነ ይሄዳል፡፡ አጋንንትን ከሚያዳክሙት፣አጋንንታዊ ኃይሉን ከሚነሱት ጸሎቶች ውስጥ አንዱ ሰይፈ ሥላሴ ነው፡፡ የሰይፈ ሥላሴ ጸሎት በሥጋም በነፍስም፣ አጋንንት ውጊያም ጥቅም ኃይለኛ እና ድንቅ በመሆኑ ጸሎቱን ማዘውተር ይገባናል፡፡

ሰይፈ ሥላሴን በመጸለይ ሁለት ዋና ጥቅም እናገኛለን፡፡ አንደኛው አጋዕዝተ ሥላሴን እናመሰግናለን፡፡ ሁለተኛ በጸሎት ኃይል እራሳችን እንጠበቅበታለን፡፡ ስለዚህ ሰይፈ ሥላሴን አዘውትረን መጸለይ አንዱ ውዴታችን ሳይሆን ግዴታችን ሊሆን ይገባል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ ”ዲያቢሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቁጣ ወደ እናንተ ወርዷልና” ብሎ ስለነገረን ወደ ሕይወታችን በቅናት ቁጣ እየመጣ የሚያመሰቃቅለንን፣ ግራ የሚያጋባንን፣ የሚያባክነንን፣ የእኛ የሆነውን የሚነጥቀንን ዲያቢሎስ በሰይፈ ሥላሴ ጸሎት ልናርቀው እና ልንርቀው ይገባል፡፡ [ራዕ. ፲፪÷፲፪]

ሰሜን ኢትዮጵያውያን በተለይ የትግራይ ኢትዮጵያውያን ዲያብሎስ የእናንተ የሆነውን ኢትዮጵያዊነትን፣ ተዋሕዶ ክርስትናን፣ የጽዮንን ሰንደቅን፣ ግዕዝ ቋንቋን ብሎም ድንግል ነፍሳችሁን ሊነጥቃቸው ዳርዳር በማለት ላይ ነውና ዋ! በጣም ተጠንቀቁ! እንጠንቀቅ!

❖❖❖ የሥላሴ ረድኤት በረከታቸው አይለየን፤ አሜን! () ❖❖❖

___________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: