Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for January 4th, 2021

በትግሬዎች ላይ ጭፍጨፋ በተካሄደባቸው ሁመራና ዳንሻ ያሉ ነዋሪዎች | ወያኔ ማረን!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 4, 2021

እንግዲህ ወያኔን የምንቃወምባቸው ብዙ መስፈርቶች ቢኖሩም ቅሉ እንደ አዲስ አበባ፣ ባሕርዳር፣ ናዝሬት፣ ጂማ፣ ጋምቤላና በሌሎች በተቀሩት የኢትዮጵያ ከተሞችና ቦታዎች ትግሬዎች በረከቱን በማምጣቸው ኢትዮጵያ በኤኮኖሚው፣ በጤናው፣ በትምህርቱ፣ በሰላም ጥበቃው መስኮች የማይካዱና በቀደሙት አገዛዞች በሃገራችን ያልታዩ ስኬቶችን አሳይታለች። ለብዙ ዓመታት በተከታታይ እስከ 15 % የኢኮኖም እድገት ይታይ ነበር፤ ያውም የሕዝባችን ቁጥር አንድ መቶ ሚሌይን ደርሶ። ለዚህ ስኬት አንዱ ምሳሌ ሁመራ እንደሆነ ቪዲዮው ላይ የቀረቡት ወገኖቻችን መስክረዋል። ይህ ስኬት ነው በተለይ የዲያስፐራውን አማራ ልሂቃን ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ሲያንገበግባቸው የነበረው፤ “እንዴት ትግሬዎቹ ይብለጡን?” በሚል የጨቅሎች ቅናታዊ ቁጭት! የሚቀርቡን ፈረንጆች እንኳን ይህን ሐቅ በደንብ ታዝበውታል። ኦሮሞዎችም ኢትዮጵያኛና የአፍሪቃ ኩራት የሆነውን የግዕዝ ፊደል ከበታችነንት ስሜት የተነሳ አንቀበልም ብለው የላቲኑን ደካማ ፊደል ወስደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ “እንግሊዝኛ” ይሁን በማለት ላይ ናቸው። ዛሬ ኦሮሞዎቹ በሚገዟት የጠፋችው ኢትዮጵያ የሰው ሕይወት እንደ ቁንጫ መቆጠሩ ብቻ ሳይሆን ኤኮኖሚውም በ -15% አሽቆልቁሎ በመውደቅ ላይ ይገኛል። ሁሉም ነገር “ምን ልስጥ? ምን ላካፈል?” ሳይሆን “አምጣ ሁሉም የኔ ነው!” በሚለው የጥፋት መንገድ ወደ ኋላ እየሄደ ነው። ልክ ኦሮሞዎቹ “ኬኛ ብቻ” እያሉ በወረሩት ግዛት ኢትዮጵያውያንን እያሰቃዩ እንደሚያሳድዷቸውና እንደሚገድሏቸው፤ በማይካድራ፣ ዳንሻ እና ሁመራም ጋላማራዎቹ “ኬኛ ብቻ” ብለው ትግሬ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሱዳን እንዲሰደዱ፣ የቀሩትም በጅምላ ተጨፍጭፈዋል። ይህ እኮ በምድርም በሰማይም ከባድ ዋጋ ያስከፍላል፤ ወገን ይህን እንዴት መገንዘብ ተሳነው? በጣም አሳዛኝ የሆነ ዘመን ነው!

______________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

The Nobel Prize Allowed Evil A. Ahmed to Borrow The Eritrean Army | What a Tragedy!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 4, 2021

ዶ / ር ኢሲያስ ይርጋው፦ “ለአብይ አህመድ የኖቤል ሰላም ሽልማት ያስገኘለት “የሰላም ተግባር” የኤርትራን ወታደሮች ፣ የኤርትራን ጦር በትግራይ ላይ እንዲያዘምት መፍቀዱ በጣም አሳዛኝ ነው

ዶ/ር ኢሳያስ በደንብ ተናግረዋል፤ ብዙ ጠቃሚ መልዕክቶችን ያዘለ ግሩም ቃለ መጠይቅ ! የጠያቂው ዶ/ር ትህትና፣ ተቆርቋሪነትና አክብሮት የተሞላበት አቀራረብም ሊመሰገን ይገባዋል፤ አንዳንድ በጎ ቱርኮችም አሉ። የኖቤል የሰላም ሽልማት አሁን የ ሃፍረት ምልክት ነው ፥ ለዘር ማጥፋት ፈቃድ ነው ስንል ያለምክኒያት አልነበረም።

Dr. Isias Irgau: „It’s tragic that the PEACE PACT that earned Abiy Ahmed The Nobel Peace Prize allowed him to borrow Eritrean soldiers, the Eritrean army to conduct this war against Tigray„

Well said, Doc! We’ve been saying all the time that The Nobel Peace Prize is now a mark of shame – a license for genocide.

👉 አብይ የኖቤል የሰላም ሽልማትን እንዲያገኝ ያስቻለውን ጉዳይ ተቃርኖ በመላው የትግራይ ክልል ውስጥ ጦርነት ለማካሄድና በ ፮/ 6 ሚሊዮን ሰዎች ላይ ጦርነት መክፈቱ ለማሰብ እንኳን በጣም ይረብሻል።

For Abiy to have won The Nobel Prize and Wage a War on 6 Million People is Appalling to Think About

👉 Noble Peace Prize = License for Genocide

👉 የኖቤል የሰላም ሽልማት = ለዘር ማጥፋት ወንጀል ፈቃድ

__________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ታቦተ ጽዮን ያለባትን ከተማ ነክተን ጠላት ሱዳን መጣብን ፥ ታዲያ ዛሬ የወልቃይት መሬት-አስመላሽ የት ገባ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 4, 2021

ወንድሞቻችን ላይ ሲሆንና ወገንህን ለማጥቃት ምላስህ ንግግርህ ረጅም፣ እጅህ ረጅም፣ እግርህ ረጅም! እስኪ አሁን በትግራይ ላይ ያሳየኸውን ወኔህን በሱዳን ላይ አሳየን! አዎ! ለወገኖቻችን፣ ለወንድሞቻችን አልሆንም፤ ለዛም ነው ጠላት የደፈረን!

ደርግ የአፄ ኃይለ ሥላሴን ጄነራሎች፣ መኳንንትና ወታደሮችን ጨፈጨፈ ፥ ለአይጧ ሶማሊያ ወረራ ተጋለጥን፤ ዛሬ ደግሞ ግራኝ አህመድ ዳግማዊና ደርግ 2.0 በአንድ ላይ ሆነው የወያኔን ጄነራሎችና ሠራተኞች ሁሉ ከስልጣን አባርረውና በውጭ ሠራዊታት እየተደገፉ የትግራይን ሰራዊትን ሲያዳክም፤ የተረፉትን ሃሞት ያላቸውን ትግሬ ኢትዮጵያውያንን ሲያርቅና ሲያግልል፤ እባቦቹ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሱዳን፣ ግብጽ፣ ቀጥሎም ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ጂቡቲ እና ኬኒያ ከእነ አልሸባብ፣ አይሲስ እና አልቀይዳ ያለምንም ተቃውሞ ሰተት ብለው ለመግባት በመዘጋጀት ላይ ናቸው።

በሱዳን መተት የተያዘው ወገናችን ግን ይህን እያየ እንኳን በግራኝ አብዮት አህመድ ላይ ለመዝመት ከመነሳሳት ተቆጥቧል። ምክኒያቱ? ለኑሮው ሁሉ ትርጉም የሚሰጠው በትግሬ ወንድሞቹ ላይ ያለው ጥላቻ ብቻ ስለሆነ ነው። ሰነፍ ሁላ!

አሁን ተገላልጦ የወጣው ጥላቻ በህወሃት ላይ ብቻ እንዳልሆነ ነግሮናል፤ ጥላቻው በመላው የትግራይ ሕዝብ ላይ ነው ፤ ይህ ደግሞ አሁን የተከሰተ ነገር አይደለም፤ ከመቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት በተለይ ከአድዋው ድል በኋላ በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚታይ የጥላቻ እንቅስቃሴ በሁሉም የፖለቲካ፣ የማሕበረሰባዊ፣ የምጣኔ ሃብታዊ ብሎም የመንፈሳዊ ህይወት ይታያል። ዋናው ጥያቄ ከምን የመጣ ነው?

መልሱ አንድ እና አንድ ነው፤ በሃገራችን ትክክለኛውን ኢትዮጵያዊነትን፣ ጥልቅ መንፈሳዊነትንና ሃሞት ያለው ወኔን ይዘው የቆዩት ትግሬ ኢትዮጵያውያን፤ ምናልባትም በላስታና ላሊበላ አካባቢ የሚገኙት የቤተአምሐራ ኢትዮጵያውያን ብቻ ስለሆኑ ነው። ለዘመናት፡ በረሃቡም፣ በበሽታውም በጦርነቱም ክፉኛ እየተጠቁ ያሉት እነዚህ አካባቢዎች ናቸው፤ የሁሉም ሉሲፈራውያን አትኩሮት በአኩስም እና ላሊበላ ላይ ነው፣ ከዚህ አካባቢ በተገኙት በእነ አፄ አምደ ፅዮን፣ አፄ ዮሐንስ ፥ ዛሬም በእነ ጄነራሎች አሳምነውና ሰዓረ እንዲሁም አቶ ልደቱ አያሌው ላይ የተደረገውና እየተደረገ ያለው ጥቃት የሚሰነዘረው የክስተቱን ጥልቅ መንፍሳዊ ልኬት ይጠቁመናል።

ስለዚህ አሁን በሰነፉትና በተዳከሙት ኢትዮጵያውያን ላይ እየታዩ ያሉት እንደ ቅናት፣ ምቀኝነትና አድመኛነት የመሳሰሉ በጣም አደገኛና ገዳይ የሆኑ የሰው ልጅ ባሕርያት ወደ ጥላቻ ስለሚወስዱን ፣ የተመሰቃቀለ፣ አከፊና መከራ የበዛበት መራራ ኑሮን ለመኖር እንገደዳለን ማለት ነው።

[የያዕቆብ መልእክት ምዕራፍ ፫፥፲፮]

ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና።”

[የያዕቆብ መልእክት ምዕራፍ ፬፥፪፡፫]

ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤ ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም።”

[፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፬፥፳]

ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?”

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፳፡፩፥፳፫]

ወንድምም ወንድሙን፥ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ ይገድሉአቸውማል። በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፥ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።”

___________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: