Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for January 3rd, 2021

አሕዛብ ለምን ያጕረመርማሉ? ወገኖችስ ለምን ከንቱን ይናገራሉ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 3, 2021

👉 አህዛብ የዋቄዮ-አላህ ሃይል በወገኖቻችን ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋዎችን በሚያካሂድበት፣ ሐሰተኛው፣ ምላሰኛው፣ ፈራጁ፣ ሸንጋዩና ገዳዩ በበዛበት በዚህ ከባድ ወቅትና በዚህ የዕለተ ሰንበት እንደ አንድ መንፈሳዊ ውጊያ ይሆነን ዘንድ እስኪ ይህን ሃሳቤን ላጋራችሁ አንባቢ ወገኖቼ፦

አዎ! “ሐሰትን የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፤ ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው እግዚአብሔር ይጸየፋል። በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው፤ ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።”

ይህ ኃያል ቃል በተለይ አህዛብ የዋቄዮአላህ ልጆችን በቀጥታ ይመለከታል። እባቡን ግራኝ አብዮት አህመድን ወገኖቻችን፤ “አፈ ቅቤ ልበ ጩቤ” የሚሉት ያለምክኒያት አይደለም፤ ለነገሩማ እኔ “አፈ ፍዬል ልበ ጋኔን” ብለው እመርጣለሁ። ግን ይህን ከየት የተማረው ይመስለናል? አዎ! ከእስልምናው ቁርአን ከሐሰተኛው ነቢይ መሀመድ ነው።

👉 ለምሳሌ ከብዙ በጥቂቱ ቁርአን በሱራ አል ኢምራን328 ዋቄዮአላህ ለተከታዮቹ እንዲህ ይላቸዋል፦ አይሁዶችን እና ክርስቲያኖችን ጓደኛ(ረዳቶች) አድርጋችሁ አትያዙ፡ ከእነርሱ ጋር ጓደኛ የሆነ እስልምናውን እንደተወ ይቆጠራል።“

ይህን ሱራ በጣም ታዋቂና ተቀባይነት ያላቸው ተፍሲሮቻቸው አልቡኻሪእና ኢብን ካቲርእንዲህ ሲሉ አብራርተውታል፦

ልባችን ቢረግማቸውም በአንዳንድ ሰዎች ፊት ፈገግ እንላለን። አፈ ቅቤ ልበ ጩቤ!

በተቃራኒው የእኛ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን እንዲህ ይለናል፦

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፭፵፥፬፡፵፭]

እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።”

🔥ክርስቲያኖች አንድ ማወቅ ያለብን ጥብቅ ነገር ቢኖር፡ የእስልምና እምነት መሥራች የሆነው መሀመድ ባሏን፡ወንድሟን፡እና አጎቷን አርዶ የገደለባት ሴት መሀመድን መርዝ አብልታው፡ ለሞት በሚያጣጥርበት አልጋው ላይ ለሙስሊሞች ታላቅ ተልዕኮ ሰጥቷቸው ነበር። መሲሁ አምላካችን ኢየሱስ ወደ አባቱ ከማረጉ በፊትም ለክርስቲያኖች እንዲሁ ታላቅ ተልዕኮ ሰጥቷቸው ነበር፡ ይህም እንደሚከተለው ይገለጻል።

[ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፰፥፲፱፡፳]

እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”

መሀመድም ለተከታዮቹ ለሞት በሚያጣጥርበት አልጋው ላይ የመጨረሻውን ትዕዛዝ እንዲህ ሲል አዘዛቸው።

ሱራ አል ተውባህ= 929 ከእነዚያ መጽሐፍን ከተሰጡት ሰዎች እነዚያን በአላህና በመጨረሻው ቀን የማያምኑትን፣ አላህና መልክተኛው እርም ያደረጉትንም እርም የማያደርጉትንና እውነተኛውንም ሃይማኖት የማይቀበሉትን እነርሱ የተዋረዱ ኾነው ግብርን በእጆቻቸው እስከሚሰጡ ድረስ ተዋጉዋቸው፡፡

🔥 ምንም እንኳን መሀመድ ገና ብዙ ተከታይ እና ኃይል ባልነበረው ጊዜ በመካ ወረደልኝ ባላቸው በቁርዓን አንቀጽ ላይ

በሱራ አል በቀራህ=2256 ላይበሃይማኖት ማስገደድ የለም ብሎ እንዳልነበር ሁሉ በሚቀጥለው ምዕራፍ የተናገረው ሁሉ ተረስቶ በሱራ አል ኢምራን= 385 “” ከእስልምና ውጪ ሌላ እምነት ተቀባይነት የለውም በማለት ተናገረ።

ነገሩ በዚህ ብቻ አላቆመም ቀጥሎም

በሱራ አል ማኢዳህ 533 “” አላህን እና ነቢዩን የሚቃወሙትን

( ክርስቲያኖችን፡አይሁዶችን፡ በብዙ አማልክት( ጣዖት) የሚያመልኩትን ግደሏቸው፡ በመስቀል ላይ ስቀሏቸው፡ እግሮቻቸውን እና እጆቻቸውን በማፈራረቅ ቆራርጧቸው በመጨረሻም ከሐገር አባርሯቸው በማለት ለሙስሊሞች ታላቁን ትዕዛዝ ሰጣቸው።

🔥ዛሬ በሐገራችን የምናያቸው የዋቄዮአላህ አርበኞች ወይም አክራሪ ሙስሊሞች ፣ አላህ ዋክባር! ቢስሚላሂ! እያሉ ክርስቲያኑን የሚያርዱትና በጅምላ ለማረድ በመዘጋጀት ላይ ያሉት በቁርዓኑ በትክክል የተገለጸውን ነው። እስልምና እንግዲህ ይህ ስለሆነ “ተቻችለን፣ ተከባብረን ቅብርጥሴ” ብሎ መሸፋፈን ራስን ማታለል ነው።

በሱራ አል ማኢዳህ =551፥ በሱራ አል ኢምራን=328 “አይሁዶችን እና ክርስቲያኖችን ጓደኛ( ረዳቶች) አድርጋችሁ አትያዙ፡ ከእነርሱ ጋር ጓደኛ የሆነ እስልምናውን እንደተወ ይቆጠራል ይልሃል።

አሁን ወደ መጀመሪያው የመሀመድ ታላቁ ተልዕኮ ብሎ ሙስሊሞችን ያዘዘውን ትዕዛዝ አንድ በአንድ እንየው።

ሱራ አል ተውባህ=929 ሙስሊሞች በመሀመድ አይሁድንና ክርስቲያኖችን እንዲዋጓቸው ታዝዘዋል። ለምን ካልን በመሀመድ ነቢይነትና በአምላኩ አላህ ባለማመናቸው፡ መሀመድ የከለከለውን ስለሚያደርጉ፡ የፈቀደውን ስለማይቀበሉና፡ በእስልምና አስተምህሮ ስለማይኖሩ : እውነተኛው እምነት የሆነውን እስልምናን ስለማይቀበሉ ነው ይለናል በተፍሲሩ ( በትርጉሙ)

አክራሪ ሙስሊሞች ነቢያቸው መሀመድ ካዘዛቸው ውጪ ምን የተለየ ነገር አደረጉ በማለት Professor. William Wagner. How Islam Plans to Change the World. በተባለው መጽሐፉ እውነተኛ ሙስሊሞች አክራሪዎቹ ናቸው በማለት ሐሳቡን ይደመድማል። ሌሎቹ በማስመል የሚኖሩ እና አል ጣቂያን(የማታለል ጥበብን)በተግባር የሚፈጽሙ ናቸው ይላቸዋል።

🔥 እስቲ ወደ ኋላ ተመልሰን በጥንቶቹ የሶሪያ ክርስቲያኖች፡ የመጀመሪያ ቤተ ክርስቲያን(የክርስቲያን ማሕበር ) የተመሠረተባት ሶሪያ በሁለተኛው የሙስሊም ከሊፋ በሆነው ኡማር ኢብን አል ከታብ ባልታሰበ ወረራ፡ ያወደሙትን አውድመው ሐገሪቷን ከተቆጣጠሩ በኋላ ክርስቲያኖች ሁለተኛ ዜጋ ሆነው ፡ ከባርነት ባልተናነሰ ኑሮ እንዲኖሩ ሕግ ወጣባቸው።

🔥ይህም ሕግ የኡማር ውል ወይም ስምምነት(Pact of Umar)ይባላል። ይህንን ውል ስናነብ የአክራሪ እስላሞች ምኞት በሐገራችን ላይ ምን እንደሆነ ፍንትው ብሎ ይታየናል።

ክርስቲያኖች አዲስ ቤተ ክርስቲያን መሥራት፡ አሮጌውንም ማደስ በፍጹም አይችሉም።

የሙስሊም መንገደኞች፡ ሩቅ መንገድ ተጓዦች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እረፍት ማድረግ ማደር ይችላሉ።

ክርስቲያኖች እስላማዊ መንግስትን ለመቃወም፡ ድጋፍ መስጠት፡ ተጻራሪ መሆንም አይቻልም።

ክርስቲያኖች፡ ለሙስሊሞች ሁሉ የአክብሮት ሰላምታ መስጠት አለባቸው።

ክርስቲያኖች በፈረስ ሲጓዙ ያለ ኮርቻ እና ልጓም መሆን አለበት። ምቾት እንዳይሰማቸው።

ክርስቲያኖች በጣታቸው ቀለበት፡ ለአንገታቸው ጌጥ ማድረግ አይችሉም።

ክርስቲያኖች የሙስሊሞች የበታች መሆናቸው ተለይተው እንዲታወቁ አንድ አይነት መልክ ያለው ፡ ልብስ ብቻ ይለብሳሉ። በግብጽና በአገራችንም ካህናት ጥቁር መልበስ የጀመሩት ይህን ተከትሎ ነው። ክርስቲያኖች፡ ከሙስሊሞች አጠገብ ቤት መሥራት አይችሉም።

ክርስቲያኖች፡ የሃይማኖት በዓላቶቻቸውን በሕዝብ ፊት ማክበር አይችሉም። ለቅሶም ድምጽን ከፍ አድርጎ ማልቀስ አይቻልም። በኦሮሚያ ሲዖል እያየነው ያለነው ይህን ነው።

በቤታቸው በኩል የሚያልፍ መንገደኛ ሙስሊምን ለሶስት ቀን መመገብ አለባቸው። የግራኝ አብዮት አህመድ ሠራዊት በትግራይ እያደረገ ያለው ይህን ነው።

ክርስቲያኖች ለሙስሊም ሊቀመጥ ከወደደ መቀመጫቸውን ተነስተው መስጠት አለባቸው።

ክርስቲያኖች በቀላሉ ተለይተው እንዲታወቁ የፊተኛው ጸጉራቸው ሙሉ ለሙሉ መላጨት አለበት። ይህም ለሙስሊሞች መሳቂያ ያደርጋቸዋል።

ክርስቲያኖች ጥበቃ እንዲደረግላቸው የተለየ የጥበቃ ገንዘብ ቀረጥ(Jizya) መክፈል አለባቸው።

የአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ቅብርጥሴ… እነ ታከለ ኡማ እና አዳነች አበቤ እያደረጉት ያሉት ይህን ነው። የአዲስ አበባን መሬት፣ ቤትና ገንዘብ ነጥቀው ወደ ኦሮሚያ ሲዖል። ልብ አላልንም እንጅ ይህ ለአለፉት መቶ ዓመታት ሲፈጸም ነበር። ሰሜኑ እንዲራብና እንዲራቆት የተደረገበት አንዱ ምክኒያት ሰሜናውያኑ ላባቸውን አንጠብጥበው ደማቸውን አፍስሰው ያፈሩትን ንብረትና ገንዘብ በኦሮሞዎች መስፋፊያና መጠናከሪያ ላይ እንዲውል በመደረጉ ነው። ደማቸውን አፍስሰው ደርግን ያስወገዱት ትግሬዎች እንኳን ለራሳቸው ቁራሽ ግዛት ይዘው ለኦሮሞዎቹ ግማሽ ኢትዮጵያን አስረክበዋቸዋል። በሕዝቡ ብርታት እንደ አዲስ አበባ በደንብ ያለሟቸውን ከተሞችን፣ ኢትዮጵያዊው በላቡ የገነባውን የሕዳሴውን ግድብና ሌሎች ፕሮጀክቶች ሳይቀሩ ይህ ነው የሚባል አስተዋጽኦ ላላደረጉት ለኦሮሞዎቹ በነፃ አሳልፈው ለመስጠት ዝግጁነታቸውን እያሳዩ ነው። በተቃራኒው ግን በትግራይ የነበሩት ፕሮጀክቶች ሁሉ በወራሪዎቹ የግራኝ አብዮት ኦሮሞ ሰራዊትና በኢሳያስ አፈቆርኪ ሰራዊት አንድ በአንድ እየፈራረሱ ነው። ትግሬዎቹ መጀመሪያ ነፃነቱን ለኢሳያስ አፈቆርኪ ኤርትራ ለገሷት፣ ከዚያም አራት ኪሎን ለ አብዮት አህመድ አሊ ኦሮሞዎች በፈቃዳቸው አስረከቡ፤ አሁን እነዚህ ሁለት ከሃዲዎች ወደ ትግራይ ተመልሰው ጭፍጨፋ እና ዘረፋ በባለውለታቸው ላይ ይፈጽማሉ። የት ነው እንዲህ ያለ ጉድ ተሰምቶ የሚያውቀው?

ወደ ኡመር ውል ስንመለስ፤ ይህ ውል ወይም ስምምነት Contract between the patriarch of Jerusalem, Sophorius and Islam’s second caliph Umar ibn al Khattab” በመባል ይታወቃል። በእንደዚህ ያለ ሕገ አራዊት ሥርዓት ተገዢ እንዳንሆን እግዚአብሔርን አብዝተን መለመን አለብን።

ለምሳሌ የሳኡዲ አረቢያው ሼክ ማርዙቅ ሳሌም አል ጋምዲ እስላማዊ ሕገ ፍልስፍና ብሎ በ፪ሺ፪/2002 .ም በቴለቪዥን የኡመርን ስምምነት ዛሬም መጠቀም አለብን በማለት ሰብኮ ነበር።

🔥አክራሪ እስላሞች ልክ እንደ ዘመነ ኡመር ክርስቲያኖችን ኃይል ተጠቅመን መግዛት አለብን የሚል ከፍተኛ ምኞት አላቸው።

ዛሬ አሰቃቂ ግድያ: በኢትዮጲያ በተለይ በባሌ፡ በወለጋ፣ በወሎ፣ በአሩሲ፡ በሻሸመኔ፡ በኦጋዴን፣ በሐረርጌና በቤኒሻንጉል የሚታየው ይህንን የሕገ አራዊት በክርስቲያኖች ላይ ለመጫን ነው። የቤተ ክርስቲያን መምህራንና ተቆርቆሪዎቿ ሁሉ ትኩረታቸው፡ የክርስቶስ ተቃዋሚ በሆነው በእስልምና ርዕዮተ ዓለም ላይ መሆን አለበት።

🔥የእስልምና ትክክለኛ ትምህርት አውቀን ሕዝቡን ማንቃት፡ መሀመድን ሐሰተኛ ነቢይ መሆኑን ገልጾ መናገር። አላህ በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጸው እግዚአብሔር አለመሆኑን ገልጾ በማስተማር አንዳንድ ነፍሳትን የማዳን ሥራ መሥራት። ክርስቲያኖች በአህዛብ ጥቃት ሲደርስባቸው፡ ከጥቃት እንዲሸሹ እና ከጥቃት እራሳቸው እንዲከላከሉ አስቀድመው በመዘጋጀት እንዲኖሩ ማድረግ ግድ ነው።

እግዚ አብሔር አጽራረ ቤተ ክርስቲያንን ያስታግስልን፡ በመግደል እንጸድቃለን የሚሉትን አይነ ልቦናቸውን አብርቶ ወደ ቀናው መንገድ ይመልስልን።

[መዝሙረ ዳዊት ከ ምዕራፍ ፩ እስከ ፭]

፩ አሕዛብ ለምን ያጕረመርማሉ? ወገኖችስ ለምን ከንቱን ይናገራሉ?

፪ የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ።

፫ ማሰርያቸውን እንበጥስ፥ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል።

፬ በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል።

፭ በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል፥ በመዓቱም ያውካቸዋል።

፮ እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ።

፯ ትእዛዙን እናገራለሁ፤ እግዚአብሔር አለኝ። አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።

፰ ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ።

፱ በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃዎች ትቀጠቅጣቸዋለህ።

፲ አሁንም እናንት ነገሥታት፥ ልብ አድርጉ፤ እናንት የምድር ፈራጆችም፥ ተገሠጹ።

፲፩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፥ በረዓድም ደስ ይበላችሁ።

፲፪ ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፭]

፩ አቤቱ፥ ቃሌን አድምጥ፥ ጩኸቴንም አስተውል፤

፪ የልመናዬን ቃል አድምጥ፥ ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥ አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁና።

፫ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፥ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ፥ እጠብቃለሁም።

፬ አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና፤ ክፉ ከአንተ ጋር አያድርም።

፭ በከንቱ የሚመኩ በዓይኖችህ ፊት አይኖሩም፤ ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላህ።

፮ ሐሰትን የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፤ ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው እግዚአብሔር ይጸየፋል።

፯ እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ አንተን በመፍራት ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ።

፰ አቤቱ፥ ስለ ጠላቶቼ በጽድቅህ ምራኝ፤ መንገዴን በፊትህ አቅና።

፱ በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው፤ ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።

፲ አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በምክራቸውም ይውደቁ፤ ስለ ክፋታቸውም ብዛት አሳድዳቸው፥ እነርሱ ዐምፀውብሃልና።

፲፩ በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ግን ደስ ይላቸዋል፤ ለዘላለሙ ደስ ይላቸዋል፥ እነርሱንም ትጠብቃለህ፤ ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ ይመካሉ።

፲፪ አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና፤ አቤቱ፥ እንደ ጋሻ በሞገስ ከለልኸን።

_____________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: