Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

ፀረ-ትግሬ አቋም እንዳይኖረን አባ ዘ-ወንጌል አስጠንቅቀውናል ፥ አስተዋዩ ወንድማችንም ያስታውሰናል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 17, 2020

አንድ ወገን “ኢትዮጵያዊ” ሊባል የሚችለው ልክ እንደዚህ ወንድማችን ዓይነት አቋም ሲኖረው ብቻ ነው። ግን እንደምናየው አብዛኛው ይህ ትውልድ ወራዳ፣ ከንቱና ባለጌ ነው።

አባ ዘ-ወንጌል “ዋ!” ብለው አስጠንቅቀውናል፤ የኢትዮጵያን ትንሣኤ የማየት ዕድል የሚኖራቸው በትግሬ ኢትዮጵያውን ላይ ጥላቻን የማያሳዩት ብቻ እንደሚሆኑ በግልጽ ጠቁመውናል። እነ ዘመድኩን በቀለ ለአጀንዳቸው እንደሚያመቻቸው አድርገው በማቅረብ ይህን የአባታችንን መልዕክት ክፍል በጽሑፎቻቸው አላካተቱም። ትልቅ ቅሌት! ይህ መለኮታዊ ምስጢር ያለው ማስጠንቀቂያ እንጂ “ከአወቅኩሽ ናቅኩሽ” ስጋዊ የስንፍና እና ፉክክር አቋም የተነሳ በግድየለሽነት መታለፍ የሚገባው ማስጠንቀቂያ አይደለም። ጊዜው የፈተና ጊዜ ነው፤ ማንነታችንን በሥራና በተግባር የምናሳይበት ዚጌ ነው፤ በጽዮን ላይ በማመጽ እንደነ ግራኝ አብዮት የትንቢት መፈጸሚያዎች እንዳንሆን ልንጠነቀቅ ይገባናል።

ከአሥር ዓመታት በፊት “አክራሪ” የሚባሉትን የአማራ፣ ኦሮሞ እና ትግሬ ብሔርተኞችን በቅርቡ የመከታተልና የማጥናት ዕድሉ ነበረኝ። ሳልወድ።

የህወሃት ደጋፊዎች የነበሩትን ወገኖች ከአሥር ዓመታት በፊት በአንድ አጋጣሚ እንዲህ አልኳቸው፤ “ይህ የብሔር ብሔረሰብ ክልላው ሥርዓት የትም አያደርሰንም፤ ወደ እርስበርስ ጦርነት ነው የሚወስደን…” ይህ አቋሜ ስላላስደሰታቸው እንዲህ አሉኝ፤ “ብሔረሰቦቹ እኮ እራስን በራስ የመወሰን ነፃነቱንና መብቱን ስለሚሰጣቸው ከምኒሊክ አማራዎች በቀር፤ ሁሉም ብሔረሰቦች ተቀብለውታል።” እኔም፤ “እንዴ! በቅድሚያ የዚህ የብሔር ብሔረሰብ ሥርዓት መስራች እኮ እራሳቸው አፄ ምኒሊክ ናቸው፤ እሳቸውም ቢሆኑ ከአደዋው ድል በኋላ በኦሮሞ የስጋ ማንነታቸው ነበር ኢትዮጵያን ሲመሯት የነበሩት፤ ይህ ፀረ-አማራ አቋማችሁ በጎ አይመስለኝም።” ብያቸው አርእስት እንድንቀይር ለመንኳቸው። እንደሚወራው መጥፎ ወገኖች አልነበሩም፤ የያዙት አቋም የተሳሳተና እራሳቸውን በይበልጥ እንደሚጎዳቸው ሆኖ ነበር የታየኝ። አጋጣሚውን ሳገኝ በየጊዜው ስለሁኔታቸው እጠይቃቸው ነበር፤ በራሳቸውና በሚያቋቸው አጋሮቻቸው ቤት ውስጥ መቅሰፍት እንደገባባቸው ነበር የታዘብኩት፤ ከስኳር እና ደም ግፊት እስከ ነቀርሳ እና ጽንስ መጨናገፍ በእያንዳንዱ ቤት እንደገባ ተነግሮኝ ነበር። “ወደ እምነታቸሁ ተመለሱ!” ነበር ያልኳቸው። በኦሮሞዎቹም መካከል ተመሳሳይ ነገር ነው የታዘብኩት፤ በትግሬ እና አማራ ላይ ከያዙት የጥላቻ አቋም የተነሳ እስከ ማበድና መሰቀል የደረሱትን ወገኖች በቅርብ አይቻለሁ፤ አጽናንቻለሁ። አሁን ሰሞኑን ከምናየው የአማራ የዘረኝነት እብደትም ጋር በተያያዘ ተመሳሳይ መቅሰፍት ወደ አማራ ብሔርተኞች ቤት ውስጥ እንደሚገባ ምንም ጥርጥር የለውም፤ እስኪ ከሰሞኑ ልሂቃኑን እንጠይቃቸው?

ለወንድማችን የከበረ ምስጋና!

ግራኝ አብዮት አህመድ ከአረቦቹና ቱርኮች ጋር ተናብቦ በመስራት ላይ ነው። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር ጉብኝት ሌላ ድራማው ነው፤ ከሱዳን፣ ግብጽ እና ሳውዲ አረቢያ ጋር በምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ከኤሚራቶችና ኢሳያስ አፈቆርኪ ጋር በሰሜንና ምስራቅ፣ ከቱርኮች፣ ካታርና ሶማሌዎች ጋር በደቡብ ምስራቅ በኩል የአህዛብ ሠራዊቶችን በማሰባሰብ ላይ ነው። ኬኒያስ? እናያለን። ሱዳን ሰራዊቷን እንድታስጠጋ የፈቀደው ግራኝ አብዮት አህመድ ነው። በዚህ 100% እርግጠኛ ነኝ። በዚህ ሤራው በቅድሚያ ስደተኞች ከትግራይ ወደ ሱዳን እንዳይሄዱ ያደርጋቸዋል፤ ቀጥሎም በአረቦቹ መሪነት እነግብጽ የአማራና ቤኒሻንጉል ክልልን (ግድቡን)እንዲቆጣጠሩ ይፈቅድላቸዋል። አይ ሞኙ ከንቱው ሃበሻ! እርስበርስ በከንቱ ስትበላላና ስትደክም ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ የመንፈስ ዘመዱ የሆኑትን አውሬዎች ይውጡህ ይሰለቅጡህ ዘንድ ወደ ብቸኛዋ ሃገርህ እየጋበዘልህ ነው። አዎ! አረቦችን ለማስገባት ትግሬዎችን ማድከምና መበታተን ነበረበት።

አይ ሞኙ ከንቱው ሃበሻ! እርስበርስ በከንቱ ስትበላላና ስትደክም ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ የመንፈስ ዘመዱ የሆኑትን አውሬዎች ይውጡህ ይሰለቅጡህ ዘንድ ወደ ብቸኛዋ ሃገርህ እየጋበዘልህ ነው። አዎ! አረቦችን ለማስገባት ትግሬዎችን ማድከምና መበታተን ነበረበት።

👉 አባታችን አባ ዘወንጌል ይህን ነግረውን ነበር

በአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያ ትወረራለች። ሰላም በማስከበር በሚል ሰበብም በ2 ሃያላን ሀገራት የሚመሩ ሰባት የሙስሊም ሀገራት በኢትዮጵያ ምድር ላይ እሳት ያዘንባሉ። በአሰብ ወደብ ላይ በልዩ ሁኔታ የተከማቸው የጦር መሣሪያ በኢትዮጵያ ምድር ላይ እንደበረዶ ይዘንባል። ብዙ ፍጅትም ይሆናል። ኦርቶዶክሳውያን በያሉበት፣ በየተገኙበት እንደከብት ይታረዳሉ። የኢትዮጵያ ምድር በደም ትጨቀያለች። የደም ጎርፍ፣ የደም አበላ በምድሪቱ ላይ ይፈሳል።”

_______________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: