የሳጥናኤል ጎል ቍ. ፬ | በሰሜን ኢትዮጵያውያን ላይ ጦርነት እንዲከፍት የታዘዘው ግራኝ የሲ.አይ.ኤ ምልምሉ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 16, 2020
የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ ቍ. ፬ ፥ ፀሐፊ ፍሰሐ ያዜ
👉 እኔ ያከልኩበት ማስታወሻ፦
እ.አ.አ በ2012 ዓ.ም በቤልጂም ብራሰልስ ከተማ ነበር ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ የተሰዋው። (ነፍሱን ይማርለት!) እኔ በወቅቱ እዚያ ነበርኩ። ይገርማል በዚሁ ወቅት ነበር ከሰሜን ያልሆነው አብዮት አህመድ አሊ በሉሲፈራውያኑ ተመርጦ በ2014 ዓ.ም የተቀባው።
👉 ሌላው ደግሞ እኅተ ማርያምን በዚሁ ዓመት እንድትታይ እና ወደ ኢትዮጵያም እንድትገባ ያደረጓት እነርሱ ናቸው የሚል ጥርጣሬ አለኝ። የኢትዮጵያ ዝርያ እንዳላት የሚነገርላት የብሪታኒያዋ ንግሥት ኤልሳቤጥ ፪ኛ ወኪል ትሆንን?
👉 በሃገራችን በየመስኩ በተደጋጋሚ ብቅ ብቅ እያሉ የሰዎችን አእምሮ ለማጠብ የተሰማሩት የ “ዶ/ር” ቹ ብዛት አያስገርማችሁምን? አዎ! በተዋሕዶ ሰሜን ኢትዮጵያውያን ላይ ጦርነት እንዲከፈት ሲወተውቱና የጦርነት ነጋሪትም የሚጎስሙት እነዚሁ የወደቁት ልሂቃንና ሜዲያዎቻቸው እንደሆኑ እያየነው ነው። አቤት መብዛታቸው!
[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፺፩፥፯]
“ኃጢአተኞች እንደ ሣር ሲበቅሉ ዓመፃ የሚያደርጉ ሁሉ ሲለመልሙ፥ ለዘላለም ዓለም እንዲጠፋ ነው።”
❖ ❖ ❖ አውሬው ግራኝ አብዮት አህመድ፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በድንግል ማርያም ስም ከሃገራችን ኢትዮጵያ ቶሎ ይወገድልን። አሜን! አሜን! አሜን!❖ ❖ ❖
ለመሆኑ “የሰሜን እዝ”ላይ ህወሃት ጥቃት ማድረሱንና በእነርሱ ቁጥጥር ሥር መሆኑ ምን ማስረጃ አለ?

ግራኝ አብዮት ትግሬ የእዙን አባላት ከገደለ በኋላ እራሱ ተቆጣጥሮት ሊሆን አይችልምን? ወይንም ኢሳያስ አፈቆርኪ እዙን ተረክቦት ቢሆንስ? ህወሃቶች ወይ ይህ ከቁጥጥራቸው መውጣቱ አስደንግጧቸዋል፤ አልያ ደግሞ ከቀናት በፊት እንዲህ በማለት እንዳወሳሁት ሁሉም ተናብበው በመስራት በትግራይ ሕዝብ ላይ ድራማ እየሠሩ ጀነሳይድ ለመፈጸም ወስነዋል፤ እንደሚመስለኝ የህወሃት አመራሮች ከአገር ውጭ ሊሆኑ ይችላሉ። ዋናው ዓላማው ትግሬን ከአማራና ኤርትራውያን ጋር ማባላትና ትግሬ ኢትዮጵያውያንን መጨፍጨፍ ስለሆነ በደ ባሕርዳር እና አስመራ የተተኮሱትን ሮኬቶቹንም እራሱ ግራኝ በኤሚራቶች ድጋፍ ተኩሷቸው ሊሆን ይችላል።
👉 ከቀናት በፊት እንዲህ በማለት የጻፍኩትን ፦ “ቤተ እስራኤል በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እስራኤል ፥ ቤተ ኢትዮጵያ በእግር ወደ ሱዳን” https://youtu.be/VzL0_Ck4ceY
“አዎ! እንደምናየው የትግራይን ሕዝብ ሊያስጨርሱት የወሰኑ ይመስላሉ፤ ዛሬ ሳሰላስል የመጣልኝ ጥያቄ፡ “ላለፉት ሁለት ዓመታት ሀወሃት የጦር ሠራዊቱን ጡንቻ ለማሳየት ብዙ ልምምዶችን ሲያካሂድ ነበር፤ ይህን ልምምድ በተለይ የትግራይ ሕዝብ ነው እንዲያየው የተደረገው፤ ይህን የልምምድ ትዕይንት የተከተለው ባለፈው በትግራይ ተካሂዶ የነበረው ምርጫ ነበር፤ ታዲያ ልምምዱ “እኔ ነኝ አለኝታችሁ፤ እኔን ከመረጣችሁ እከላከላችኋለሁ፤ ካልመረጣችሁ ለጠላት አሳልፌ እሰጣችኋለሁ” የሚል መልዕክት ኖሮት ይሆን? ምናልባት ህወሃት እንደጠበቁት በትግራይ ነዋሪዎች ዘንድ ባለመመረጣቸው፤ አሁን ሕዝቡን እየተበቀሉት ይሆን? እንግዲህ እንኳን ትግራይን መላው ምስራቅ አፍሪቃን የመከላከል ብቃቱ እንዳላቸው ለሰላሳ ዓመታት ያህል አሳይተዋል፤ ታዲያ ዛሬ ያሰለጠኑትን ልፍስፍስ የግራኝን ሠራዊት እንዴት ሰተት ብሎ ወደ ትግራይ እንዲገባ ፈቀዱለት? ጦርነት መምጣቱስ ላልቀረ ገና አዲስ አበባ አራት ኪሎ እያሉ መዋጋት ይችሉ አልነበረምን? ለምን ወደ ትግራይ ሄደው መሸጉ? ሆን ብለው ይህን ጦርነት ወደ ትግራይ ለማምጣት አይደለምን?
👉 ዛሬ የወጣ አንድ መረጃ ምናልባት በቀል ሊሆን እንደሚችል በከፊል ያረጋግጥልኛል፦
“ግማሽ ትግራዋይ ፣ ግማሽ ኤርትራዊት የሆነችው ሰሚራ “አባቴን ለመጨረሻ ጊዜ ሲያለቅስ ካየሁ ረጅም ጊዜ ሆኖኛል” ብላለች፡፡
“የማውቃቸው ሰዎች ወያኔን ይጠላሉ፡፡ አሁን ግን ህወሀትን እንዲያሸንፍ ይፈልጋሉ፡፡ ስልጣኑን እንዲረከቡ ይፈልጋሉ፡፡ በ [የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ]ላይ ተስፋ የነበራቸው ሰዎች እንኳን፡፡“
“It had been a long time since I last saw my father cry,” said Semira, who is half Tigrayan, half Eritrean.
“The people that I know, they hate the TPLF. But now they want the TPLF to win. They want them to take over the power. Even people who had hope in [Ethiopia’s prime minister, Abiy Ahmed].
https://www.dw.com/en/ethiopia-eu-suspends-budget-support-over-tigray-conflict/a-55944784
___________________________
Leave a Reply