የትግራይ ጦርነትና ግራኝ ትዊተርን አጨናነቁት | የእርስ በርስ ጦርነት ወደ አሜሪካ እየመጣ ነውን?
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 15, 2020
አሜሪካ ከፍተኛ ውጥረት ላይ ትገኛለች። በዋሽንግተን ዲሲ በትራምፕ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች መካከል ግጭት ተቀስቅሷል፤ ሰዎች በቢለዋ ተወገትው ቆስለዋል። በአሜሪካ ምርጫ ከተካሄደበትና በትግራይ ላይ ጦርነቱ ከጀመረበት ዕለት አንስቶ የአሜሪካ ቀጣዩ ፕሬዚደንት ማን እንደሆነ እስካሁን ግልጽ አይደለም። ይህ በአሜሪካ ታሪክ ታይቶ አይታወቅም።
ትዊተር ትግራይን እና ግራኝ አብዮት አህመድን በተመለከቱ እጅግ በጣም ብዙ ተደጋጋሚ ትዊቶች ተጥለቅልቋል። ይህ በአጋጣሚ አይደለም! የፕሬዚደንት ትራምፕ ተቀናቃኞች (ግራኞች) ምናልባት ትራምፕ ከመሰናበታቸው በፊት የአመጽ አዋጅ ያወጣሉ ብለው ፈርተው ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ግራኞቹ እንደ የትግራይ ደጋፊዎችና ተሟጋቾች መስለው ስለ አመጽ በመለጠፍ እና የፍለጋ ስልተ ቀመሮችን ለማዛባት አሁን ሰዎች ጊዜው ሳይደርስ እርምጃ እንዲወስዱ መልዕክት ለማስተላለፍ ፈልገው ሊሆን ይችላል።
የሲ.አይ.ኤ ቅጥረኛው ግራኝ አብዮት አህመድ በሰሜን ኢትዮጵያውያን ላይ የከፈተው ጦርነት ባስከተለው ዕልቂት አሜሪካ ክፉኛ ትቀጣለች። በትግራይ ላይ በተከፈትው ጦርነት ብቻ እስካሁን እስከ መቶ ሺህ ሰሜን ኢትዮጵያውያን ሳይገደሉ እንዳልቀረ ይገመታል። ሬሳዎችን የሚያነሳላቸው ሰው ጠፍቶ ጅቦች…እህ ህ ህ!!!ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል በተባሉትም ክልሎች ሰሜን ኢትዮጵያውያን እየታደኑ በመታረድ ላይ ናቸው።
ይህን ሁሉ ጭካኔ እግዚአብሔርና መላዕክቱ ያዩታል፤ ስለዚህ አሜሪካ፣ አውሮፓና አረቢያ በሚቀጥሉት ወራት በረሃብ፣ በበሽታና በእርስበርስ ጦርነት ይናወጣሉ።
__________________________
Leave a Reply