ገዳይ አብይ ተንቤንን በአውሮፕላን የሚደበድበው አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅን ለመበቀል ነው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 14, 2020
❖ አባ ዓቢየ እግዚእ በ፲፬/14ኛው መቶ ክ/ዘመን ትግራይ ተንቤን (መረታ) ውስጥ ተወለዱ
+ ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ። ይሕን ድንቅ ያዩ ከ ፩/1ሺህ በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል
☆ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ እ.አ.አ በ2014 ዓ.ም በሉሲፈራውያኑ ተቀባ
እንደ ግራኝ አህመድ ቀዳማዊ አባቱ። ዲቃላው አብዮት አህመድ አሊ የሴቲቱን የገዥነት ስምና ክብር በመያዝ ነው በአክሱም ጽዮን ላይ ጦርነቱን ያወጀው። እንደምናስታውሰው ከመቶ ሃያ ዓመታት በፊት ኢትዮጵያውያን በአድዋ ላይ የተቀዳጀነው ድል ምንም እንኳ ባጠቃላይ የእግዚአብሔር ድል ይሁ እንጅ በውስጡ ግን የሚያስተላልፈውና የሚናገረው ሌላ ምስጢር ነበር፤ ይህም የአደዋው ድል የእቴጌ ጣይቱ ብጡል ድል መሆኑን ነው። ድሉ የሴቶችን የበላይነት ይናገር ነበር፤ የሴቶች የበላይነት ስምና ክብር የታየበት፣ የተገለጠብትና የነገሰበት ድል ነበር። ይህ ደግሞ አዲሱ የዓለም መንግስት የተመሰረተበት ህግ ወይም መልክና ምሳሌ ነው። በተቀደሰችው ምድር በኢትዮጵያ ላይ ይነግስ ዘንድ ያለውም የአህዛብ የስጋ ማንነትና ምንነት በዚህ መልክና ምሳሌ የሚገልጽ ነበር። አንድ ወንድ እንኳን በምድሪቱ ውስጥ ስላልነበረ ያ የስጋ ማንነትና ምንነት በሴቲቱ መልክና ምሳሌ በኩል በመንግስቱ ዙፋን ላይ ሊነግስ የከለከለው አልነበረም።
በግራኝ አብዮት አህመድ በኩልም እየተለጸ ያለው ይህ የስጋ ማንነት እና ምንነት ነው። “ገና በሰባት ዓመቴ እናቴ ንጉሥ ትሆናለህ ብላኝ ነበር” እያለ ሲሽለመጠመጥ ነበር ፥ ከፕሬዚደንቷ እስከ ሰላም ሚንስትሯ ድረስ ቀጣፊ ሴቶችን በብዛት ማንገሱ ያን ለአህዛብ የተሰጠ የዲያብሎስ የስጋ ማንነትና ምንነት በራሱ ላይ አንግሶ የመጣ የእግዚአብሔር ቀንደኛ ጠላት ስለሆነ ነው። ይህን በሃጋር፣ በእስማኤል፣ በግራኝ አህመድ ቀዳማዊ፣ በአፄ ምኒሊክ፣ በእቴጌ ጣይቱ ብጡል፣ በአፄ ኃይለ ሥላሴ፣ በመንግስቱ ኃይለማርያም እና በኃይለማርያም ደሳለኝ ላይ የነገሰውን የዲያብሎስ የስጋ ማንነትን እና ምንነት በራሱ ላይ በማንገስ ነው ዛሬ ግራኝ አብዮት አህመድ በአክሱም ጽዮን ላይ ለመዝመት የደፈረው።
ጻድቁ አባታችን አባ ዓቢየ እግዚእ ‘በሚኖሩበት‘ በማርያም ታምባ ተንቤን ዙሪያ፡ ይህን በምጽፍበት ወቅት፡ የውጊያ አውሮፕላኖች ብዙ ድብደባዎች በማካሄድ ላይ መሆኑ በክርስቶስ ተቃዋሚነቱ እና በፀረ–ተዋሕዶ አቋሙ ምን ያህል እርቀት እንደሄደ ነው የሚያሳያን። ይህን እያዩ ከዚህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ጎን የተሰለፉ “ኢትዮጵያውያን ነን፣ ተዋሕዶ ነን” የሚሉ ከንቱ ግብዞች ሁሉ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች እና የኢትዮጵያም ጠላቶች ስለሆኑ አብቅቶላቸዋል፣ ወደ ጥልቁ እየፈረጠጡ ያሉ ሰው–መሰል የሰይጣን ፈረሶችና የሳጥናኤል ባሪያዎች ሆነዋል።
ይህ የእባብነት ቆዳ ቀይሮ በመምጣት በቅድስት ኢትዮጵያ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አዲሱን የሉሲፈርን የዓለም መንግስት ለመመስረትና ሕዝቡንም ሊገዛ የተገሰለ ቆሻሻ፣ ጨካኝ፣ አላጋጭ የዲያብሎስ የግብር ልጅ ክፉ አሟሟትን እንደሚሞታት ምንም ጥርጥር የለኝም።
👉 ❖❖❖ አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)❖❖❖

አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በ፲፬/14ኛው መቶ ክ/ዘመን ትግራይ ተንቤን (መረታ) ውስጥ ነው። የተባረኩ ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ። አጥምቀው ‘ዓቢየ እግዚእ’ ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ዻዻስ ሰላማ መተርጉመ መጻሕፍት ናቸው። ትርጉሙም “በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው” ማለት ነው።
+ ዓቢየ እግዚእ በሕጻንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቁ። ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኮስ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደብረ በንኮል ሔደው መንኩሰዋል።
+ በገዳሙ በጾም: በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያን አግኝተዋል። በጊዜው በ፵/40 ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ ይበሉ ነበር።
+ ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን አፍርተዋል። ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ
አባትም ነበሩ። ከትግራይ እስከ ደንቢያ ደግሞ ሃገረ ስብከታቸው ነው።
+ አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ። ቀኑ ነሐሴ ፲/10 ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለ፫ ቀናት ባለመጉደሉ ከ፩ሺህ በላይ
ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ። ጻድቁ ባካባቢው የነበሩት ኢ-አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና “አምላከ ሙሴ” ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ።
+ ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ። ይሕን ድንቅ ያዩ ከ ፩/1ሺህ በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል። ይሕም ዘወትር ነሐሴ ፲/10 ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው(ጐንደር)ይከበራል።
+ ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ። ያኔ ጐንደር በቀሃና አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች። ጻድቁ ቀን ቀን እየሰበኩ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር።
+ በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ: እባብና መሠል አራዊት ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት። ይሕንን የተመለከቱት አባ ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ። በፍጹም ልባቸውም ስለ ሕዝቡ ለመኑ።
+ የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ “በስምሕ የተማጸኑ: በቃል ኪዳንህ ያመኑ: በምድር አራዊት አይሠለጥኑባቸውም።
በሰማይም እሳትን አያዩም። ጐንደርንም አራዊት ገብተው ሰውን አይጐዱም።” ብሏቸው አርጓል።
+ ጻድቁም የወንጌል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ ገዳማቸው ተንቤን ተመልሰዋል። ይሔው እኛ ምን ብንከፋ: ጻድቁንም ብንረሳቸው እግዚአብሔር ግን ዛሬም በጻድቁ ምልጃ ከተማዋን ጠብቆ
ይኖራል። ነገን ደግሞ እርሱ ያውቃል። ዛሬ ቤተ ክርስቲያኑ የታነጸበት ቦታ (ጎንደር ቀበሌ 09 ኪዳነ ምሕረት) ጻድቁ የጸለዩበት ቦታ ነው። እንኳን በወርሃዊ በዓላቸው (በ፲፱/19) ይቅርና ዓመታዊ በዓላቸው (ግንቦት ፲፱/19) ለንግስ የሚመጣው
ሰው ቁጥር ያስተዛዝባል።
+ አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት በቅድስና ኑረው: ፫ ሙታንን አስነስተው: ብዙ ድውያንን ፈውሰው: ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው: የድኅነት ቃል ኪዳንም ተቀብለው: በ፻፵/140 ዓመታቸው ግንቦት ፲፱/19 ቀን አርፈዋል።
የጻድቁ ክብር ለሁሉ ነውና እባካችሁ እናስባቸው።
+ ተአምሪሁ ለጻድቅ አቡነ ዓቢየ እግዚእ – – – ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም። አሜን።
👉 ❖❖❖ ከበዙ ተአምራቱ አንዱን ❖❖❖

ጻድቁ አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው #ተንቤን (መረታ) ሳሉ አንዲት መበለት መጥታ “አባቴ! የምጠጣውን ጸበል ባርከህ ስጠኝ?” አለቻቸው። ጻድቁም በውሃው ላይ ጸሎትን አድርሰው: በመስቀላቸው ባርከው ሰጧት።
+ ወደ ባልንጀራዋ ስትደርስ ግን ሐሳቧን ቀየረችና “ልጠጣው” ብላ የተቀበለችውን ማይ (ጸበል)
ልትጠመቅበት (ልትጸበልበት) ወሰነች። ባልንጀራዋንም “በላዬ ላይ አፍሺልኝ” ስትል አዘዘቻት።
+ ባልንጀራዋም “እሺ” ብላ ልታፈስላት (ልትጸብላት) በፋጋ(ግማሽ ቅል) ያለውን ጸበል አነሳች። ልታፈሰው ስትዘቀዝቀው ግን ከሆነው ነገር የተነሳ 2ቱም ደነገጡ። ጸበሉ የረጋ ደም ወደ መሆን በቅጽበት ተለውጧልና።
+ ፍጹም ፍርሃት የወደቀባቸው ሴቶቹ እየተሯሯጡ ወደ አባ ዓቢየ እግዚእ በዓት ደረሱ። ከውጭ ሆነውም “አባ! አባ! የሰጠኸን ጸበልኮ የረጋ ደም ሆነ” አሏቸው። ጻድቁም እንዳላዋቂ “ምን አጠፋችሁ?” ሲሉ ጠየቁ።
+ “አባታችን! ምንም አላጠፋንም። ብቻ አፍሺልኝ ብየ ስሰጣት እንዲህ ሆነ” ስትል አንዷ መለሰች። ጻድቁ ግን በየውሃት “ልጆቼ! ሁሌም : ‘ምንም አላጠፋንም‘አይባልም። ሰው ሆኖ የማይበድል የለምና።
+ . . . አንቺም ልጄ! እኔን ያልሺኝ ‘የምጠጣው ጸበል ስጠኝ‘ ነበር። ግን ልትጸበይበት ወደድሽ። ስሕተትሽ ከዚህ ይጀምራል። (የቅዳሴ ጸበል ለመጸበል አይሆንምና)
¤ በዚያ ላይ “አልቦ ዓቢይ ኃጢአት ከመ ወልጦ ቃል . . .ከውሸት በላይ ከባድ ኃጢአት የለም።” [ዮሐ. ፰:፵፬]
+ . . . በተጨማሪ ደግሞ ያለ ስልጣኗ እህትሽን ‘አጥምቂኝ‘ አልሻት። ስለነዚህ ነገሮች ጸበሉ ተለውጦባቹሃል” ብለው ወደ ጸበሉ በመስቀል አማተቡ። “እፍ” ሲሉትም የረጋ ደም የነበረው ማይ ወደ ጸበልነቱ ተመለሰ። ይህንን ያዩ ሴቶቹ በግንባራቸው ተደፍተው ለጻድቁ ሰገዱ።
👉 ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም። አሜን።
❖ አምላካችን በወዳጆቹ ምልጃ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይሠውርልን።
__________________________
Leave a Reply