Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • December 2020
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ማንን ለመምታት ነው ወደ ሰማይ ጥይት የተኮሳችሁት? ለየትኛው ድል? ለማን ሠራዊት?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 7, 2020

👉 ጦርነት እና ሰላም

ጦርነቱ የተጀመረው እኮ ኦርቶዶክሳውያንን እርስበርሱ አጋጭቶ፤ በትግራይ እና አማራ ክልሎች የሚገኙትን ኦርቶዶክሳውያንን ሆድ እና ጀርባ ለማድረግ ነው፤ ደግሞ ተሳክቶላቸዋል።

☆ “ክፉ ትውልድ ደረቅ ሴትን ይመስላል፤ እግዚአብሔርን “ቅሰፈኝ!” ይለዋል”

በጦር አንደበት፣ በፈረስ ጉልበት ያሸነፍን ይመስል ሙሉ አማራ ክልል እንዲህ ሲጨስ ያደረ ለምንድን ነው? በሰንበት ምድር ሰው ማሕሌትና ቅዳሴ ይስማ ወይስ የእነሱን ጥይት ይስማ? እያንዳንዷ የቀልሃ ጠብታ አንድ ቀን ትጠማዋለች። ፈጽሞ የሚያሳዝን፣ የሚያሳፍር ነገር ነበር።

ዛሬ እኮ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ ተብሎ የተከለለው ክልል ጣልያን የከለለው እንጂ እንዲህ የሚባል ክልል እኛ አናውቅም፤ ጠላት ያሰመርልን ክልል አንቀበልም። እኛ የምናውቀው አንዲ አገር፤ ከዚያ ባለፈ ክፍለ ሃገር ነው የምናውቀው፤ በጌምድር፣ ጎጃም፣ ትግራይ፣ ወሎ፣ ሸዋ፣ ወለጋ፣ አርሲ፣ ሲዳሞ፣ ሐረርጌ፣ ኢሉባቡር፣ ጋሞጎፋ የሚባሉትን ክፍለ ሃገራት ብቻ ነው።

ፖሊስ ሌባ እያባረረ ወደላይ ቢተኩስ ለማስፈራራት ነው፤ ተኩሶ ላለመምታት ነው፤ ግን በባዶ ሜዳ ለደስታ ተብሎ ጥይት ወደ ሰማይ የሚተኮሰው ወደ ሰማይ ያለው ማን ነው? እግዚአብሔር አይደልን? ማንን ፍለጋ ነው ወደ ሰማይ የምንተኩሰው? ይህ እኮ ባቢሎናውያኑ የነ ናምሩድ የነ ሰናኦር ሥራ ነው፤ ኑ እግዚአብሔርን እንውጋው! ወደ ሰማይ ጦር ይወረውሩ የነበሩ እነርሱ ናቸው። እንዴት አንድ አማኝ ክርስቲያን ቁጭ ብሎ ወደ ሰማይ ጥይት ይተኩሳል? ለስድስት ሰዓት ሙሉ እንዴት ጥይት በከንቱ ያለማባራት ወደ ሰማይ ይተኮሳል። በገንዘብ ደረጃ እንኳን ሲታሰብ እያንዳንዱ ጥይት በሚሊየን ብር ዋጋ ያወጣል፤ በዚህ እንኳን ብልጠት የለም። ሲጀመር እኮ ጦርነቱ ተጀመረ እንጂ አላለቀም፤ መቀሌን ለመቆጣጥር? መቀሌ እኮ የጠላት ከተማ አይደለችም የእኛው ናት፤ አስመራን፣ ካርቱምን ወይ ናይሮቢን አይደለም እኮ የያዝነው። እኛ የያዝነው እኮ የገዛ ከተማችንን ነው፤ እዚያም ያሉት እኮ ወገኖቻችን ናቸው፤ ምኑ ነው ተዓምሩ? ለመሆኑ እስካሁን በተደረገው ጦርነት ስንት ወገን የሞተ ይመስላችኋል? ስንት ተዋጊ፣ ስንት ንጹሐን ተገድለዋል? ቀላል አይደለም! እንደው የሰውን ጨለማ ልብ፣ የሰውን አለማስተዋል ለመግለጥ ቃል ያጥረኛል። እነርሱ እንደሚሉት እሺ ቲፒኤልኤፍ ጠፋች፤ ግን ተውትና መንግስት ጡጦ የሚያጠባው የእሷ ትንሽ ወንድሟ ኦነግ አለ አይደለም እንዴ?! ኧረ ኦነግንም ተውት፤ እራሱ ብልጽግና ብሎ የሚጠራው ፓርቲ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ወዳጅ ይመስላችኋልን? ዋናው ጠላት እሱ አይደለ እንዴ!

ደግሞ እኮ “ቅዱስ ገብርኤል ነው በዕለተ ቀኑ ለድል ያበቃን!” እያሉ በየፌስቡኩ በመለቅለቅ ሊቀ መላዕክቱን የእነርሱ ወራዳ ሥራ ተሳታፊ ያደርጉታል፤ እንዴ ምኑን ከምኑ ነው የሚያገናኙት? ቅዱስ ገብርኤል ነው እንዴ ጦርነቱን ያስጀመረው? ሠራዊቱ ገብርኤል እርዳኝ እያለ ነው የተዋጋው? እንደው ያሳዝናል፤ “ክፉ ትውልድ ደረቅ ሴትን ይመስላል” እንዲሉ ይህ ክፉ ትውልድ እግዚአብሔርን “ቅሰፈኝ” ይለዋል።

ለመሆኑ የጦርነቱ ዓላማ ቤተ ክርስቲያንን ለማገዝ ነው? እኛ “ቲፒኤልኤፍ ትጥፋ ከተጀመረ ላይቀር” አልን እንጅ ጦርነቱ የተጀመረው እኮ ኦርቶዶክሳውያንን እርስበርሱ አጋጭቶ፤ በትግራይ እና አማራ ክልሎች የሚገኙትን ኦርቶዶክሳውያንን ሆድ እና ጀርባ ለማድረግ ነው፤ ደግሞ ተሳክቶላቸዋል።

ወገን፤ ወታደር አያድንም፣ መከላከያ ሰራዊት አያድንም፣ ፋኖ አያድንም፣ ሚሊሺያ አያድንም፣ ልዩ ኃይል አያድንም፣ የሚያድን መድኃኔ ዓለም ብቻ ነው።

ቃለ ሕይወት ያሰማልን፤ መምህር ዮርዳኖስ! አስተዋይ ወገን አያሳጣን! “አባት፣ መምህር፣ ሊቅ” የተባለ ሁሉ ስንቱ ልሂቃን ከንቱ ነገር እየተናገረ፣ ከንቱ እንደሆነ፣ የተሳሳቱ ምልክቶችን እያሳየና ስጋዊ የሆኑ መል ዕክቶችን እያስተላለፉ እንደሆነ እያየንና እያዘንን ነው።

__________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: