***“እንደ ዝንቦች እንጠፋለን!!!”***
“የሌኒንግራድ እገዳ” በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ በጣም ግልጽና ኢ-ሰብዓዊ ከሆኑት የጦር ወንጀሎች አንዱ ነው።
☆ እ.አ.አ መስከረም ፲፱፻፵፪/1942 – ነሐሴ ፲፱፻፵፬/1944 ዓ.ም – የሌኒንግራድ ከተማ እገታ
👉 ሂትለር እራሱ እገዳውን አዘዘ
👉 ከተማዋ ዙሪያዋን ተከበበች፣ መውጫና መግቢያ መንገዶች ተዘጉ
👉 ለ ፪.፭/ 2.5 ሚሊዮን የከተማዋ ነዋሪዎች ምግብ፣ ውሃ፣ መብራትና ስልክ ማቅረብ አቆመ
👉 የሌኒንግራደሮች የጭካኔ ረሃብ የስሌቱ አካል ነበር
👉 ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሞቱ
👉 ከተማዋን ግን መያዝ አልቻለም፤ ሂትለር ተሸነፈ
ከሰማንያ ዓመታት በፊት ዛሬ ሳንትፒተርስቡርግ በመባል የምትታወቀውን እና የሩሲያን ሁለተኛ አንጋፋ ከተማን ሌኒንግራድን (የፕሬዚደንት ፑቲን ከተማ) በሁሉም መንገድ ለመያዝ ባላቸው ፍላጎት ሂትለርና የናዚ ጀርመን አመራሮቹ እጅግ ኢ-ሰብዓዊ የሆኑ የትግል ዘዴዎችን ከመጠቀም አልተገደቡም፡፡ ሂትለር ከተማዋን ሙሉ ለሙሉ ለማውደም ፣ 2.5 ሚሊየን የሚሆነውን መላውን ህዝቧን ለማጥፋት ፣ በረሃብ ለመቅጣትና እና የተከላካዮችን ተቃውሞ ለማፈን በከፍተኛ የአየር እና በጦር መሳሪያዎች ደጋግሞ መትቷታል፡፡ ከተማዋ በእግድ ተከበባ ነበር ፡፡ ተከላካዮች እና የተቀረው የሌኒንግራድ ህዝብ በተከታታይ የቦምብ ፍንዳታ ተፈጽሞባቸው ፣ ረሃብ ፣ ብርድ እና በሽታ አጥቅተዋቸው እንኳን የጠላትን ጥቃት በጀግንነት እስከ መጨረሻው ተከላክለውት ነበር ፤ ቦምብ፣ ረሃብ፣ በሽታ እና ብርድ ሌኒንግራሮችን አልሰበሯቸውም ነበር።
ናዚዎች የሌኒንግራድ መያዙን ከዋና ዋና ስልታዊ እና ፖለቲካዊ ግቦች አፈፃፀም ጋር ያያይዙታል፡፡ እነሱ ይህችን ከተማ እና ህዝቧንም ከምድር ገጽ ለማጥፋት አስበው ነበር፡፡
በሌኒንግራድ የተደረገው ውጊያ በታላቁ የአርበኞች ጦርነት ወቅት በጣም ረዥም ነበር ፡፡ የፋሺስት ጀርመን ወታደራዊ-የፖለቲካ አመራር ሌኒንግራድ ከጥቃት ወረራው የመጀመሪያ ዒላማዎች እንደ አንዱ አደረገው፡፡ ነገር ግን በሌኒንግራድ ለ 900 ቀናት በመከላካይ ጦርነት ወቅት የሩሲያ/ሶቬይት ወታደሮች ከተማዋን ለጠላት አሳልፈው አልሰጡም ፣ በርካታ የጠላት ኃይሎችን እና ከናዚዎች ጋር አብሮ የነበረውን መላውን የፊንላንድ ጦር ድል አድርገዋቸው ነበር፡፡ እና የሌኒንግራድ መከላከያ የሩሲያ/ሶቪዬት ህዝብ እና የመከላከያ ሰራዊታቸው ድፍረት እና ጀግንነት ምልክት ለመሆን በቅቷል፡፡ ናዚዎች ሌኒንግራድን ሙሉ በሙሉ ለመያዝ ባለመቻላቸው ከተማዋን በጭካኔ የቦምብ ፍንዳታ እና ድብደባ በመምታት ህዝቡን እና ተከላካዮችን በረሃብ እና በብርድ ቀጥተው ለማንበርከክ ሞክረው ነበር፡፡
የጀርመን ወታደሮች ሌኒንግራድን የማጥቃት ዘመቻ የተጀመረው እ.ኤ.አ. ሐምሌ 10 ቀን 1941 ዓ.ም ነበር፡፡ በዚህ ቀን የጀርመን እና የፊንላንድ ወታደሮች በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን አቅጣጫዎች ከተማዋን ለማጥቃት ዘመቱ፡፡
የጀርመን ትዕዛዝ ሌኒንግራድን በትንሽ ደም በመውሰድ በቁጥጥር ስር ለማዋል እና የሞስኮ ቡድን ሰሜን ኃይሎችን በሞስኮ ላይ ለማጥቃት ዓላማው ሳይሳካ ቀርቷል ፡ ስለዚህ እስክ 1944 ዓ.ም ድረስ ሌኒንግራድን ለዘጠኝ መቶ ቀናት (ለሁለት ዓመታት ተኩል ያህል) በናዚ ወታደሮች ታግዳና ተከብባ እንድትቆይ ተደርጎ ነበር። የተከበበችው ከተማ ሁኔታ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነበር፡፡ የጋራ ሥርዓቶቹ ሁሉ አልሠሩም፡፡ ከተማዋ መብራት፣ ስልክ፣ ሙቀትና የውሃ አቅርቦት ተነፍጓት ነበር፡፡ የኃይል አቅርቦቱ ውስን ነበር፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ ህዝቡ እንዳለ ታግቶ ነበር፤ አልተለቀቀም፤ ስለዚህ በአስቸጋሪ ቀዝቃዛ ክረምት እና በቂ አቅርቦቶች በሌሉበት ሁኔታ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ ተጋለጡ፡፡ በእገዳው ጊዜ ሁሉ የነዋሪዎችን መፈናቀል በዋነኝነት ሕፃናትን ነበር ያጠቃው፡፡ ሆኖም በላዶጋ ሐይቅ በኩል “ከዋናው ምድር” ጋር የተከበበውን ብቻ የሚያገናኝበት ብቸኛው መንገድ “የሕይወት ጎዳናዎች” ውስን ነበሩ፡፡
ግማሽ ሚሊየን ሰዎች ፣ ብዛት ያላቸው የኢንዱስትሪ መሣሪያዎች ፣ ባህላዊ እሴቶች እና ሌሎች ንብረቶች ከከተማው ተወስደዋል ፡፡ በአጠቃላይ የሥራ ዘመኑ ከ 1.6 ሚሊዮን ቶን በላይ ጭነት በ “የሕይወት ጎዳና” ተጓጉዞ ወደ 1.4 ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ተደርጓል፡፡
በረሃብ ፣ በብርድ ፣ በበሽታ፣ በቦምብ እና በከባድ ድብደባ ምክንያት የሞቱት የሌኒንግራድ ከተማ ነዋሪዎች ጠቅላላ ቁጥር ፩/1 ሚሊዮን ሰዎች ደርሶ ነበር።

ግራኝ አብዮ አህመድ አሊ በመፈንቅለ ክልል ጀብዱው እነ ጄነራል አሳምነውን የአማራ ክልል ከተሰኘው ክፍለ ሃገር ገድሎ ካስወገደ በኋላ በጋላዎች የሚመራውን የጋላማራ አገዛዝ በክልሉ አስቀመጠ፣ ባስፈለገ ጊዜ ፊሽካ ተነፍቶ በክልሉ ስም ለዘመቻ የሚጠራውን “የአማራ ልዩ ሃይል” አደራጀ፣ አሁን በወለጋ በሚኖሩት አማራዎች ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ባደረገ ማግስት፤ “ና! ወደ ትግራይ ልንዘምት ነው፣ ወልቃይት እርስትህን ነፃ ታወጣለህ!” ተብሎ እንዲወጣና የእሳት እራት እንዲሆን አደረገው። ጎን ለጎን፤ በቤኒሻንጉል እና ኦሮሚያ ህገ-ወጥ ክልሎች አማራዎች ላይ ጭፍጨፋውን ቀጠለ፤ በሉሲፈራውያኑ ልሂቃኑ የሚመራውና “አማራ” ሳይሆን “አማራ ነኝ” እያለ እራሱን ለመከላከል ብቃት ያለው መንጋ ግን የጎጃምን ግዛቱን (እርስቱን) ከቤኒሻንጉል እና ኦሮሚያ አስመልሶ የሕዳሴ ግድቡን ለመቆጣጠር ከመታገል ይልቅ በትግሬ ወገኑ ላይ ካለው ጥላቻ የተነሳ በርሃማዋን “ወልቃይት እርስቴን ላስመለስ” በሚል ወኔ ለጋላዎች ሤራ እራሱን አሳልፎ በመስጠት እራሱን በእሳት ያስጠርጋል። በዚህም እርስቱንም፣ ወኔውንም ማንነቱንም ሁሉ ይነጠቃል! “….ሰዎች ጥቅም ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸው…የሚፈልጉትን እያሳየህ ወደምትፈልገው ስፍራ ውሰድ እና ጣላቸው… ከዚያም በሬ ሆይ! ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ… ብለህ ተርትባቸው” ብሎህ ነበር እኮ የዘመትክለት እባቡ አብይ።

በዘመነ ኮሮና፣ በዘመነ አንበጣ፤ ግራኝ አብዮ አህመድ በትግራይ ኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመው ያለው ጭካኔ የተሞላበት ፋሺስታዊ ተግባር ናዚው ሂትለር ከሰማኒያ ዓመታት በፊት በሩሲያውያኑ ላይ ከፈጸመው ኢ-ሰብዓዊ ተግባር ጋር እጅግ በጣም ተመሳሳይ ነው። ልብ እንበል፤ ግራኝ ትግራይን ማገድ፣ መተንኮስ፣ ለወረርሽኝ በሽታ፣ ለአንበጣ፣ ለረሃብ ማጋለጡን የጀመረው ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት ነበር። የሂትለርን ፍኖተ ካርታ ይዞ ነው ጥቃቱን በማካሄድ ላይ ያለው።
ትናንትና የመቀሌ ዩኒቨርስቲን አጥቅቶ ብዙ ተማሪዎችን መጉዳቱ ተሰምቷል። እነዚህ ጭፍጨፋዎች ተገቢውን ዓለም አቀፋዊ ትኩረት እንዳያገኙ፤ እንደ ዘላን ተዋጊ ዛሬ ወደ ሰሜን ነገ ወደ ደቡብ፣ ምስራቅና ምዕራብ እየተዘዋወረ ለኦሮሙማ ፕሮጀክቱ ጭፍጨፋዎችን “በብልጠት” ይቀጥላል። በወለጋ ጨፈጨፈ ፥ ዓለም ለጭካኔው ትኩረት ማሳየት ስትጀምር ወደ ሰሜን ዞረ፣ የሰሜኑ ጭፍጨፋና የስደተኞች መብዛት የዓለም አቀፉን ትኩረት ማግኘት ሲጀምር ወደ ምዕራብና ደቡብ ዞሮ በቤኒሻንጉል እና ኦሮሚያ ሌላ አሰቃቂ ጭፍጨፋ እንዲካሄድ አደረገ። ታዲያ ይህ ዲያብሎስን የሚያስንቅ አረመኔያዊ ተግባር አይደለምን?! የናዚዎች ጭካኔ እንዲገታ ሂትለር መገደል ነበረበት፤ በሃገራችንም የሕዝባን ስቃይ እና ሰቆቃ እንዲቆም ግራኝ አብዮት አህመድ ባፋጣኝ መጠረግ አለበት።
__________________________