Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • November 2020
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    30  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for November 12th, 2020

የሕንድ TV | ኦሮሞዎች በትግሬዎች ላይ ጦርነት ከፍተዋል | አብይ የጦር ወንጀለኛ ነው!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 12, 2020

ጋዜጠኛዋ፦ አቢይ ባለፈው ዓመት የኖቤል ሽልማት ተሸለመ፤ ዛሬ በገዛ ወገኖቹ ላይ የአየር ድብደባዎችን እያደረገ ነው፤ በእሱ አመራር ኢትዮጵያ በእርስ በእርስ ጦርነት አፋፍ ላይ ቆማለች።

አስከፊ ወንጀሎችን በመፈፀም ወይም በመከላከል ከደፈሩ የኖቤል ተሸላሚዎች ዝርዝር ውስጥ ይህን ጠቅላይ ሚኒስተር ማከል ይችላሉ።

👉 “You can add this prime minster to the list of nobel laureates who ended up committing or defending unspeakable crimes።”

ጋዜጠኛው በመጨረሻ፦ “በትግራይ ላይ የተከፈተው ጦርነት ሊቆም የሚችለው የትግራይ ሕዝብ ለአብይ አህመድ እጁን ሲሰጥ ብቻ ይመስላል።” ዋው!

ግራኝ አብዮት አህመድ ከመንግስቱ ኃይለ ማርያም የከፋና መሰቀል ወይም መረሸን ያለበት የጦር ወንጀለኛ ነው። 100%

ዋው! ህንዶቹ ከአብዛኛው ኢትዮጵያዊ በተሻለ መልክ ታዝበዋል! ያስገርማል! ፩.፫ ቢሊየን የሕዝብ ቁጥር ያላትና በ፴/30 ግዛቶች የተከፈለችው ሕንድ ፯፻፭/705 ብሔሮች እና ፯፻፹/780 ቋንቋዎች አሏት። ከፓፕዋ ኒው ጊኒያ (፰፻፴፪ /832 ቋንቋዎች)ቀጥሎ በዓለም ብዙ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሃገር ናት። ሁለቱም ሃገራት የጎሳ/ነገድ/ብሔር ጦርነት አይተው አያውቁም፤ ምክኒያቱ ከደቡብ ሕንድ በቀር አብዛኛው ዜጋ ክርስቲያን ስላልሆነ ዲያብሎስ ለጭፍጨፋ አይፈልገውምና ነው። ዲያብሎስ ጦርነቱን በጥንታውያኑ ክርስቲያን ሕዝቦች ላይ ነው ያወጀው፤ በደቡብ ሕንድ/ኬረላ ግዛት ኦርቶዶክስ ወገኖቻችንም ላይ።

የህንዶቹ ጋዜጠኞች ትክክል ናቸው፤ ጋሎቹ በሰሜን ኢትዮጵያውያን ላይ ነው ጦርነት እያካሄዱ ያሉት፤ አማራውን አድክመነዋል እንውጠዋለን እንሰልቅጠዋለን ብለው ስለሚያስቡ፤ ባፋጣኝ በትግሬ ኢትዮጵያውያን ላይ ዘመቱ። ይህ ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት በግራኝ ቀዳማዊ ዘመን፣ ቀጥሎ ከመቶ ሃምሳ ዓመት በፊት በጋላ ወረራ ዘመን፣ በደርግ ዘመን እና ዛሬ የተካሄደና የሚካሄድ ነው። ከሰማይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም።

እኔ እርግጠኛ ነኝ ኢትዮጵያዊ የተዋሕዶ ጀግና አፄ ዮሐንስ ዛሬ ቢኖሩ ኖሮና ህወሀቶች የያዙትን ሠራዊትና ትጥቅ ብዛትና ጥንካሬ ቢኖራቸው፡ ዛሬ ጦርነቱ በታሪካዊቷ የኢትዮጵያ ክፍለ ሃገር በትግራይ ሳይሆን ኦሮሞ እና ሶማሊያ በተባሉት ህገ-ወጥ የወራሪዎች ክልሎች ነበር የሚያካሂዱት፤ እርግጠኛ ነኝ፤ ኢሳያስ አፈቆርኪን ጨምሮ እነዚህን የኢትዮጵያ እና አምላኳ ጠላቶችን ከሃገራችን ብቻ ሳይሆን ከሶማሊያ እና ሱዳንም ጠራርገው ባስወጧቸው ነበር። የህወሃትን የቻይና ድሪቶ ሳይሆን ክቡሩን ሰንደቃችንን የሚይዙት ዳግማዊ አፄ ዮሐንስ በቅርቡ መነሳታቸው አይቀርም።

👉 ግራኝ ከጻፈበት የሕንድ ቲቪ ቻነል ገጽ የተመረጡ አስተያየቶች፦

👉 Nobel peace prize winner is the contrary to the prize. Is like this prize is cult to start killing innocent people. Shame shame killer of civilians. Ethiopia I use to think you were better but no.

👉 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ከሽልማቱ ተቃራኒ ነው፡፡ ልክ ይህ ሽልማት ንፁሃንን መግደል ለመጀመር አምልኮ ነው፡፡ አሳፋሪ አሳፋሪ ገዳዮች ፡፡ ኢትዮጵያ እኔ የተሻልሽ ትመስይኝ ነበር ግን አይደለሽም፡፡

👉 Obama after nobel prize destroyed libya, syria, ukraine etc

👉 ኦባማ ከኖቤል ሽልማት በኋላ ሊቢያ ፣ ሲሪያ ፣ ዩክሬን ወዘተ አጠፋቸው!

👉 Abiy Ahmed is the first Nobel peace laurate to wage war against his own people and reject peace talk. It’s time to remove his name from the Nobel peace laurate list.

👉 ከራሱ ህዝብ ጋር ጦርነት በመክፈት የመጀመሪያው የኖቤል ሰላም ተሸላሚ አብይ አህመድ ብቻ ነው፡፡ ከኖቤል የሰላም ተሸላሚዎች ዝርዝር ውስጥ ስሙን ለማስወገድ ጊዜው አሁን ነው፡፡

👉 Just a normal day in an Islamic country

👉 ይህ በእስላማዊት ሀገር ውስጥ እንደ አንድ መደበኛ ቀን ነው

👉 ይህ የበሻሻ ቆሻሻ የመረጃ ጦርነቱን በጣም ይፈራዋል። ይህን ቪዲዮ አስመልክቶ ግራኝ አብዮት አህመድ በአስተያየት መልክ ለሕንዱ ቴሌቪዥን ተበሳጭቶ የጻፈው፦

_________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ደርግ 2.0 | የተባበሩት መንግስታት ወደ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ወሳኝ ሰብአዊ ዕርዳታ ለመውሰድ ‘ምንም መንገድ’ የለም”፤ በማለት አስጠነቀቀ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 12, 2020

የስልክ መስመሮች እና የትራንስፖርት አገናኞች አሁንም በመቋረጣቸው የሰብአዊ ድጋፍ አድራጊዎች ወደ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል አስፈላጊ አቅርቦቶችን ማቅርብ ወይም ወይም የሰብአዊ ፍላጎቶችን መገምገም እንደማይቻል የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

No Way’ to Get Vital Humanitarian Aid into Ethiopia’s Tigray Region, UN Warns

With telephone lines still cut and transport links disrupted, it is impossible for humanitarians to get vital supplies into Ethiopia’s Tigray region or assess evolving humanitarian needs, the UN Office for the Coordination of Humanitarian Affairs (OCHA) has said.

👉 UN Says 11,000 Have Fled Ethiopia to Sudan, 50% of Them Children

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 11,000 ኢትዮጵያን ጥለው ወደ ሱዳን መሰደዳቸውን የገለጸ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 50% የሚሆኑት ህጻናት ናቸው

___________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በጽዮን ቀንደኛ ጠላት ሳውዲ አረቢያ ኃይለኛ ዝናብ፣ በረዶና መብረቅ ቀንደኛውን ሰይጣንን ገለጡት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 12, 2020

በረዶው ጉድ ነው፤ በአውሮፓ እንኳን የለም! መካ በመብረቅ ጋጋታ ተናወጠች! ሰይጣንም በጥቁሩ ድንጋይ፣ በመኪና ተገለጠ!

ባቢሎን ሳውዲ አረቢያ ግራኝ ወኪሏን በጽዮን ተራሮች ላይ ቦምብ እንዲጥል አዘዘች፤ እግዚአብሔር አምላክ ቁጣውን በመብረቅ፣ በረዶና ጎርፍ ገለጠ!

👉 የለም ብለን ጠፋን

በእባብ ተገለጠ የለም ሲሉት ሰይጣን፣

ፍሬውን አብልቶ በሞቱ ሲያስቀጣን፤

ስጋ ለብሶ ታየ የለም ሲሉት ጌታን።

በመስቀል ላይ ሞቶ ቤዛ ሆነ ላለም፤

ደሞም ይኸዉ በኛ መሀል ሰይጣን፤

ሰዉን ከሰዉ ሲያጋጭ በተሰጠው ስልጣን።

ይኸውና እግዜሩ ሰው ከሰው ሲያስማማ፤

አይን አይቶ ልብ ቢል ጆሮአችን ቢሰማ።

እንዲህ ሆኖ ሳለ ቅርብ ሆኖ እውነቱ፤

እሩቅ መንገድ ለፋን አለ ብለን ሳንኖር።

የለም ብለን ጠፋን፤

የለም የሚል ሀሳብ ከአለ ቃል ተወልዶ፤

ማስተዋል ያቃተው በቅንነት ረሀብ ሩቅ ሀገር ሄዶ።

በክህደት ሲከሳ በ እምነት አይሰባም፤

በዚህ አያያዙ እንኳንስ ከገነት ፵ አመት ተጉዞ ከነአን አይገባም።

_____________________

[መጽሐፈ ኢዮብ ምዕራፍ ፴፰]

፳፪ በውኑ ወደ በረዶው ቤተ መዛግብት ገብተሃልን?

፳፫ ይኸውም ለመከራ ጊዜ ለሰልፍና ለጦርነት ቀን የጠበቅሁት ነው።

፴፫ የሰማይን ሥርዓት ታውቃለህን?

፴፬ የውኆች ብዛት ይሸፍንህ ዘንድ

፴፭ መብረቆች ሄደው። እነሆ፥ እዚህ አለን ይሉህ ዘንድ

፴፮ በውስጡስ ጥበብን ያኖረ፥

፴፯፤፴፰ የሰማይን ደመና በጥበቡ ሊቈጥር የሚችል ማን ነው?

፴፱፤፵ በዋሾቻቸው ውስጥ ተጋድመው፥

፵፩ ልጆቹ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ

ሙሉው ምዕራፍ ይነበብ!

_________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኢንተርኔት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቋረጠ | ጽዮንን አትንኳት፣ አትዳፈሯት፣ አትፈታተኗት!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 12, 2020

ማታ ላይ በብዙ አገራት ኢንተርኔት ብልጭ ድርግም ይል ነበር። ዩቲውብን እና ትዊተርን የመሳሰሉት የማሕበራዊ ድሕረ ገጾች ሙሉ በሙሉ ወርደው ነበር።

ኢንተርኔት ይህን የመሰለ ጉንፋን ሲይዘው ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው። ኮሮና? ይህ ጅምሩ ነው፤ የሙቀት መለኪያው ነው!

አውሬው ኢንተርኔትና ስልክን ዘግቶ ወገኖቻችን ይጨፈጭፋል፤ አንተ ሶፋ ላይ ቁጭ ብለህ “በለው! ጨፍጭፈው! እስዬሁ?” እንዴት?

አሁን ኢንተርኔት ተመልሷል፤ ዩቲውብም በሩን ከፍቷል፤ ግን እብዶቹ አሁንም ተመልሰው የጦርነት ከበሯቸውን ይመቱ ይሆናል፤ ወዮላችሁ!

ዩቲውብ መቋረጡን ሳይ ወዲያው ምን ትዝ አለኝ፤ “በየ ድህረገጹ በተለይ በኢትዮጵያውያን ዩቲውብ ቻነሎች ሌት ተቀን በጥላቻ ተግተው ሲለፈልፉ የሚሰሙትና የሚታዩት የኢትዮጵያ ጠላቶች፣ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ናቸው። ይብላኝ ለነርሱ!

ሌላ በሃሳቤ የመጣልኝ “ተሰውረው ከዲያብሎስ ሠራዊት ጋር በመፋለም ላይ ያሉት ቅዱሳን አባቶቻችን እኮ በጸሎት ኃይላቸው ሳተላይቶችን ማውረድ ይችላሉ፤ ኢንተርኔቱንም የመገለባበጥ ብቃት ይኖራቸዋል ፤ ታዲያ አሁን ይህን አድርገውት ይሆን?” የሚለው ጥያቄ ነበር።

ሁሉን በቅርቡ ዕልም ድርግም ሊል እንደሚችልና ዓለምም ከንቱ እንደሆነች እንወቀው። ምቀኞቹ በኮፒራይትና በሰበባሰበቡ የወገኖቻቸውን ቻነሎች ለማዘጋት ተግተው ሲሰሩ ስናይ “ምን ያህል ክፉዎች፣ ተንኮለኞች፣ ከንቱዎችና ደካሞች ቢሆኑ ነው?” ብለን እንድንጠይቅ ነው የሚያስገድደን።

ከሦስት ቀናት በፊት “ቤተሰብ ሚዲያ” በተሰኘው የወራዶች (ምናልባት ተሐድሶዎች?)ዩቲውብ ቻኔል የቀጥታ ስርጭት ላይ ገብቼ፤ ጋዜጠኛ/ መሪጌታ ብርሃኑ ተክለ ያሬድን (አባይ ሜዲያ)ባልጠበቅኩት መልክ ከገዳይ አብይ ጎን ተሰልፎ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚካሄደውን ጦርነት ሲደግፍ ስለሰማሁት በላይቭ ቻት የሚከተለውን ጻፍኩለት፤

ወንድም ብርሃኑ አንተ አዲስ አበባ በምቾት ቁጭ ብለህ ከእኛ ጋር በኢንተርኔት ትገናኛለህ፤ መቀሌ ባሉ ወግኖቻችን ላይ ግን ግራኝ አብዮት ቦምብ እያወረደባቸው ነው!ምነው በወለጋ ለተጨፈጨፉት ወገኖቻችን ይህን ያህል ስሜታዊ ሆነህ አልተሟገትም? ዛሬ ይህን ያህል ወርደህ ለገዳያችን አህዛብመናፍቅ አገዛዝ ነፍስህን በመሸጥህ አዝናለሁ”

አዎ! በሃገራችን እኛ የማናየው እና የማንሰማው ትልቅ ግፍና በደል እየተፈጸመ ስለሆነ ይህን የሚያዩት የጸሎት አባቶቻችን፣ እንደነ አቡነ ተክለ ሐይማኖት፣ አቡነ ሐብተ ማርያም እና አባ ዘወንጌል የመሳሰሉት አባቶች ከእግዚአብሔር መላዕክት ጋር ሆነው ከዲያብሎስ ሠራዊት ጋር ለእኛ የማይታየንን ውጊያ በማድረግ ላይ ናቸው። እስኪ ይታየን ግራኝ አብዮት በትግራይ ኢንተርኔትን እና ስልክን ዘግቶ ጭፍጨፋውን እና ሽብሩን በተዋሕዶ ልጆች ላይ እየፈጸመ፤ የተቀረነው በሰላም ኢንተርኔት ስንጠቀም። አንድ ጥያቄ ልጠይቅና፡ እንደው አሁን ይህን ስጽፍ የውጊያ አውሮፕላኖች በቤቴ ላይ ቦምብ ለመጣል ሲያልፉ ባይ ምን ይሰማኝ ነበር?

በወገኖቻችን ላይ ስለሚካሄደውና ከፍተኛ ጭካኔ የተሞላበት ጂሃዳዊ ጭፍጨፋ ዓለም ሊያየውም ሊሰማውም አይሻም። የእኛዎቹ ከሃዲዎችም ድፍረቱን አግኝተው የጦርነት ከበሯቸው በመምታት ሕዝባችንን እያስጨረሱብን ነው። እግዚአብሔር ግን ዝም አይልም! ቅዱሳን አባቶቻችን ግን ሳተለያቱንና ኢንተርኔቱን የማቆም ኃይል ስለተሰጣቸው አስፈላጊ በሆነበት ወቅትና ሰዓት መደረግ ያለበትን ነገር ሁሉ በቅደም ተከተል ያደርጉታል።

ባለፈው መስከረም መጨረሻ ላይ “ዓለም ከጥቅምት መጀመሪያ (ኦክቶበር ፲፫/13) በኋላ ትለወጣለች፣ ትገለባበጣለች፣ ከሰይጣን የሆኑ የሚታዩበት ጊዜ ይመጣል…” በማለት ጽፌ እንደነበር አስታውሳለሁ። ያው አሁን እያየነው ነው፤ ሁሉም ጭንብላቸውን ገልጠዋል! በተዋሕዷውያን ላይ ጂሃዳዊ ጦርነቱ ታውጆብናል። ግን እያየን ነው፤ መሀመዳውያኑ ግራኝ አብዮት አህመድ፣ ሬድዋን ሁሴን፣ ደመቀ መኮንን ሀሰን፣ ጄነራል አደም መሀመድና፤ የጦርነት ተቃውሚ በመምሰል የምትቀርበው ሞፈርያት ካሚል ይህን ጦርነት እንዲመሩት መደረጋቸውን? አዎ! አጋንንቱ እራሳቸውን በማሳየት ላይ ናቸው።

ሰውን ከእግዚአብሔር ከሚለየው አጉል ሰላም ይልቅ ከእግዚአብሔር የማይለየው ጦርነት ይሻላል፤ ስሜታዊ ከሆነና ለቤተ ክርስቲያን ዘለቄታዊ ጉዳት ከሚኖረው ስምምነትና አንድነት ይልቅ ስለ ሐይማኖት መጠበቅ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ የሚኖረውና ለዚህ ሲባል የሚሆን አለመስማማት ይሻላል፡፡ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

____________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: