የእህት አገር አርሜኒያ ህዝብ የከሃዲውን መንግስታቸውን ፓርላማ ተቆጣጠሩት | የግራኝ ወታደሮች ወደ ሱዳን እየሸሹ ነው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 10, 2020
በሁለቱ እህትማሞች እና ጥንታውያን ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ሃገራት፤ በአርሜኒያ እና ኢትዮጵያ ተመሳሳይ ክስተት ጎን ለጎን መታየቱ በአጋጣሚ አይደለም። ውጊያችን የክርስቶስ ተቃዋሚው ከሚመራቸው ከመንፈሳዊ ኃይላት ጋር ነው!
የአርሜኒያ ጠቅላይ ሚንስትር በአርሜኒያ እና አዘርበጃን መካከል በተፈጠረው ጦርነት ክህደት የተሞላበት “የሰላም ስምምነት” በመፈረሙ ነው አርሜኒያኑ ፓርላማውን የተቆጣጠሩት። አርሜኒያውን፤ ጀግኖች!
ኢትዮጵያውያን ኢንጂነር ስመኘው ሲገደል፣ እነ ጄነራል አሳምነው ሲገደሉ፣ በኦሮሚያ ሲዖል ኢትዮጵያውያን ሲታገቱ፣ ሲጨፈጨፉና ሲፈናቀሉ አራት ኪሎ ያለውን ቤተ ፒኮክ እና ፓርላማ እንዲህ መውረር ነበረባቸው። ይህን ሳያደርጉ ስለቀሩ ነው አሁን እባቡ ዐቢይ በሰሜን ኢትዮጵያውያን ላይ ለጀመረው ጥቃት የእሳት ማገዶ እያደረጋቸው ያለው። ግራኝ የሰበሰባቸው ወታደሮች በብዛት ወደ ሱዳን እየሸሹ እንደሆነ ዜናዎች እየወጡ ነው። በዘመነ ኮሮና እንደገና ስደት? አሳዛኝ ነው! የዚህ ‘ጦርነት’ ቀስቃሽ በእብሪት የተወጠረውና ለድርድር አልቀመጥም ያለው ግራኝ መሆኑን አንርሳው!
____________________________
Leave a Reply