Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for October 31st, 2020

ፈረንሳይ | ክርስቲያን ኢትዮጵያን አያስታውሷትም ፥ ሻማዎቹ ግን ካርታዋን ሰርተዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 31, 2020

በመሀመዳውያኑ በአሰቃቂ መልክ ለተገደሉት ክርስቲያኖች የመታሰቢያ ዕለት በኒስ ከተማ ካቴድራል

በማክሮን ባላጋራ በግራኝ አብዮት አህመድ የሚጨፈጨፉትን ክርስቲያን ወገኖቻችንን ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ አያስታውሳቸውም፤ እግዚአብሔር ብቻ አስታዋሻቸው ነውና!

_____________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , | 1 Comment »

የመሬት መንቀጥቀጡ በዮሐንስ ራዕይ ላይ በተጠቀሱት ሰባቱ የእስያ አብያተ ክርስቲያናት | ድንቅ ነው!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 31, 2020

በቱርክ እና ግሪክ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀ ልክ በዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ ውስጥ በተጠቀሱት የ፯/ 7ቱ አብያተ ክርስቲያናት አካባቢ መሆኑ እጅግ በጣም የሚያስገርምና ብዙ ነገር የሚናገር ነው። በግሪኳ ፍጥሞ (Patmos) ደሴት ነበር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የራእይን መጽሐፍ የፃፈው። በቱርክ ደግሞ በመንቀጥቀጡ ክፉኛ የተመታቸው ክፉኛ የተመታችው ስሚረነስ (Smyrna) ፯ቱ አብያተክርስቲያናት ከሚገኙባት ቦታዎች አንዷ ናት። ዛሬ ኢዝሚር ትባላለች። የክርስቶስ ተቃዋሚውና የሀሰተኛው ነብይ መሀመድ የልደት ቀን በሚከበርበት (መውሊድ) ዕለት መከሰቱ ደግሞ ያለምክኒያት አይደለም። ዋ! ዋ! ዋ!

[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፩፥፱]

እኔ ወንድማችሁ የሆንሁ ከእናንተም ጋር አብሬ መከራውንና መንግሥቱን የኢየሱስ ክርስቶስንም ትዕግሥት የምካፈል ዮሐንስ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክር ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።”

👉ከሦስት ሳምንታት በፊት እነዚህን ፯ ዓብያተክርስቲያናት በሚከተለው ጽሑፍ ማንሳቴን አሁን ስገነዘብ “ምን ይሆን?” እያልኩ በመገረም በመንቀጥቀጥ ላይ ነኝ።

አውሎ ንፋሱ “ኢዝሚር” ብለው የሰየሟትን የመጽሐፍ ቅዱሷን ሰምርኔስ ከተማ ነው ያጠቃት።

ስምርኔስን ኢዝሚር፣ ናዝሬትን አዳማየቦታ መጠሪያ ስሞችን እየቀያየሩ እግዚአብሔር ያልሰጣቸውን ቦታዎች ለሚወሩ ለክርስቶስ ተቃዋሚዎች፤ ዋ! ! !

በዮሐንስ ራዕይ ላይ የተጠቀሱት ሰባቱ የእስያ አብያተ ክርስቲያናት ያለምክኒያት አይደለም ዛሬ “ቱርክ” በተባለቸው የክርስቶስ ተቃዋሚ ሃገር እንዲገኙ የተደረገው። ድንቅ ነው!

የቦታዎቹን ስም ልክ ናዝሬትን – አዳማ ፣ ደብረዘይትን – ቢሾፍቱ ብለው እንደሰየሙት እንደ እኛዎቹ የቱርክ ወኪሎች ወራሪዎቹ ቱርኮችም እግዚአብሔር የሰየማቸውን ቦታዎች እንደተለመድው እንዲህ በማለት ቀይረዋቸዋል፦

. ኤፌሶን – ሰልጁክ

. ሰምርኔስ – ኢዝሚር

. ጴርጋሞን – ቤርጋማ

. ትያጥሮን – አኪሳር

. ሰርዴስ – ሳርት

. ፊልድልፍያ – አላሸሂር

. ሎዶቅያ – ዴንዝሊ

_________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | 1 Comment »

 
%d bloggers like this: