ጀግናዋ እህታችን በዚህ ሩጫዋ ግራኝን + ወያኔን + ኮሮናን ድል አደረገቻቸው | ይህ ትልቅ ምልክት ነው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 12, 2020
በስፔና ቫሌንሲያ ከተማ የሴቶችን የ፭ ሺህ ሜትር ክብረወሰንን ባስደናቂ መልክ የሰበረችው አትሌት ለተሰንበት ግደይ በኢትዮጵያ ላይ አሳዛኝ ድራማ በመስራት ላይ ላሉት የብልጽግና እና ህውሀት የሉሲፈራውያኑ ቅጥረኞች አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀዩን ካርድ አሳይታቸዋለች። በዚህ ድንቅ ሩጫዋ ኮሮና የተባለው ጋኔን እነ አብዮት አህመድ አሊ በአውሮፕላን እና በሻንጣ ወደ ሃገራችን ካላስገቡት በቀር ኢትዮጵያውያኑን እንደማይዛቸውም ነው በግልጽ ያሳየችን። እስኪ ይታየን የመላው ዓለም ነዋሪዎች የኦክስጅን እጥረት በሚፈጥረው የኮሮና ቫይረስ እየተሰቃየ ባጭሩ ሲቀጠፍ እህታችን የረጅም ርቀት የዓለም ክብረወሰን ሰበረች። እግዚአብሔር ከአውሬዎቹ ይጠብቅሽ!
____________________________
Leave a Reply