Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for October 9th, 2020

አውሎ ንፋስ + በረዶ + ጎርፍ + መብረቅ በክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 9, 2020

አውሎ ንፋሱ “ኢዝሚር” ብለው የሰየሟትን የመጽሐፍ ቅዱሷን ሰምርኔስስ ከተማ ነው ያጠቃት።

ስምርኔስን ኢዝሚር፣ ናዝሬትን አዳማየቦታ መጠሪያ ስሞችን እየቀያየሩ እግዚአብሔር ያልሰጣቸውን ቦታዎች ለሚወሩ ለክርስቶስ ተቃዋሚዎች፤ ዋ! ! !

በዮሐንስ ራዕይ ላይ የተጠቀሱት ሰባቱ የእስያ አብያተ ክርስቲያናት ያለምክኒያት አይደለም ዛሬ “ቱርክ” በተባለቸው የክርስቶስ ተቃዋሚ ሃገር እንዲገኙ የተደረገው። ድንቅ ነው!

👉 የቦታዎቹን ስም ልክ ናዝሬትን – አዳማ ፣ ደብረዘይትን – ቢሾፍቱ ብለው እንደሰየሙት እንደ እኛዎቹ የቱርክ ወኪሎች ወራሪዎቹ ቱርኮችም እግዚአብሔር የሰየማቸውን ቦታዎች እንደተለመድው እንዲህ በማለት ቀይረዋቸዋል፦

. ኤፌሶን – ሰልጁክ

. ሰምርኔስ – ኢዝሚር

. ጴርጋሞን – ቤርጋማ

፬. ትያጥሮን – አኪሳር

. ሰርዴስ – ሳርት

. ፊልድልፍያ – አላሸሂር

. ሎዶቅያ – ዴንዝሊ

[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፪]

፩ በኤፌሶን ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። በቀኝ እጁ ሰባቱን ከዋክብት የያዘው በሰባቱም የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚሄደው እንዲህ ይላል።

፪ ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንዳትችል፥ እንዲሁም ሳይሆኑ። ሐዋርያት ነን የሚሉቱን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤

፫ ታግሠህማል፥ ስለ ስሜም ብለህ ጸንተህ አልደከምህም።

፬ ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።

፭ እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሐም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።

፮ ነገር ግን ይህ አለህ፤ እኔ ደግሞ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃልና።

፯ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ።

፰ በሰምርኔስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። ሞቶ የነበረው ሕያውም የሆነው ፊተኛውና መጨረሻው እንዲህ ይላል።

፱ መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ፥ ነገር ግን ባለ ጠጋ ነህ፤ የሰይጣንም ማኅበር ናቸው እንጂ አይሁድ ሳይሆኑ። አይሁድ ነን የሚሉት የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ።

፲ ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ፥ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፥ አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።

፲፩ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል የነሣው በሁለተኛው ሞት አይጐዳም።

፲፪ በጴርጋሞንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ያለው እንዲህ ይላል።

፲፫ የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፥ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም።

፲፬ ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።

፲፭ እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ።

፲፮ እንግዲህ ንስሐ ግባ፤ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፥ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ።

፲፯ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፥ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፥ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል።

፲፰ በትያጥሮንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። እንደ እሳት ነበልባል የሆኑ ዓይኖች ያሉት በእቶንም የነጠረ የጋለ ናስ የሚመስሉ እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ይላል።

፲፱ ሥራህንና ፍቅርህን እምነትህንም አገልግሎትህንም ትዕግሥትህንም ከፊተኛውም ሥራህ ይልቅ የኋለኛው እንዲበዛ አውቃለሁ።

፳ ዳሩ ግን። ነቢይ ነኝ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤

፳፩ ንስሐም እንድትገባ ጊዜ ሰጠኋት ከዝሙትዋም ንስሐ እንድትገባ አልወደደችም።

፳፪ እነሆ፥ በአልጋ ላይ እጥላታለሁ፥ ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩትን ከሥራዋ ንስሐ ባይገቡ በታላቅ መከራ እጥላቸዋለሁ፤

፳፫ ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።

፳፬ ዳሩ ግን ይህን ትምህርት ለማትይዙ ሁሉ የሰይጣንንም ጥልቅ ነገር እነርሱ እንደሚሉት ለማታውቁ ለእናንተ በትያጥሮን ለቀራችሁት እላለሁ፤ ሌላ ሸክም አልጭንባችሁም፥

፳፭ ነገር ግን እስክመጣ ድረስ ያላችሁን ጠብቁ።

፳፮-፳፯ ድል ለነሣውና እስከ መጨረሻም ሥራዬን ለጠበቀው እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ በአሕዛብ ላይ ሥልጣንን እሰጠዋለሁ፥ በብረትም በትር ይገዛቸዋል፥ እንደ ሸክላ ዕቃም ይቀጠቀጣሉ፤

፳፰ የንጋትንም ኮከብ እሰጠዋለሁ።

፳፱ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።

…ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ይግቡ…

___________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | 1 Comment »

አርሜኒያ ኃያሏ ቅድስት አርሴማ ለሰማዕትነት የበቃችባት ሃገር ናት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 9, 2020

በዚህ ቪዲዮ፦

👉 በኤሽሚያድዚን አርሜኒያ የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ መቃብር የሚገኝበትን ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን እናያለን።

👉ቅድስት አርሴማን አርመኖች ቅድስት ሪፕሲሜ ብለው ነው የሚጠሯት

👉 ቅድስት አርሴማ በሮማ ከተማ በ፪፻/ 200 ዓ.ም አካባቢ ተወለደች፤ እዚህ በኤሽሚያድዚን አርሜኒያ በጥቅምት ፱/9. ፪፻፺/290 ዓ.ም በሰማዕትነት አረፈች፤ በ፫፻፩/301 ዓ.ም መላው የአርሜኒያ ሕዝብ ክርስትናን እንዲቀበል ዋና ምክኒያት የሆነች ሰማዕት(የኔ እናት!)

👉 በአውሮፓውያኑ የግንቦት ፳፫/23 ዕለት በአርሜኒያ ታላቅ የቅድስት አርሴማ / ሪፕሲሜ በዓል ይከበራል

👉 ሁለቱ ጥንታውያን ክርስቲያን የተራራ ሕዝቦች፣ አርመኖችና ኢትዮጵያውያን በቅድስት አርሴማ በኩል ያገኙት ድንቅ የሆነ መንፈሳዊ ትስስር የክርስቶስ ተቃዋሚውን ማንነት ለማጋለጥ ይበቁ ዘንድ ነው።

👉 ቅድስት አርሴማ ሰማዕት ዘአርሜኒያ፥ ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት

የቅድስት አርሴማ ወላጆች አባቷ ቴዎድሮስ እናቷ አትናትያስ ይባላሉ። በፈሪሃ እግዚአብሔር በአምልኮ ጸንተው በሕጉ ተመርተው የኖሩ ደጋግ ሰዎች ናቸው። ልጅ አጥተው መካን ሆነው ሲኖሩ ዘር እንዲሰጣቸው ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩ ነበር። እግዚአብሔርም ጸሎታቸውን ሰምቶ ደም ግባቷ ያማረ መልከ መልካም የሆነች እንደ ጸሐይ የምታበራ ልጅ ሰጣቸው። ቅድስት አርሴማ የነበረችበት ዘመን ዘመነ ሰማዕታት ይባላል። ዲዮቅልጥያኖስ የሮም ቄሳር ሆኖ የነገሰበት (እኤአ ከ፪፻፹፬/284ዓ/ም – ፫፻፭/305 ዓ/ም) : አብያተ ክርስቲያናት የተዘጉበትና አብያተ ጣኦታት ተከፍተው ክርስቲያኖች በክርስቶስ ስም ልዩ ልዩ መከራና ሰማዕትነት የሚቀበሉበት ዘመን ነበር። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ” እንዳለ [ዕብ ፲፩፥፴፭፡፴፯]

ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ መልኳ ውብ የሆነ ብላቴና ድንግል ሊያገባ ፈልጎ ሔደው መርጠው ያመጡለት ዘንድ ሠራዊቱን በየሀገሩ ሰደደ። ይህች ቅድስት አርሴማ በሮሜ ሀገር በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ከሌሎች ማኅበረ ደናግል ጋር ነበረች። እየፈለጉ ሲሄዱ እሷን አይተው ሥዕሏን ሥለው ወስደው ሰጡት። መልካም ብላቴና አግኝታችሁልኛል ሄዳችሁ አምጡልኝ አላቸው። እርሷም በመንፈስ አውቃ እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ እንጂ ከአረማውያን ጋር አንድነት የለኝም ብላ ከ39 ደናግል ጋር ወደ አርማንያ ተሰደደች።

ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ የከበረች አርሴማን በፈለጋት ጊዜ አላገኛትም: ግን በአርማንያ አገር እንዳለች ሰምቶ ለአርማንያ ንጉሥ ለድርጣድስ አስፈልገህ ላክልኝ ብሎ ላከበት። ንጉሥ ድርጣድስ ደናግሉ ከተሰወሩበት አስፈልጎ አገኛት። እሱም የቅድስት አርሴማን መልከ ቀናነቷን አይቶ ይህችንስ አሳልፌ አልሰጥም ብሎ መሪያቸው አጋታን አባብላ እሺ ታሰኝለት ዘንድ አዘዛት። እሷም አይሆንም ያልሁ እንደሁ ጸብ አጸናለሁ ብላ እሺ አለችው እሷን ግን ለመንግሥተ ሰማያት የታጨሽ ነሽና ይህ ዕልው እንዳያረክስሽ እወቂ ብላ ልቧን አስጨከነቻት። ንጉሡም ይዞ ወደ እልፍኙ ሊአስገባት ከአደባባይ መካከል ተነሥቶ ድንግል አርሴማን ያዛት። ኃይል መንፈሳዊ ተሰጥቷታልና ጎትታ ከመሬት ቀላቀለችው። እርሱ ግን በጦርነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለነበር በታናሽ ብላቴና ስለተሸነፈ ያን ጊዜ አፈረ። ራሷንም በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጧት። ከዚህ በኋላ ደናግሉን ሁሉ ከእናታቸው (እመምኔት) አጋታ ጋር በሰይፍ አስመትቷቸዋል። ሥጋቸውም በተራራ ጫፍ ላይ እንዲጣል ተደረገ። ይህም የሆነው በመስከረም ፳፱/ 29 ነው።

ሰማዕታት ከተገደሉ በኋላ በንጉሡ ላይ ጋኔን ተጫነበት: መልኩም ተለውጦ እንደ እርያ ሆነ። ወዳጆቹም በዳነልን እያሉ ሲጨነቁ የታዘዘ መልአክ መጥቶ እኅቱን ከጎርጎርዮስ በቀር የሚያድነው የለም አላት። ንጉሥ ድርጣድስ የአርማንያውን ሊቀጳጳስ ቅዱስ ጎርጎርዮስን በሃይማኖት ምክንያት ተጣልቶ ከአዘቅት ጉድጓድ ውስጥ አስጥሎት ነበርና የሞተ መስሏቸው ደነገጡ። እርሱ ግን መልአኩ ለአንዲት መበለት ነግሮለት ምግቡን እየጣለችለት ይኖር ነበርና ምናልባት አምላኩ ጠብቆት ይሆናል ብለው ገመድ ቢጥሉ መኖሩን ለማሳወቅ ገመዱን ወዘወዘው። ቢጎትቱት በ15ዓመቱ ከሰል መስሎ ወጥቷል። የንጉሡ እኀት ወንድሜን አድንልኝ አለችው። ቅዱስ መጀመሪያ አጽመ ሰማዕታትን አሳዩኝ ብሎ አሳይታው ያን አስቀብሮ ካለበት ሄዶ ባድንህ በፈጣሪዬ ታምናለህን? አለው። ግዕዛኑን ፈጽሞ አልነሳውም ነበርና በአዎንታ ላሱን ነቀነቀ። የተደረገለትን እንዳይዘነጋ ከእጁ ከእግሩ የእርያ ምልክት ትቶ ጸልዮ አድኖታል። አመንኩ አጥምቀኝ አለው ለማጥመቅስ ሥልጣን የለኝም አለው። በአንጾኪያው ሊቀጳጳስ ተጠመቀ። እሱንም ሊቀጳጳስነት አሹሞት ብዙ ተግሳጻት ጽፎ ብዙ ድርሳናትን ደርሶ ብዙ የቱሩፋትን ሥራ ሠርቶ አርፏል። ዕረፍቱ ታሕሣስ ፲፭/15 ቀን ነው።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን: እኛንም በእናታችን በቅድስት አርሴማ አማላጅነት በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን: በረከታቸውም ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን!

__________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: