ከወር በፊት ልክ በዛሬው መድኃኔ ዓለም ዕለት ጨረቃዋ ላይ ያየሁት ተዓምር
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 7, 2020
👉 መድኃኔ ዓለም ነሐሴ ፳፯ / 27 / ፪ሺ፲፪ ዓ.ም
እጄ ያለወትሮው እየተንቀጠቀጠ ካሜራውን መያዝ እኪያቅተኝ ድረስ፤ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን፣ ክቡር መስቀሉን፣ ላሊበላ ቤተ ጊዮርጊስን ቀለማቶቻችንን እና ኢ‘ት‘ዮጵያን ያየሁ መሰለኝ፤ የተሰማኝም ይህ ነው።
ጨረቃዋ እንደ መስተዋት ሆና ጌታችንን፣ እመቤታችንን፣ ክቡር መስቀሉን፣ ኢትዮጵያችንን፣ ቀለማቶቻችንን፣ የላሊበላን መስቀል (ያለፈውን የፀሐይ ግርዶሽ እናስታውሳለን?) ለመላው እያሳየች እኮ ነው። ኢትዮጵያኛው እና መስቀለኛው “ት” ፊደል እኮ በግልጽ ይታያል፤ በጣም ይገርማል! ይህ ተዓምር ቀላል ነገር አይደለም። በዚሁ ዕለት በአዲስ አበባ ኮተቤ ሚካኤል አካባቢ ከተከሰተው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ጋር ምን ሊያገናኘው እንደሚችል አላውቅም። ግን የሆነ ነገር አለ።
👉 ባለፈው የሆሳዕና ዕለት እመቤታችንን እና ልጇን ጌታችንን ነበር የታዩኝ፤
____________________________
Leave a Reply