Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for October 3rd, 2020

፫ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ እስር ሲዖል ተገደሉ ፤ ለዋቄዮ-አላህ ተሰው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 3, 2020

የተሰውትን ወንድሞቻችንን ነፍሳቸውን ይማርላቸው!

ዋናው የጀርመን ብሔራዊ ቴሌቪዥን በትናንትናው ዕለት አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጠቅሶ እንደዘገበው።

የሚገርመው መገጣጠም፤ ጋሎችን ወደ ኦሮሞነት በመለወጥ ኦሮሙማን የፈጠረችው ጀርመን በዛሬው ዕለት የጀርመን የዉህደት ብሔራው ቀንን በማክበር ላይ ትገኛለች። በተጨማሪ ይህ ዕለት ሰይጣናዊው ኢሬቻ ለአቴቴ መስዋዕት የሚያቀርብበት ቀን ነው።

በጣም ያሳዝናል፤ በጣም ደም የሚያፈላ ምስል እያየን ነው፤ እኛ ኢትዮጵያውያን በታሪካችን እንደዚህ ዘመን ተዋርደን አናውቅም፤ እንስሳም እኮ እንዲህ አይያዝም፤ ሃገራችንን ለጠላቶቿ አስረክብን ዓለም እንዲሳለቅብን ተደረግን፤ የኢትዮጵያውያንን መንበርከክ ዓለም ለሺህ ዓመታት ያህል ስትመኘው ነበር፤ ዛሬ ተሳካላት። ሳውዲዎቹ እና ተባባሪይዋ የግራኝ ቄሮ አህዛብ አገዛዝ እሳቱ ወደማይጠፋበት ዘላለማዊ ሲዖል ይውረዱ!

____________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቤተክርስቲያን የባህል ጎዳና ሆነች | ራያዎች በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እንዲጨፍሩ ተደረጉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 3, 2020

ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን፡ ክብረ በዓል፤ የተዋሕዶ ጠላቶች የራያ ጨፋሪዎችን ወደ አዲስ አበባ አምጥተው፡ ምዕመናንን እንዲያውኩ ሲያደርጓቸው።

በተዋሕዶ ክርስትና እና ቤተ ክርስቲያን ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ከሁሉም አቅጣጫ እየመጣ ነው። አባቶቻችንን በየገዳማቱ ማጥቃትና መግደል የመጨረሻው ዒላማቸው እንደሆነ ብናውቅም፤ መጀመሪያ ግን ክርስቲያናዊ ሕይወትን በመላው የማሕበረሰብ ክፍሎች፣ በየመንገዱ፣ በየመስሪያ ቤቱ፣ በየጎረቤቱ በመቅረብ ብሎም ወደ ቤተክርስቲያን በሱቅ መልክ፣ በጎብኚ መልክ፣ የመስገጃ ቦታ በመሻማት (ሩፋኤል፣ ራጕኤል) ቀስ በቅስ ጠጋ ጠጋ በማለት ይዋጉታል።

ይህ ክስተት ላለፉት ዓመታት የምናየው ነው። በተለይ በአዲስ አበባ አድባራትና ዓብያተ ክርስቲያናት የሕዝበ ክርስቲያኑን መንፈሳዊ እርጋታና ሰላሙን ለማወክ ገበያዎችን ይከፍታሉ፣ የመዝሙር ሲዲዎችን በከፍተኛ ጭኸት የሚያስተዋውቁትን መኪናዎችን አምጥተው ያቆማሉ፤ ባሕላዊ ዘፋኞችን እና ጨፋሪዎችን ወደ ቤተ ክርስቲያን ግቢ ያስገቧቸዋል። (ልክ እዚህ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ግቢ ራያዎችን እንደምናያቸው) የስከሩ ጨፋሪዎች ሁሉ ሲገቡ የሚታዩባቸው በዓላት አሉ። ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ሌላ ቦት ባሕላቸውን ቢያስተዋውቁ ባልከፋ፤ ነገር ግን ያመጧቸው ሆን ተብሎ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው “ሁሉም ባሕል ነው፣ ሁሉም አንድ ዓይነት ነው” የሚለውን አጀንዳ ለማራማድ ይጠቀሙባቸው ዘንድ ነው።

ከራያ ያመጧቸውን የባህል ጨፋሪዎች (ድሮም ወደ አክሱምና ላሊበላ አካባቢ አምጥተው እዚያ እንዲሰፍሩ መደረጋቸው የጣዖቱን ዋቄዮ አምልኮት ያስፋፉ ዘንድ በእባባዊ መልክ በማቀድ ነበር) በየአብያተ ክርስቲያናቱ እንዲገቡ በማድረግ የቤተክርስቲያንን ሥርዓት ለማበላሸትና እምነታችንንም ወደ ባሕላዊ ሥርዓት ለመለወጥ ይቻላቸው ዘንድ በደንብ አቅደውበት ነው።

በነገራችን ላይ፡ እንደ “መስቀል” እና “ጥምቀት” የመሳሰሉትን ክብረ በዓላት የየተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት፤ በምህጻሩ UNESCO በሚባለው ድርጅት እውቅናን እንዲያገኝ መደረጉ መንፈሳዊ የሆነችውን ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ወደ ዓለማዊው የባህል፣ ወግና ልምድ ሥርዓት ይለወጥ ዘንድ የተጠነሰሰ ዲያብሎሳዊ ሤራ ነው። ቤተ ክርስቲያንን የባሕል ተቋም ለማድረግ የሚሠራ ሥራ ነው።

ቤተ ክህነትም ሆነች ምዕመናን ክርስቲያናዊ በዓላታቸውን በአውሬው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካል ዕውቅና እንዲያገኙ ከመታገል መቆጠብ ይኖርባቸዋል፤ አሊያ ይህ ትልቅ ስህተት ነው የሚሆነው።

____________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: