እንደ ታማኝ በየነ በመሳሰሉ አሽቃባጮች ኢትዮጵያ ተዋረደች
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 22, 2020
ይህን ቪዲዮ እና ንግግሩን ገና ዛሬ ማየቴና መስማቴ ነው። ማመን ነበር ያቃተኝ፤ በእውነት እጅግ በጣም የሚያሳፍር ነው፤ ለታሪክም የሚቀመጥ ነው። እነዚህን አሽቃባጮች እንዴት እንቅልፍ እንዴት ይወስዳቸዋል?
ምስኪኖቹ የደምቢዶሎ ተማሪዎች ከተሰወሩ ፪፻፺፬ / 294 ቀናት ሆኗቸዋል። አብዛኛው “ኢትዮጵያዊ ነኝ” የሚለው ወገን ግን ቀስበቀስ እየረሳቸው ነው፤ እንዴት ያሳዝናል፣ ምን ዓይነት ዘመን ላይ ደረስን? ምን ያህል አሳፋሪ ትውልድ ቢሆን ነው?! ከስማኒያ ዓመታት በፊት ዘመዶቻቸውን ያጡት የአውሮፓ አይሁዳውያን በየሜዲያው እየተጋበዙ የዘመዶቻቸውን በሂትለር ናዚዎች መጭፍጨፍ ጥልቅ በሆነ መልክ ስቅስቅ እያሉ በማልቀስና ድርጊቱም እንዳይደገም ለተቀረው ዓለም ለማስጠንቀቅ ተግተው ሲሰሩ ሳያቸው፤ እኛ የትናንትናውን ሰቆቃ እና ስቃይ እንኳን ለማስታወስ ብሎም የወገናችንን ሞት ለመበቀል የማንሻ ደካሞች እንደሆንን ነው በሃዘን የምታዘበው።
_____________________________
Leave a Reply