Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • September 2020
  M T W T F S S
   123456
  78910111213
  14151617181920
  21222324252627
  282930  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

የመስቀሉ ጠላቶች መጀመሪያ በሬውን፣ ቀጥሎ አቴቴን፣ ከዚያም ቡልዶዘሩን | ዛሬ ይህን ይመስላል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 20, 2020

ዛሬ መስቀለ ኢየሱስ ነው ፣ ክቡር መስቀሉ ወደ ኢትዮጵያ የመጣበት እና የእመቤታችን በዓልም፡ “ጴዴኒያ” ነው።

ቪዲዮው የሚያሳየው አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በትናንትናው ዕለት ምን እንደሚመስል ነው። እጅግ በጣም ያሳዝናል! ደም ያፈላል!

የመስቀል ጠላቶች ከእለተ ዓርብ ጀምሮ የምላስ ጦራቸውን ስለው፣ የቅናት እና የምቀኝነት ምላሳቸውን አጠንከረው፣ መስቀልን ከምእመናን ልቡና ለማጥፋት መላ ጊዜያቸውን አጥፍተዋል፤ ሊያጠፉት ግን አልቻሉም ኃይል አለውና።

አዎ! የመስቀሉ ጠላቶች መጀመሪያ በሬውን፣ ቀጥሎ የአቴቴ ኤሬቻን፣ ከዚያ ቡልዶዘሩን

ባለፈው ዓመት መስቀል አደባባይ እንዲገባ የተደረገውን ያን ምስኪን በሬ እናስታውሳለን? አዎ ያኔ ምስኪኑን በሬ የኢሬቻ ጋኔን ሞልተው ላኩትና ፀረመስቀል ዲያብሎሳዊ ስራቸውን ጀመሩ

በዚያን ወቅት የሚከተለውን ጽፌ ነበር፦

ከደመራ አንድ ሳምንት በፊት በመስቀል አደባባይ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን እና ግዮን (አባይ) ሆቴል አቅራቢያ የሚፈሰውን ወንዝ የዋቄዮ-አላህ ልጆች ከለሉት፣ ከዚያም የሩጫ ውድድር አካሄዱ፣ የደመራ ችቦ በበራ በሳምንቱ ሰይጣናዊውን የኢሬቻን በዓል በመስቀል አደባባይ በማክበር አጋንንታቸውን በአካባቢው አራገፉ።

በመስቀል አደባባይ ደመራ ዕለት በሬው የተላከውም በቤተ ክርስቲያን እና ክቡር መስቀሉ ላይ ለመሳለቅ ታስቦ ነበር። አንርሳው!

አዎ! ይህ በመስቀል አደባባይ እና ቅዱስ እስጢፋኖስ አካባቢ ያለው ቦታ ከፍተኛ የመንፈሳዊ ውጊያ የሚካሄድበት ቦታ ነው። ነገሮችን ለማባባስ በቤተክርስቲያን እና ቤተክህነቷ ውስጥ ሰርገው የገቡ የዲያብሎስ የግብር ልጆች ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ናቸው።

“….ሰዎች ጥቅም ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸውየሚፈልጉትን እያሳየህ ወደምትፈልገው ስፍራ ውሰድ እና ጣላቸውከዚያም በሬ ሆይ! ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይብለህ ተርትባቸውእያለች አሽካካችብን እኮ የሰዶሟ ፒኮክ።

አውሬው አብዮት አህመድ አሊና የፈለፈለው እንቁላሉ ታከለ ዑማ የቤተ ክህነትን ፈቃድ ሳይጠይቁ የማረሻ ግሬደሮችን ወደ መስቀል አደባባይ ተጣድፈው በመላክ ቁፋሮውን ጀመሩ፤ እነ እስክንድር ነጋ ለመስቀሉ ባላቸው ክብር ተቃውሟቸውን ለማሰማት ወደ መስቀል አደባባይ ሲያመሩ ጦርነት ያወጀባቸው ግራኝ አህመድ ወደ እስር ቤት ወርወራቸው፣ በሽብርተኝነትም ወነጀላቸው። የመስቀል ደመራ ቀናት ሲቃረቡ ግራኝ ውርንጭላውን ታከለ ኡማን ለማዳን ከጉድጓድ ቆፋሪ ከንቲባነቱ አንስቶ የማዕድን ቆፋሪ ሚንስትር አደረገው። አቤት የእነዚህ ሁለት አውሬዎች ወንጀል!

👉 እነ ዘመድኩን በቀለ አብዮት አህመድን እና ታከለ ዑማን በማድነቅ (ንስሐ ግቡ!) ለመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ድጋፋቸውን ሲሰጡና ተዋሕዷውያንን ለማሳመንና ወደ ግራኝ ካምፕ ለማምጣት ካድሪያዊ የሆነ ጽሑፍ ሲያቀርቡ (የዘመድኩን ጽሑፍ ታች ኮሜንት ላይ ይገኛል) በጊዜው ቁፋሮው እንደጀመረ የሚከተለውን ጽፌ ነበር፦

👉 አሁን የዘንዶዋን አቴቴን እንቁላል በመስቀል አደባባይ ሊቀብሩት ነው…

እንግዲህ ያው፤ ይህን ያህል ነው ወራሪዎቹ የዲያብሎስ ልጆች የናቁንና የደፈሩን! ቀስበቀስ…አንድ ባንድ…ነጥብ በነጥብ…

ክረምቱ በመቃረቡና የቁፋሮ ሥራውንም በሰበባ ሰበቡ በማጓታት የሚቀጥለው ታላቅ ክርስቲያናዊ የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል በአደባባዩ እንዳይከበር ያደርጋሉ ማለት ነው። ለስቅለት ዕለትና ለትንሣኤ ክብረ በዓል ቤተ ክርስቲያንን ዘጉ፣ አሁን ክቡር መስቀሉ እንዳይከበር ወይ በወረርሽኝ፣ ወይ ደግሞ በዚህ ቁፋሮ መሰናክል ይፈጥራሉ ፥ ቀጥሎ ያለው ትልቁና ለሕዝበ ክርስቲያኑ በጣም አስፈላጊ የሆነው ክብረ በዓል ጥምቀት ነው ፤ አዎ! ለሱም ጃንሜዳን ለአህዛብ ነጋዴዎች በመስጠት ብሎም የሆቴልና ሱቅ ግንባታዎችን በማቀድ ላይ ናቸው።

ወገን፤ ለሃገራችን ኢትዮጵያና ልጆቿ፣ ለቤተ ክርስቲያናችን እንደነ አብይ አህመድ፣ ብርሃኑ ነጋ፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ ለማ መገርሳና ታከለ ኡማ ክምንዜውም የከፋ ጭካኔ፣ ውድቀትና ውርደት ያመጣ መንጋ የለም።

ግን ለዚህ ሁሉ ሰዶማዊ የፍዬል ድፍረታቸው ተጠያቂዎቹ ቤተ ክህነት፣ የክርስቲያኖችን ወኔ ያስነጠቁት ሰባኪያን እና “አባቶች” እንዲሁም እግዚአብሔርን በውስጣቸው ይዘው ወለም ዘለም በማለት ሁሌ ከላይ ትዕዛዝ የሚጠብቁት የተዋሕዶ ልጆች ናቸው። በአምላክህ ላይ፣ በሃይማኖትህ ላይ፣ በቋንቋና ባሕልህ ላይ፣ በሃገርህ ላይ፣ በአባቶችና እናቶችህ እንዲሁም ልጆችህ ላይ የተነሱትን አማሊቃውያን ጠላቶችህን አንድ ባንድ የመድፋት 100% መብት እያለህ እጅህን አጣጥፈህ ቁጭ የምትለው ለምንድን ነው?

👉 ለፋሲካ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመግባት የወሰኑትን ምዕመናን የ666ቱ አብይ ፖሊሶች እንዴት እንዳሰቃዩአቸው እናስታውሳለን?

👉 የናዝሬትን ሕፃናት የገደሉት ሃይማኖትን ገድለዋታል | ተዋሕዶ በመሆናቸው

እህቴ፤ የእኔ እህት ተዋሕዶ በመሆኗ፣ ማህተብና መስቀል በማጥለቋ በአገሯ ባሰቃቂ መልክ ተገደለች። ወይኔ!

👉 መስቀል አደባባይንና ጃን ሜዳን ለመውረስ ጂሃድ እያካሄዱ ነው

👉 ኡስታዙ፤ ኢየሱስ ጌታ አይደለም ነብይ እንጂ። ጌታ አይወልድም አይወለድምብሎ እንዲያውጅ ተደረገ

👉 በኢሉባቡር ፖሊሶች የተዋሕዶ ልጆችን ማህተብ በምላጭ ሲበጥሱ ነበር፣

👉 በናዝሬት 7 የተዋሕዶ ሕፃናት በትንሣኤ ዕለት ተመርዘው ተገደሉ (የመርዝ ጂሃድ)

[ትን.ኤር.፱፥፳፩፡፳፬]

ሕፃናቱን ከመንገድ ጕልማሶቹንም ከአደባባይ ያጠፉ ዘንድ ሞት ወደ መስኮታችን ደርሶአል ወደ አዳራሻችንም ውስጥ ገብቶአል። የሰውም ሬሳ እንደ ጕድፍ በእርሻ ላይ፥ ማንምም እንደማይሰበስበው ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው። ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር።

____________________________

One Response to “የመስቀሉ ጠላቶች መጀመሪያ በሬውን፣ ቀጥሎ አቴቴን፣ ከዚያም ቡልዶዘሩን | ዛሬ ይህን ይመስላል”

 1. addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ said

  ወንድም ዘመድኩን በቀለን ተጠያቂ ከሚያደርጉት ካድሪያዊ ጽሑፎቹ መካከል የሚከተለው ይገኝበታል፤ በትንሣኤ ማግስት መጻፉ ደግሞ ጉዳዩን በጣም አሳዛኝ ያደርገዋል። በፊስቡክ ገጹ ሐሙስ, ሚያዝያ 22 2012 የተጻፈ፦

  • ስለ ጃንሜዳው ምንም መረጃ የለኝም። በመስቀል አደባባዩ ጉዳይ ግን አቋሜ ከከተማ አስተዳደሩና ከአቢቹ ጎን ነው። ኢቲፉፋ፣ ኢቲሙዳ ፣ ፉንዱረ ቆፈ። ጀባዻ !!

  ~ የግል ዕይታዬ ነው። ተናግሬአለሁ።

  የመስቀል አደባባይ ጉዳይ !!

  •••
  በመስቀል አደባባይ ጉዳይ እኔ ዘመዴም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋና እንደ አንድ ኦርቶዶክሳዊ የተዋሕዶ አማኝ ሃሳብ የመስጠት ሕገ መንግሥታዊና ተፈጥሮአዊ መብቴን ተጠቅሜ እንደሚከተለው አድርጌ በጉዳዩ ላይ የራሴን፣ የግሌን ሃሳብ መስጠት እጀምራለሁ። መብቴ ይከበር።

  •••
  ሰሞኑን በዚሁ በእኛው የፌስቡክ መንደር የዕለት እንጀራችን ይሆኑ ዘንድ ከተሰጡን የመነታሪኪያ አጀንዳዎች መሃል የመስቀል አደባባይና የጃንሜዳ ጉዳይ ከዋነኞቹ ምድብ የሚገኙ ናቸው። ጨዋታው ከክፉ አእምሮ ብቻ ፈልቆ ሊያነታርከን የመጣ ነው ብሎ መደምደም ባይቻልም ደግሞም በጉዳዩ ላይ ምን ታስቦ ነው ብሎ መጠየቁም ስህተት አይደለም። ስንጠይቅ ግን በመላምት ሳይሆን በጥንቃቄ ቢሆን ይመረጣል። መንጋው ግን ኔትወርክ አገኘሁ ብሎ መበጥረቁ ደስስ አይልም።

  •••
  የመስቀል አደባባይ ልማት ጉዳይ ቀደም ብሎ ከዓመታት በፊት የተያዘና ለህዝብ ይፋ የሆነ ፕሮጀክት ነው። በወቅቱ ሁላችንም እኔንም ጨምሮ ያለመዋሸት የመስቀል አደባባይን በመንግሥት ይፋ የሆነውን ዲዛይን ዓይተን መደሰታችንንም አስታውሳለሁ። ቀጥሎም አቢቹ ወደ ሥልጣን ከመጣም በኋላ የቤተ መንግሥት እድሳትና ፓርክ፣ የወንዝ ዳር ልማት፣ የእንጦጦ ተራራንና የመስቀል አደባባይ እድሳት እንደርጋለን እያለ ሲወተውት ያልሰማው የለም። ሁሉም ሰምቷል። ነገርግን በወቅቱ ማብራሪያ ፈልጎ ጉዳዩ ይመለከተኛል ብሎ የጠየቀ ባለድርሻ አካል የለም። ቤተ ክህነቱም ጭምር። በነገራችን ላይ ዘመዴ ይለኛል እንጦጦን የጎበኘ ወዳጄ “ ዘመዴ እንጦጦ ቀን ወጥቶለታል። ለራጉኤል፣ ለማርያም፣ ለቁስቋም፣ ለሽንቁሩ ቱሪስት ይጎርፋል። ውስጥ ለውስጥ የእግር መንገድ፣ የብስክሌት መንገድ፣ ካፍቴርያ ይሠራል። ከምር አፄ ዳዊት አሁን ነው የተካሡት ብሎኛል። መልካም ነው።

  •••
  እውነት ለመናገር የእንጦጦን ተራራ ያዩ ወዳጆቼ እንደሚነግሩኝ ከሆነ እዚህ ጀርመን አውሮጳ እንደማየው አድርገው አሳምረው መሥራታቸውን ነው የሰማሁት። ለእግረኛና ብስክሌት ለሚነዳ ሽርሽርም በጫካ ውስጥ የእግር ጉዞ ማድረግ ለሚፈልግ ሰው በሚመች አዕምሮንም በሚያድስ መልኩ መሠራቱን በሥራው የተደሰቱ ወዳጆቼ ነግረውኛል። ዕድሜ ከሰጠኝ እኔም አንድ ቀን ሽር ብትን እልበት ይሆናል። እናም ከአፄ ዘርዓያዕቆብ አባት ከአፄ ዳዊት በኋላ በዳግማዊ አጼ ሚኒሊክ የተጎበኘችው የእንጦጦ ተራራ አሁን በአቢቹ ዘመን በድጋሚ እንደተጎበኘች ነው የዓይን እማኞች የሚናገሩት። ሁሌ ትችት ደስስ አይልም። ፓትሪያርኬን አንቆ የገደለውን፣ ቤተ ክርስቲያንን አውድሞ ባዶ እጇን ያስቀራትን ደርግን አንድ ድልድይ ሠርቷል ብለን በአንድ እግራችን ቆመን እንጸልይለት የለ እንዴ? ገዳይ ድልድይ ሠራ ብሎ ጮቤ መርገጥ ዛሬ የተጀመረ አይደለም። እናም የፈለገ ቢሆን በስህተቱ እወቀስን በመልካም ሥራው ደግሞ ማመስገን እንልመድ።

  •••
  አሁን የመስቀል አደባባይን ጉዳይ ነገሩን ያጦዘው በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ በአቡነ ያሬድ አማካኝነት ወጣ የተባለው ደብዳቤ ነው። እግዚአብሔር ያሳያችሁ፣ ድንግል ማርያም ታመልክታችሁ። በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ይሄን ሁሉ ዓመት ስለ ፕሮጀክቱ ከጠቅላዩ ጀምሮ ሲነገር፣ ሲወራ፣ ሲመከር፣ ሲዘከር ዝም ጭጭ ብለው ሲያበቁ፣ መስቀል አደባባይ ሲታጠር ዝም ብለው ሲያበቁ፣ መስቀል አደባባይ መቶ ሜትር ጥልቅ ሆኖ ተቆፍሮ አፈሩ ተግዞ ሊያበቃ ሲል ከእንቅልፉ ብትት ብሎ እንደባነነ ሰው ድንገት ብድግ ብለው ሲያበቁ“ ምን እየተሠራ ነው? ማብራሪያ እፈልጋለሁ ማለት ልክ አይመስለኝም። ልክም አይደለም።

  •••
  ቦታው ቤተ ክርስቲያንን አያገባትም ብዬ እንደ ሲሳይ አጌና፣ እንደ መሳይ መኮንን፣ እንደ ግርማ ጉተማም አፌን አልከፍትም። ይቅርታ አድርጉልኝና እኔ መራታ ልሆን እችላለሁ እንጂ በፍፁም ገሌ ክፍትአፍ ልሆን አልችልም። እንኳን ሥፍራውን ለዘመናት ስትጠቀምበት የቆየችውን ይቅርና ለሳምንታት የተከራዩትን የቀበሌ ቤት እነ አጅሬ ስም አይጠሬ ህወሓቶች እንኳ በዘመናቸው የአከራይ ተከራይ ምንትስዬ ቅብጥርስዬ እያሉ የሰው ቤት የአንተ ነው ውረስም እያሉ ስንቱን ሳምንቴ ተከራይ ባለሱቅ አድርጋው የለም እንዴ? በተለይ ስንቱ የወያኔ አባል ነው ቀደም ብሎ በሚያገኘው መረጃ ተመርቶ መርካቶ የአረጋውያንን ሱቅ በሚያማልል ብር እየተከራየ በዚህ ሙድ መርካቶ ገብቶ የብዙዎችን መጦሪያ ወርሶ ባለ ሱቅ ሆኖ የቀረው? ስንቶችስ በዚህ ምክንያት አብደው ሞቱ። እናም ዘመናትን ያስቆጠረውን ስፍራ ቤተ ክርስቲያን አያገባትም ማለትም ነውር ነው። [ ይሄ የአከራይ ተከራይ ጉዳይ አይደለም ]

  •••
  ዛሬ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚለው የቤተ ክህነቱ ደብዳቤ አይደለም ከዓመት በፊት ከሳምንታት በፊት የት ነበር? እንዲያው ደርሶ በፌስቡክ ጫጫታ ድንገት ተነስቶ ነገር ካበቃ በኋላ ቤተክርስቲያኒቷን ደካማ ለማስመሰል በሚመስል መልኩ የማይቆም ነገር ለማስቆም መንጠራራት ከምር ልክ አይደለም። እኔ እንዲህ ነው የማስበው። ቀድሞ ነው መጥኖ መደቆስ፣ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ የሚባል ነገርም እኮ አለ። ጅብ ከሄደ ነው ነገሩ።

  •••
  የመስቀል አደባባይን በተመለከተ አርክቴክት ዮሐንስ በግሩም ሁኔታ ያዘጋጀውን እዚህ ላይ ማንሳት ተገቢ ነው። በዳግማዊ አጼ ምኒልክ እና በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት የመስቀል ደመራ በዓል ከአራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በስተደቡብ ወረድ ብሎ በሚገኘው ቦታ ላይ ይከበር እንደነበር መርስኤ ኀዘን ወልደቂርቆስ በዘመን ትውስታ መጽሐፋቸው አስፍረውልናል ይላል አርክቴክቱ። ይቀጥልናም።

  •••
  በግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ደግሞ ከቤተ መንግሥቱ በስተደቡብ መኖሪያቸውን ያደረጉት (የአሁኑ አዲስ አበባ ሙዝየም) ራስ ብሩ ወልደ ገብርኤል ከግል ርስታቸው ከፍለው ለመስቀል ደመራ ማክበሪያ አደባባይ እንዲሆን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰጡት መሠረት የደመራው አደባባይ ከጊዮርጊስ ወደ አሁኑ መስቀል አደባባይ ተዛወረ።

  •••
  ደርግ ወደ ሥልጣን ሲመጣ በጉልበት ከወረሳቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አደባባዮች እና ይዞታዎች አንዱ ይኸው መስቀል አደባባይ ሲሆን ስያሜውንም ከመስቀል አደባባይ ወደ አብዮት አደባባይነት በመቀየር የደመራውንም ሥርዓት ከአደባባዩ ነጥሎ ወደ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን መለሰው።

  •••
  ሕወሓት መራሹ ኢህአዴግ አዲስ አበባን ለመቆጣጠር አንድ ሳምንት ሲቀረው ሀገሪቱን ለ6ቀናት ብቻ በማስተዳደር የሚታወቁት ጀነራል ተሥፋዬ ገብረኪዳን አብዮት አደባባይ የሚለውን ስያሜ በመሠረዝ ወደቀደመ ስያሜው (መስቀል አደባባይ) መለሱት።

  •••
  ኢህአዴግ ሀገሪቱን ግንቦት ወር 1983 ዓም ላይ ሲቆጣጠር ከአራት ወራት በኋላ የመስቀል ደመራ በዓል በጥንታዊ ይዞታው በአሁኑ መስቀል አደባባይ መከበር ጀመረ። ይኸው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁንም በዚሁ ቦታ ላይ እየተከበረ ይገኛል በማለት የመስቀል አደባባይን ታሪካዊ የትመጣውን በአጭሩ ያስረዳናል። ወዳጄ መስቀል አደባባይ መስቀል አደባባይ ነው። አሁንም ወደፊትም ደመራው በዚያው ይከበራል። አከተመ።

  •••
  መስቀል አደባባይ ማለት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ አደባባይ ነው። የጨሰ የሙዚቃ ድግስ ይዘጋጅበታል። በኦሎምፒክ አደባባይ ሃገር የሚያስጠሩ አትሌቶች ልምምድ ይሠሩበታል። ሰላማዊም የተቃውሞ ሰልፍም ይወጣበታል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የታክሲና የአውቶቡስም መነሃሪያም ነበር። ስቴዲየሙ ሲሞላባቸው ሙስሊሞችም ይሰግዱበታል። ስክሪን ተሰቅሎ የዓለም ዋንጫ ይታይበት ነበር። መስቀል አደባባይ ስሙን ይዞ አገልግሎቱ ግን ዘርፈ ብዙ ነው። ደርግም፣ ኢህአዴግም፣ ቅንጅትም፣ አዴፓም፣ ኦነግም ደንፍተውበታል፣ ፎክረውበታል፣ እሪሪሪ ብለውበታል። እያሉበትም ነው።

  •••
  የእኔን የመረጃ ምንጮች ጠየቅኩ። ሁሉም ማለት በሚቻል መልኩ ነገ የሚፈጠረውን አናውቅም እንጂ ዛሬ መስቀል አደባባይን የማስዋቡ ፕሮጀክት ምንም ክፋት የለውም። ምን አልባት ስጋታችን አቢቹ ወፈፍ አድርጎት ልክ የሚኒሊክ ቤተ መንግሥትን ወደ አንድነት ፓርክ እንደቀየረው ሁሉ ይሄንንም እነ ግርማ ጉተማን ለማስደሰት ሲል የመስቀል አደባባይ የሚለውንም ( ዩኒቲ ፓርክ) እለዋለሁ ብሎ አቧራ እንዳያስጨስ ነው የምንሰጋው ይላሉ። [ እንደዚያ ሲል የተደመጠ ይመስለኛል። (ዩኒቲ ስኴር ሲል የሰማሁት ይመስለኛል) እንጂ በተረፈ ግን ሥራው ለመስቀል በዓል እንዲደርስ ተደርጎ ሌት ተቀን እንደሚሠራ ነው የሚናገሩት። ሌቦቹ በብዛት መቀሌ ስለገቡ አዲሶቹ ገዢዎች ብልጽግና ለቀጣዩ ምርጫ ሲል ነስር በነስርም ሆነው በቶሎ ለማድረስና ነጥብ ለማስቆጠር ይሞክራሉ ብለን እንገምታለን ነው የሚሉት። ገንዘቡ ቀደም ብሎ የተመደበ ነው። ሥራው ሌት ተቀን እየተሠራ ነው። ለበዓሉ ይደረሳል ነው የሚሉት የመረጃ ምንጮቼ።

  •••
  ሁሉንም ነገር የመቃወም ሱስ ባይሆን ጥሩ ነው። መስቀል አደባባይ እንደ መስቀል አደባባይነቱ መች ተጠበቀ? በየግንቡ ስር የሚጸዳዳው ሰው ቀላል ነው እንዴ? ያ አካባቢ በግሩም ሁኔታ ተሠርቶ ቢያልቅ ጥቅሙ ለሁላችንም ነው። ለሃገሪቷም ጠቃሚ ነው። አቢቹ አዝሎት አይሄድ። ወይ እንደነ መለስ ዜናዊ ሥልጣን ላይ ወጥቻለሁና ፕሮጀክቱን አጋሮ፣ ወይም በሻሻ ልውሰደው አላለ። መስቀል አደባባይን በተመለከተ ከተቻለ መደገፍ እንጂ መንጫጫቱ ዋጋ የለውም። የመንጫጪያው ሰዓት አልፏል። በተለይ የወያኔ አክቲቪስ ጉዳዩን አጀንዳ አድርጎ ሲያጦዘው ሳይ ይበሰጨኛል።

  •••
  አሁን ከተቻለ የአርክቴክት የሆንስን የመጨረሻዋን ምክር ተግባራዊ ለማድረግ መንቀሳቀስ ነው። 3) የቦታው ታሪካዊ እና ትውፊታዊ ባለቤት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቦታው ላይ ባለድርሻ (Stake Holder) እንደመሆኗ መጠን የከተማ መስተዳደሩ ቦታውን እንዴት ሊያዘጋጀው እንዳሰበ ሃሳብ እንድትሰጥበት ተገቢውን ክብር ሰጥቶ ቢያንስ የዲዛይን ሰነዶቹን ሊሰጣት እና ምክሯን ሊያካተላት ይገባል። አሁን ይሄ ብቻ ነው መፍትሄው። ከተማ አስተዳደሩም ሁላችንም ጴንጤዎች ነንና በሚል ትዕቢት ምን ታመጣላችሁ የሚልም ንቀት ካለበት ትቶ ወደ ቤተ ክህነቱ ሄዶ በትህትና ይነጋገር። እንጂ የሲሳይ አጌንና መሳይን መኮንንን ምክር ሰምቶ፣ የወሐቢይን ጫጫቴ አድምጦ ሃገር ከሆነችው ቤተ ክርስቲያን ጋር ባይላተም መልካም ነው ባይ ነኝ። በተረፈ ሁሉን ነገር ከ666፣ ከኢሉሚናንቲ፣ ከዘረኝነትና ከተረኝነት ጋር እያያዙ በሆነው፣ ባልሆነውም ሁሉ ማላዘን አይገባም።

  •••
  ቀደምት ፓትርያርኮቹ እነ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስና አቡነ ቴዎፍሎስ ቤተ ክርስቲያን ወደፊት ሊደርስባት ከሚችለው አደጋና፣ ከሚመጣው ፈተና ተርፋ ትሻገር ዘንድ ቀድመው በማሰብ የሰበካ ጉባኤንና የሰንበት ትምህርት ቤትን አቋቁመዋል። ( የደርግ መምጣት ሳይገለጽላቸው አልቀረም። ) በዚህ ምክንያት አብዮቱ ፈንድቶ ደርግ የቤተ ክህነቱንም፣ የቤተ ክርስቲያንንም ቀጣይነት ፈተና ላይ በጣለ ጊዜ፣ ርስቷን፣ ጉልቷን፣ ህንጻዎቿን፣ ቤቶቿን ሁሉ ወርሶ ባዶ እጇን ባስቀራት ጊዜ ሰበካ ጉባኤ ባይኖርና ሰንበት ትምህርት ቤት ባይኖር ኖሮ አልቆልን እኮ ነበር። ታቦት አውጥታ፣ ዣንጥላ ዘቅዝቃ ለምና ነው ያን ዘመን የተሻገረችው። የቀደሙት አባቶች እንዲህ ወደፊት ሊፈጠር የሚችል ችግር አስቀድመው ተመልክተው መፍትሄ ያስቀምጣሉ። እንጂ እንደዛሬው መስቀል አደባባይ ከታረሰ፣ ጃንሜዳም ከተወረሰ በኋላ ደብዳቤ በመጻፍ አለመጣም አልቀርም አይነት ጨዋታ ውስጥ አይገቡም። ደግሞም ተቦክቶ ለተጋገረ ዳቦ ተሰብስቦ ውይይትና አስተያየት መስጠት ፋይዳው አይታየኝም።

  ••• አሁን እንደኔ እንደኔ እነዚህ ነገሮች ቢታዩ ብዬ ጥቆማ እሰጣለሁ።

  ፩ኛ፥ አደባባዩ “ መስቀል አደባባይ” የሚለው ስሙ እንዳይቀየር መነጋገር።

  ፪ኛ፥ በተያዘለት ጊዜ በፍጥነት ተገንብቶ አልቆ ለመስቀል በዓል እንዲደርስ ማገዝ።።

  ፫ኛ፥ የከተማውም አስተዳደር ከቤተ ክህነቱ ጋር ተመካክሮ የደረሱበትን ውሳኔ ሁለቱም በሚድያ ይፋ ማድረግ። አስተዳደሩም ቤተ ክህነቱ ለጻፈው ደብዳቤውም ምላሽ ይስጥ። አይጎዳም። ሥራውም አይቆምም።

  4ኛ፥ አዳሜና ሔዋኔ ነገር አታጋግል። ጫ ብለህ ስማ። በባዶ ሜዳ እሳት አታቀጣጥል። መንጦልጦል ብትፈልግ እንኳ በእውቀት በመረጃ የሆነች ነገር ይዘህ ተንጦልጠል። እንጂ በባዶ እጅ በጨበጣ ኔፓ ሃሳብ ይዘህ እሪሪሪ አትበል። ለዩቲዩብ ቀፋዮችም ሲሳይ አትሁን።

  •••
  በቦታው ከስር የመኪና ማቆሚያ ነው የሚሠራው እየተባለ እየሰማ መስቀል አደባባይ እየተቆፈረ ነው ይልልኛል። እና ሳይቆፈር አናቱ ላይ ሊሠራ ነው እንዴ? ዥል። የመስቀል አደባባይ ለመስቀል በዓል እንዲደርስ እጥፍ ተከፍሎ ነው እተሠራ ያለው ነው የሚለው ለእኔ የደረሰኝ መረጃ። ከሥር ብዙ መኪና ማቆሚያ ፓርክም አለው። አሁን ጠዋት ጠዋት የግል በአደባባዩ ላይ የሚቆሙት አውቶቡሶች ፕሮጀክቱ ሲያልቅ በስር ይቆማሉ ማለት ነው። አደባባዩ ማራኪና ጽዱ ይሆናል። እንደሚታወቀው አካባቢው የመጸዳጃ ቤት የለውም። አሁን ከሥር ይሠራል። ግንባታው ቀድሞ አሁን የተጀመረው ወደኋላ ከተገፋ የመስቀል በዓል እንዳይረበሽ ነው ተብያለሁ። በርታ አቢቹ፣ በርታ ታከለ። በዚህ እንኳን ከጎናችሁ ነኝ። በሌላውም ስህተት ሳገኝ እኚኚ የማለት መብቴእንደተጠበቀ ነው።

  •••
  በተረፈ ይሄን ከሚሠራ የንጹህ መጠጥ ውኃ ባቀረበልን፣ ዘይት፣ ስኳር ባቀረበልን፣ መብራት የትራንስፖርት ሥርዓቱን ባሻሻለልን። የሚለው ጥያቄም ትክክል ነው። ተገቢም ነው። የደሃ ቤት ማፍረሱን መቃወም፣ መሞገት እሱም ተገቢ ነው። አንበሳን አውርዳ የተሰቀለችውን የፒኮክ ወፍን እሽሽ ብሎ መቃወም እሱም ትክክል ነው። መስቀል አደባባይ ለምን ቆንጆ ሆኖ ይታደሳል ብሎ መሞገት ግን ምቀኝነት ነው። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በመንበረ ፓትርያርኩ ጊቢ መንበረ ፓትርያርክን የሚመጥን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን የሚመጥን ህንጻ ባቆሙ ጊዜ አቧራ ነበር የጨሰው። አሁን ጳጳሳት ከሆኑት መካከልም በወቅቱ አባ ጳውሎስ ልክ አልሠሩም ያሉም አይጠፉም ነበር። ነገር ግን መንበረ ፓትርያርኩም ሆነ፣ የሊቃነ ጳጳሳቱ መኖሪያ ህንጻ ዛሬ የአባ ጳውሎስን ስም በበጎ የሚያስነሳ ሆኖ ነው የተገኘው። ቅዱስ ፓትርያርኩ አርፈዋል። ህንጻውንና ልማቱን ግን ተሸክመውት ወደ መቃብር አልገቡም። እናም አቢቹም በጎ በጎውን ይሥራ። ሲሠራ እናመሰግነዋለን። ሲያጠፋ ደግሞ በጉማሬና ሳማ ምላሳችን ያለ ርህራሄ እንዠልጠዋለን። ይኸው ነው።

  •••
  ደግሞ ዛሬ አንተማ ኦነግ ሆነሃል በለኝና ኢኚኚኚ ስትልብኝ ዋል አሉህ። በል ደኅና ወል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: