Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • September 2020
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ዲያብሎስ በዚህ ክርስቲያናዊ ትዕግስት፣ ፍቅርና የእምነት ጽናት በጣም ይቀናል፣ ይቃጠላል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 9, 2020

እጣን እጣን ይሸታል መሬቱ.…

ስለዚህ በእኛ በክርስቲያኖች ላይ ዕባባዊ ተንኮሉን፣ ፈተናውንና መሰናክሉን በማፈራረቅ ስልታዊ በሆነ መንገድ ይመጣብናል።

በትናንትናው ቪዲዮ፤ “የቅዱስ ሩፋኤል ተአምር | ቤተ ክርስቲያኗን ካላፈረስኩ እያለ ሲዝት የነበረው ጠንቋይ ፈንድ “ለዚህም ነው ጠንቋዩ በፈነዳበት ቦታ ላይ ያ መስጊድ የተሠራው” ብየ ነበር።

አዎ! ለዚህም ነው ታች በሙስሊሙ በቀረበው “የመቻቻል” ጽሑፍ ላይ ረመዳንን ለማክበር የመጡ ሙስሊሞች ባልጠፋ ቦታ ቀስ ብለው ወደ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን በመጠጋትና ሆን ብለው ወደ ግቢው በመግባት ለዲያብሎስ አላሃቸው ለመስገድ የፈለጉት።

በመቻቻል” ስም ሙስሊሙ ጸሐፊ በከረሜላ ቀለም ነክሮ የጻፈልንን ቃላት አንብበን እንዳንታለል፤ መሀመዳውያኑ የአላህንና የመሀመድን ስም እየጠሩ ለዲያብሎስ አላህ እስከ ሰገዱ ድረስ ሁልጊዜ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ናቸው፣ የቤተ ክርስቲያንና ክርስቲያኖች ቀንደኛ ጠላቶች ናቸው።

ሆኖም ይህ ሙስሊም ጸሐፊ ያየውን ለመጻፍና ለመመስከር በመሞከሩ ሊመሰገን ይገባዋል። ምስክረነቱ በግልጽ የሚያረጋግጥልን በእኔ በኩል ሁልጊዜ የምናገረውን አንድ ነገር ነው፤ ይህም፡ “በፍርድ ቀን በዓለማችን ካሉ ሙስሊሞች ሁሉ ከባዱን ፍርድ የሚቀበሉት ወይም በጥብቅ የሚፈረድባቸው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ናቸው፤ ምክኒያቱም “ወንጌልን አልሰማንም””ክርስቲያናዊ ፍቅርን አላየንም” ማለት አይችሉምና ነው።” የሚለውን መራራ ሐቅ ነው።

ጸሐፊው “ፍቅር ያሸንፋል!” ይላል፤ ግን ይህ ፍቅር በእስልምና ዘንድ አለን? የለም! በጭራሽ፤ የሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ግቢ ቢሞላና ክርስቲያኖች የመስጊዱን ግቢ ለመጠቀም ቢጠይቋቸው መሀመዳውያኑ የሺህ ሆጀሌ መስጊድን በር ይከፍቱላቸው ነበርን? እ እ! በጭራሽ! ለመግባትም የሚሻ ክርስቲያን አይኖርም!

አዎ! ፍቅሩ በክርስትና እና ክርስቲያኖች ዘንድ ብቻ ነው የሚገኘው፤ ፍቅር ደግሞ አሸናፊ ከሆነ “በመቻቻል” ሳይሆን ሊገለጽ የሚችለው ይህን ፍቅር ያዩት ሙስሊሞች ወደ ክርስቶስ መምጣት ሲችሉ ብቻ ነው። ዋናው ጥያቄ ይህን ፍቅር ያየው ይህ ሙስሊም ጸሐፊ ከእስልምና ድቅድቅ ጨለማ ወጥቶ ወደ ክርስቶስ ብርሃን መጥቷልን? የሚለው ነው። ሌላው ነገር ሁሉ ከንቱ ነውና!

ሙስሊሙ ስለ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን እና ጠንቋዩ በፈነዳበት ቦታ ላይ ስለተሰራው መስጊድ እንዲህ ሲል ጽፏል፤ ተመልከቱ “ቤተ ክርስቲያን”ን “ቤተስኪያን” እያለ ሲጽፍ፦

27ኛዋ የረመዳን ሌሊት በቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን”

(አክረም ሐበሻዊ )

በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በረመዳን ወር የመጨረሻዎቹ ቀናት አንድ የተባረከች

ሌሊት አለች ከ 1000 ወር የምትበልጥ “የውሳኔዋ ሌሊት ” ትባላለች አማኙም የዚህ በረከት ተቋዳሽ ለመሆን ሌቱን በፀሎት ያሳልፋል። 2003 ዓ/ም ነበር እኔም በአቋራጭ መክበር ቢያቅተኝ በአቋራጭ ሀጢያቴን ላራግፍ ብዬ የዚች ሌሊት ቋሚ ተሰላፊ ለመሆን ጉዞዬን ወደ ሼህ ሆጀሌ መስጂድ አደረኩ።

ስግደቱን የሚመራው በድምፁ ውበት በሚወደደው መሀመድ ደጉ የተባለ ወጣት ነበር።

በሚገርም ሁኔታ ከአራቱም አቅጣጫ በመጡ ሰጋጆች አካባቢው ተሞልቶ መስገጃ አይደለም መቆሚያ ቦታ ጠፋ ልብ በሉ ይህ የሚሆነው ሌሊት 8:00 ሰዓት ላይ ነው!! እኔና ብዙ እንደኔው ሀጢያታቸውን ለማራገፍ የመጡ ሰዎች ሩፋኤል ደጃፍ ተሰግስገን በአይናችን መስገጃ ቦታ በምንማትርበት ጊዜ ነበር አንድ የቤተስኪያኑ ቄስ የመጡት ሌት ስለነበር መልካቸው ብዙም ትዝ አይለኝም ግን እንደ ካድሬ የሐይማኖት አባቶች በብስጭት ሳይሆን በእዝነት የሸበተ ነጭ ፂማቸው ፊቴ ላይ አለ “እንደምን አመሻችሁ ልጆቼ ” የመጀመሪያ ቃላቸው ነበር ከሁኔታችን መስገጃ ቦታ እንዳጣን ተረዱ የቤተስኪያኑንም ደጃፍ ለስግደት ሲፈቅዱልን ጊዜ አልፈጀባቸውም።

እኛም አመስግነን ስግደታችንን ቀጠልን እሳቸውም ወደ መቅደሱ ዘለቁ ግን አፍታም ሳይቆዩ ተመልሰው መጡ የመሬቱን እርጥበት ለመከላከል ይረዳል ያሉትን የሚነጠፍ ነገር ሰብስበው አመጡልን ያኔ ግን ሁላችንም እንደ መጀመሪያው ማመስገን አልቻልንም ይልቁንም የኒያን ሽማግሌ አባት ፊት እያየን አይኖቻችን እንባ አቀረሩ እንጂ !!

ኢትዮጵያዊነቴን ወደድኩት! ኮራሁበት! ሰዓቱ እየሄደ ሲመጣ ወደ ቤተስኪያኒቱ ለመሳለም የሚመጡ ሰዎች ቁጥር እየበረከተ መጣ። ስግደታችንን ላለማቋረጥ የሚያደርጉት ጥረት እጅግ ልብን ይነካል “እንደምን አደራችሁ” “ሰላም ለናንተ” የሚሉ ድምፆች ይሰሙኛል። እናት ክርስቲያኖች” እኔን ልጆቼ ብርዱ ገደላቹ” ሲሉ ኢትዮጵያዊ እንባ አነባው !!

አንዳንዶቻችን ፍቅር ያሸንፋል ሲባል የሰማነው የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ሊሆን ይችላል እኔ ግን በዛች በተቀደሰች የረመዳን ሌሊት በአይኔ አየሁት!!

ወዳጄ እውነታው ይሄ ነው፤

ስለመቻቻል የሚያስተምሩህ አላማቸው እንድትቻቻል አይደለም ይልቁንም ልዩነትህን እንድታውቅ ነው ከዛም ብስለት ከሌለህ የኔ ይበልጣል ማለት ትጀምራለህ፣ ታዲያ ያኔ መቻቻል ድራሹ ጠፋ አይደል የሚባለው? ከዛም ፍቅር በገሐድ ማሸነፉ ይቀርና የሙዚቃ ኮንሰርቶች ላይ ብቻ “ፍቅር ያሸንፋል”

ሲባል ትሰማለህ። ፍቅርም የሕይወት ማጣፈጫ መሆኑ ይቀርና የአልበም ማሻሻጫ ይሆናል!ይብላኝ ፍቅርና መቻቻልን ከ ETV ዶክመንተሪ ለሚጠብቁ እኔስ ፍቅር ሲያሸንፍ እንዴት እንደሆነ እኒያ ነጭ ፂም ያላቸው የሩፋኤል አባ አሳይተውኛል።

እኔም እንዲህ አልኩ፤

አቦ አትጨቅጭቁን ከተቻቻልን ዘመን አለፈን!!! ወዳጄ፤ ሃገሩን የማይወድ አቦ አይወለድ !!! ኢትዮጵያ ለዘልአለም ትኑር”

______________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: