እኅተ ማርያም እንኳን ተፈታሽ ፥ ግን በሕልሜ እንደነገርኩሽና ‘እሺ!’ እንዳልሽው ተመለሺ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 23, 2020
እኅተ ማርያም በታሰረች በቀናት ውስጥ በአየሁት ሕልም፤ “ከወሰድሻቸው አንዳንድ እርምጃዎችሽ ተመለሽ፣ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትና ቀኖና አክብሪ፤ የቀን መቁጠሪያ ስርዓቶቿንም ተከተይ፣ “ንግሥትነቱም”አስፈላጊ አይደለም፤ በተለይ የቤተ ክርስቲያንን የውስጥና የውጭ ጠላቶች በሕብረት ተጠናክረን መዋጋት በሚገባን በዚህ ወቅት ምዕመናኑን የሚከፋፍልና የሚያዳክም ሥራ መስራት፤ የአውሬውን አገዛዝ ማጠናከር ካለሆነ በቀር አስፈላጊም ተገቢም አይደለም።” በማለት ስነግራት፤ “እሽ፤ ከስህተቴ እማራላሁ፤ አስተካክለዋለሁ!” ነበር ያለችኝ።
ለማንኛውም እንኳን ተፈታሽ፤ አሁን፤ የተጠቀሱትን ከማስተካከል ጎን ባፋጣኝ ብታደርጊ ደስ የሚለኝ “የተዋሕዶ ልጆችን ፍለጋ” ብለሽ አንዱን ዘመቻሽን እንደጠራሽው ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ታግተው የተሠወሩትን እህቶቻችን ጉዳይ ስራየ ብለሽ በመያዝ አሸባሪውን የዐቢይ አህመድ ቄሮ አገዛዝ አዋክቢው።
በተረፈ፤ በምታድሩበት አካባቢ ባይተዋር የሆኑ የቴክኖሎጂ ድምጾችን እየተናበባችሁ ተከታትላችሁ መዝግቡ፤ በተለይ በእንቅልፍ ሰዓታችሁ ወቅት።
እውነት ለመናገር፤ ለተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከእኅተ ማርያም ይልቅ በጣም አደገኛ ሆነው ያገኘኋቸው የሚከተሉት የአሸባሪው መናፍቅ+እስላም ግራኝ ዐቢይ አህመድ ደጋፊዎችና የሰሜን ኢትዮጵያውያን(ትግሬዎች)ጠላቶች ናቸው፦
- 👉 አቡነ ፋኑኤል፤ የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ (ዐቢይ አህመድ ሙሴያችን ነው!)
- 👉 ዳንኤል ክብረት (ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ስም ሲጠራ እንባው ዱብ ዱብ ይላል)
- 👉 ዘመድኩን በቀለ (ዐቢይ አህመድ በእግዚአብሔር የተቀባ መሪ ነው)
ለእኔ ይህ ግልጽ ነው፤ በአደባባይ ካልታረሙና ይቅርታ ካልጠየቁ ፈጠነም ዘገየም ሥራቸው ለሁሉም የሚታይ ይሆናል። አሁንም ከእነዚህ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጆቹ ከሆኑ ወገኖች ተጠንቀቁ እላለሁ!በዚህ ዓለም የክርስቶስ ሰው ይህን ያህል ተወዳጅ አይሆንምና።
Leave a Reply