የዓለም መጨረሻ | ሰዶምና ገሞራ ካሊፎርኒያ በኃይለኛ እሳት እየጋየች ነው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 22, 2020
ምስራቁ የአሜሪካ አትላንቲክ ውቂያኖስ ዳርቻ በአውሎ ነፋስ እየተመታ ሲሆን ምዕራቡ የፓሲፊክ ውቂያኖስ ዳርቻ ደግሞ በእሳት እየጋየ ነው። ለደኖቹና ጫካዎቹ መቃጠል መንስኤው አስራ አንድ ሺህ መብረቆች ናቸው ተብሏል።
የዚህ ቃጠሎ ሰለባ የሆኑት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የካሊፎርኒያ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ይለቁ ዘንድ ተገድደዋል፤ በጊዚያዊ መጠለያ ድንኳኖች ውስጥም ለመኖር ተገድደዋል።
መብረቅ፤ በጣም የሚገርም የተፈጥሮ ክስተት ነው፤ ለሳይንስ ሊቃውንት የመብረቅን አፈጣጠር ምስጢር እስከ አሁን ድረስ በደንብ ሊያውቁት አልተቻላቸውም። “የቀዝቃዛና ሙቅ ዓየር መላተም” ከማለት ውጭ የመብረቀን ምስጢር ማንም አያውቀውም።
ያው እንግዲህ መብረቅ ሁሌ ከእኛ ጋር ነው፤ በየቀኑ እናየዋለን ነገር ግን ስንት የረቀቀ ቴክኖሎጂ ሠርተናል የሚሉት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ልሂቃን የዚህን ቀላል የሚመስል ክስተት ምስጢር ሊያገኙት ብሎም በየጊዚው መብረቅ የሚፈጥረውን አደጋ ለመከላከል የሚያስችል ነገር መፍጠር አልቻሉም። በእውነት በጣም አስገራሚ ነገር ነው። እግዚአብሔር የሚፈቅድላቸውና የማይፈቅድላቸው ነገሮች አሉና።
ካሊፎርኒያ በቅርቡ በኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ትናወጣለች ተብሎ ይጠበቃል፤ ከካሊፎርኒያ ውጡ! አምልጡ! ለማንኛውም ኪዳነ ምሕረት ትድረስላችሁ!
Leave a Reply