Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for August 22nd, 2020

የክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ሌላውን ጥንታዊ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ መስጊድ አደረገችው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 22, 2020

666ቱ የቱርክ መሪ ረሴፕ ኤርዶጋን ከጥቂት ሳምንታት በፊት ጥንታዊውን የቅድስት ሶፍያ ቤተ ክርስቲያን ወደ መስጊድነት ከለወጠ በኋላ አሁን ደግሞ እጅግ በጣም ጥንታዊውንና በአራተኛው ምዕተ ዓመት በገዳምነት የተመሠረተውን የኮራ መድኃኔ ዓለም ሕንፃ መስጊድ ለማድርግ ወስኗል።

ያው እንግዲህ ፍልሰታ ለማርያምን/ ኪዳነ ምሕረትን ጠብቆ በክርስቲያኑ ዓለም ቍስል ላይ ጨው መጨመሩ ነው። አዎ! ኤርዶጋንን እንደ ምሳሌው/አርአያው አድርጎ የሚወስደው የእኛው 666 አሸባሪ ግራኝ አብዮት አህመድም የክርስቲያን በዓላት ሲቃረቡ በተዋሕዶ ልጆች ላይ ለመሳለቅ ብቅ ይላል፤ በቅርቡም ደብረታቦርን/ቡሄን ጠብቆ የጂሃድ አጋሮቹን ሾሟል። በመጭዎቹ ሳምንታትም ተመሳሳይ የሞት “ጨዋታዎችን” እንጠብቃለን።

ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ ልብ በል፤ መሀመዳውያኑ ጦርነት ካወጁብን ሺህ አራት መቶ ዓመታትን አስቆጥረዋል፤ በተለይ ዛሬ በእኛ በጥንታውያኑ ክርስቲያን ሕዝቦች ላይ በኤዶምውያኑ ምዕራባውያን እየተደገፉ ግልጽ የሆነ ጥቃት እየፈጸሙብን ነው፤ ስለዚህ በቃ! በሉ! መለሳለሱንና ጉርብትናውን ሁሉ አቁሙ፤ በይሉኝታ ጊዜና ጉልበት ሳናበክን በስጋም ሆነ በመንፈስ ልንዋጋቸው ግድ ነው።

___________________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የዓለም መጨረሻ | ሰዶምና ገሞራ ካሊፎርኒያ በኃይለኛ እሳት እየጋየች ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 22, 2020

ምስራቁ የአሜሪካ አትላንቲክ ውቂያኖስ ዳርቻ በአውሎ ነፋስ እየተመታ ሲሆን ምዕራቡ የፓሲፊክ ውቂያኖስ ዳርቻ ደግሞ በእሳት እየጋየ ነው። ለደኖቹና ጫካዎቹ መቃጠል መንስኤው አስራ አንድ ሺህ መብረቆች ናቸው ተብሏል።

የዚህ ቃጠሎ ሰለባ የሆኑት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የካሊፎርኒያ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ይለቁ ዘንድ ተገድደዋል፤ በጊዚያዊ መጠለያ ድንኳኖች ውስጥም ለመኖር ተገድደዋል።

መብረቅ፤ በጣም የሚገርም የተፈጥሮ ክስተት ነው፤ ለሳይንስ ሊቃውንት የመብረቅን አፈጣጠር ምስጢር እስከ አሁን ድረስ በደንብ ሊያውቁት አልተቻላቸውም። “የቀዝቃዛና ሙቅ ዓየር መላተም” ከማለት ውጭ የመብረቀን ምስጢር ማንም አያውቀውም።

ያው እንግዲህ መብረቅ ሁሌ ከእኛ ጋር ነው፤ በየቀኑ እናየዋለን ነገር ግን ስንት የረቀቀ ቴክኖሎጂ ሠርተናል የሚሉት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ልሂቃን የዚህን ቀላል የሚመስል ክስተት ምስጢር ሊያገኙት ብሎም በየጊዚው መብረቅ የሚፈጥረውን አደጋ ለመከላከል የሚያስችል ነገር መፍጠር አልቻሉም። በእውነት በጣም አስገራሚ ነገር ነው። እግዚአብሔር የሚፈቅድላቸውና የማይፈቅድላቸው ነገሮች አሉና።

ካሊፎርኒያ በቅርቡ በኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ትናወጣለች ተብሎ ይጠበቃል፤ ከካሊፎርኒያ ውጡ! አምልጡ! ለማንኛውም ኪዳነ ምሕረት ትድረስላችሁ!

______________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኪዳነ ምህረት | ስንቱ ቀስት አለፈ ስንቱ ሰንሰለት፡ መከታዬ ሆና የጌታዬ እናት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 22, 2020

ኪዳነ ምሕረት ስንል የምሕረት ቃልኪዳን ማለት ነው፡፡ በዚህ ውስጥም ምሕረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምሕረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው፡፡

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ ክርስቶስ መካነ መቃብር ጎለጎታ እየወረደች ትፀልይ ነበር፡፡ ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችው ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ የምህረት ቃል ኪዳን ገባለት ፡፡

እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ፣ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ ቃልኪዳን አደረገ፡፡

« ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ። … » መዝ, ፹፱ ፥፫ እንዲል መፅሐፉ፡፡

ስሟን ለሚጠሩ፣ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት ቃልኪዳን ሰጥቷታል ፡፡

ታላቁ መፅሐፍ እንዲህ ይላል፦

. . . ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤ በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ። ኦሪት ዘፍ. ፱ :፲፮

በዚህም መሠረት ቃልኪዳኗን ምክንያት በማድረግ ኪዳነምሕረት እያልን እንጠራታለን!

እንኳን ለ ኪዳነ ምሕረትአደረሰን። የእመቤታችን ምህረት እና ረድዔት፤ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን!

_____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: