Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for August 19th, 2020

አርሲ ነገሌ | ጨለማው በቡሄ ብርሃን ድል ተነሳ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 19, 2020

በመጨረሻም ብርሃን ጨለማን ድል ይነሳል፤ የብርሃነ መስቀሉ ልጆች የዋቄዮአላህን የድቅድቁ ጨለማ አርበኞች ከአርሲ እና ኦሮሚያ ከተባለው ህገወጥ ክልል ጠራርገው ያስወጧቸዋል።

_____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የግራኝ ድፍረት | ለቡሄ የፈንጅ ሙልሙል፣ ለእንቁጣጣሽና መስቀል የእሾህ አበባ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 19, 2020

መልካም የቡሄ በዓል ይሁንላችሁ!!!

ይቅርታ የዚህን ጂኒ ቪዲዮ በማቅረቤ፤ መሆን ስላለበት ነው፤ ጊዜው “ሆያ ሆዬ!” የሚያስብል አይደለም፤ ሰውዬው እስካልተወገደ ድረስ ቤታችን የሃዘን ቤት ነው።

እንግዲህ የቡሄን ብርሃንና ድምቀት ለማደብዘዝ ነው ለአዲስ አበባ አዲስ/አሮጌ ከንቲባ የመረጠው። ኢትዮጵያውያንን ለማናደድና በእነርሱም ላይ ለመሳለቅ ነው ፲፪/፲፪/፲፪ ለሹምሽር እቃእቃ ጨዋታው የመረጠው። ጂኒ ዘመዶቹን እነ ታከለን የቀያየራቸው እንደተለመደው የጀነሳይዱን ጉዳይ ለማረሳሳት ብሎም፣ ወንጀለኞቹ የትግል አጋሮቹን ከጥፋተኝነትና ከፍርድ ለማራቅ ነው። ቆሻሻ! ይህ ሽብርተኛ ሰው ኢትዮጵያን የዲያብሎስ ቤተ ሙከራ አደረጋት። ንግግሩ ሁሉ ቅጥፈት፣ ሥራው ሁሉ ጥፋት። ይህ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተላከ እብድ በቡሄ የእሳት ጅራፍ ባፋጣኝ ካልተጠረግ በቀር በኢትዮጵያውያን ላይ መርዝ መሽናቱን ይቀጥልበታል።

👉 ቡሄ!

ቡሄ ምን ማለት ነው? የሙልሙል ፣ ጅራፍ፣ ችቦ ትውፊቱ ምንድነው?

👉 ቡሄ

ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት፤ የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም ቡኮ /ሊጥ ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት ሙልሙል የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡

👉 ጅራፍ

በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ እና ጀራፍ ማጮኸ ሁለት ዓይነት ምስጢር ይዞ የሚከወን ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡

የመጀመሪያው ግርፋቱን እና ሞቱን እናስብበታለን፡፡እንዲሁም ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምሰክርነት ቃል፣ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ /፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኀበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል፡፡

👉 ችቦ

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ የት መጣ ግን በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች

ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ ምሳሌ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡

👉 ሙልሙል

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን ቡሄ እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ ሙልሙል ዳቦ አለ፡፡ ለምሳሌ ሐዋርያት ምስራች ሊነግሩን፣ ወንጌል ሊሰብኩን በደጃፋችን ቆመው ቡሄ በሉ የሚሉንን አዳጊዎች የሚበሉትን መስጠታችን ምሳሌያዊ /መጽሐፋዊ / ነው፡፡ ጌታችን ደቀ

መዛሙርቱን ባስተማራችሁበት፣ በደረሳችሁበት ተመገቡ ብሏቸዋል፡፡ /ማቴ 10÷ 12/ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡ ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው

ደግሞ ሐዋርያት የምስራች ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ….” ይላሉ፡፡

መልካም የቡሄ በዓል ይሁንላችሁ!!!

__________________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: