በቅድሚያ ለሕፃን ቅዱስ ወንድወሰን፤ ቤተሰቦች መጽናናቱን ይስጥልን! እናቱ ፊት በሚያሳዝን መልክ ማረፉ ልቤን ነበር የሰበረው።
👉 ዛሬ ፲፪/፲፪/፲፪ ነው – ቅዱስ ሚካኤል + ፍልሰታ ለማርያም
በመስኮቴ በኩል ሁለት የማርያም መቀነቶች ታዩኝ፤ ወዲያው ብልጭ ያለብኝ በስቅለት ዕለት በአዲስ አበባ የታዩት ድንቅ የማርያም መቀነቶች ነበሩ። ያኔ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን ተደፋፍረው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲሄዱ የታየ ምልክት ነው፤ ባካችሁ ከዓርብ እስከ እሑድ ወደ ቤተ ክርስቲያን ተሰባስባችሁ ሂዱ! ባካችሁ! ባካችሁ!” ለማለት ደፍሬ ነበር። በማግስቱ ዲያብሎስ የዩቲውብ ቻኔሌን አዘጋብኝ። ዛሬም እዚህ የታዩኝ ሁለት የማርያም መቀነቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይ ተዋሕዷውያን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የዐቢይ አህመድ የቄሮ አገዛዝ በመቆጣጠር ላይ ወዳለው ቤተ መንግስት በማምራት አጥሩን የሚነቀንቅና ትልቅ ተጋድሎ የሚጠይቅ ተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጁ አለዚያ እጅግ በጣም የከፉ ሳምንታትና ወራት ይጠብቋችኋል! ባካችሁ! ባካችሁ ድምጻችሁን በአደባባይ ቶሎ አሰሙ! ነፍጠኛነታችሁን አሳዩአቸው፣ ተፋለሟቸው።” እላለሁ። ሕፃን ቅዱስ ወንደወሰንም የሚጠቁመን ይህን ሊሆን ይችላል።
👉 ማንቸስተር ብሪታኒያ እሑድ ነሐሴ ፲ ፪ሺ፲፪ ዓ.ም / መስቀለ ኢየሱስ
የ፮ ዓመቱ ሕፃን ቅዱስ ወንድወሰን ብስክሌቱ ላይ በመኪና ተገጭቶ ሕይወቱ አለፈች።
ሕፃናት የግል ምርጫ ለማድረግ የሚችሉበት እድሜ ወይም ብስለት ላይ ከመድረሳቸው በፊት ቢሞቱ በእግዚአብሔር ምህረትና ጸጋ ከእግዚአብሔር ፍርድ አምልጠው የዘላለም ሕይወት ያገኛሉ። እግዚአብሔር ሕፃናትን እኛ ከምንወዳቸው በላይ ያፈቅራልና።
ቅዱስ ወንድወሰን የማንቸስተር ዩናይትድና የተጨዋቹ ማርቆስ ራሽፎርድ ደጋፊ እንደሆነ የእንግሊዝ ሜዲያዎች አሳውቀዋል ፥ ማርቆስ የሃዘን መልዕክት ለቤተሰቦቹ አስተላልፏል፤ ከሰሞኑ እንደሚጎበኛቸውም ቃል ገብቶላቸዋል።
የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች ማርቆስ ራሽፎርድ በብሪታኒያ ቢወለድም ዘሩ ግን በካሪቢያን ባሕር ላይ ከምትገኘው ደሴት ሃገር ከ “ቅዱስ ኪትስ እና ኔቪስ” ነው። ቅዱስ ኪትስ እና ኔቪስ / St. Kitts und Nevis – ስሙ ላይ ስናተኮር ቅዱስ ወንድወሰን ጋር የሚመሳሰል ሆኖ እናገኘዋልን። ብንጨምርበት ማርቆስ ራሽፎርድ ፥ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው።
👉 ሕፃን ቅዱስ ወንደወሰን ምን ሊያሳየን የፈለገው ነገር አለ?
ከሁለት ወር በፊት “ኢትዮጲስ” በተሰኘው የዩቲውብ ቻነል ደራሲ አቶ “ታዲዮስ ታንቱ“ን “ጌጥዬ ያለዉ” ከተሰኘው ጋዜጠኛ ጋር ስቱዲዮ ውስጥ ሳያቸው፤ ጋዜጠኛው ከኳስ ተጨዋች ማርቆስ ራሽፈርድ
ጋር በጣም እንደሚመሳሰል ገርሞኝ ስስቅ ነበር። እንዲያውም የሁለቱንም ምስሎች በኮምፒውተሬ
ላይ አስቀርቼ ቪዲዮ ለመሥራት እየተዘጋጀሁ ነበር። ያው ከሁለት ወራት በኋላ ልክ በዕለቱ ይህ አስደናቂ አጋጣሚ ተፈጠረልኝ።
“ኢትዮጲስ” ቻነል በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የተመሠረተና በመጀመሪያዎቹ ወራት ለለገጣፎ እና ሱሉልታ ተፈናቃዮች ከፍተኛ ድምጽ የነበረ ቻነል ነው። ሽብርተኛዎቹ ዐቢይ አህመድና ታከል ዑማ በዚህ ጣቢያ ስላልተደሰቱ ጋዜጠኞቹን በማሰር ሊያዳክሙት በቅተዋል።
አሁን ይህ “ኢትዮጲስ” የተሰኘው ቻነል “ቄሮ ቄሮ / Kero Kero“ የሚል ስም የያዘና የኦሮሚያ ባንዲራ ያነገበ ቻነል ሆኖ ይታያል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? የሽብርተኛው ዐቢይ አህመድ ቄሮ አገዛዝ ወርሶታልን? ቻነሉ ለአንድ ወር ያህል ምንም አዲስ ነገር አላቀረበም።
👉 ሕፃን ቅዱስ ወንድወሰን ምንን እየጠቆመን ነው?
- – ቅዱስ
- – መልአክ (ቅዱስ ሚካኤል?)
- – ቅዱስ ማርቆስ
- – ኢትዮጲስ
- – እስክንድር ነጋ (ቪዲዮውን ሰርቼ ስጨርስ ጋላዋ አዳነች አበቤ *(አአ)በአዲስ አበባ *(አአ) ከንቲባነት መመረጧን ሰማሁ)ዋው!
- – አብይ አህመድ(ቄሮ)(መልአኩ ሰይፍና እሳት ይዞ ይመጣባቸዋል)
👉 ከሕጻን ቂርቆስ ጋር አብረን እናስታውሰው፦
ሦስት ዓመት እንኳን ሳይሞላው በሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ታላቅ ሰማዕትነትን የተቀበለው ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሞስ (ስምዖን) እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ፡፡ ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስ በሕዳር ፲፭ ቀን የተወለደ ሲሆን ሀገሩ በታችኛው እስያ ልዩ ስሙ ሀንጌቤን ይባላል፡፡ ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ነበርና መምለኬ ጣዖት የሆነው ንጉሥ እስክንድሮስ ቅድስት ኢየሉጣን “ለጣዖቴ ስገጂ” ብሎ አስገደዳት፡፡ እርሷም
“ሕጻኑ ልጄ መጥቶ ይመስክር” ብላ ስትናገር ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጠራና ተጠየቀ፡፡ ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስም “ለጣዖት አንሰግድም፣ ዘላለማዊ የሆነ የማይሻር አምላክ ስላለ ለእርሱ ነው የምንሰግደው” ብሎ የአምላኩን ክብር በሕፃን አንደበቱ መሰከረ፡፡ ሕፃኑም ይህንን በመሰከረ ጊዜ ዕድሜው ገና ሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ነበር፡፡
እጅግ በጣም የሚገርመው ቅዱስ ቂርቆስ በከሃዲው ንጉሥ ፊት የጌታችንን ክብር በመሰከረ ጊዜ ንጉሡ እጅግ ተቆጥቶ አርባ ጋን ውኃ የሚይዝ በርሜል አስጥዶ አርባ ቀን ሙሉ እሳት አስነድዶ ቅንጭብ፣ ዘይት፣ ዝፍጥና ሌላም በእጅጉ የሚጎዱ ነገሮችን በውስጡ ጨምሮ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን ወደዚያ እቶኑ እሳት እንዲከቷቸው አዘዘ፡፡
ንጉሡም እሳቱ እንዳልጎዳቸው ሲያውቅ ከዚያ አውጥቶ በሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አፍና አፍንጫ መርዝ ከተተበት፣ ነገር ግን መርዙ ምንም አልጎዳውም እንዳውም ምግብ ሆነው፡፡ ዳግመኛም ጨውና በርበሬ በዐይኑ አነደደበት፡፡ አሁንም ምንም አልነካውም፡፡ ከዚህም በኀላ ሹም እስክድሮስም አስራ አራት የተሳሉና የጋሉ ብረቶች ያመጡ ዘንድ ዳግመኛ አዘዘ፡፡ ሰባቱን በእናቱ አካል ሰባቱን በሱ አካል ውስጥ ይተክሉ ዘንድ ከነዚሁም ሁለቱን በጆሮዎቹ ሁለቱን በዓይኖቹ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ አንዱን በልቡ ይተክሉ ዘንድ አዘዘ፡፡በሕፃኑም ላይ ሹሙ እንዳዘዘው አደረጉበት፡፡ አሁንም ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደና ፈወሳቸው፡፡
ዳግመኛም የሕጻኑን እራስ ከነቆዳው ገፈው በእሳት ውስጥ ይጨምሩ አንድ ሹም አዘዘ፡፡
እንዲሁም አደረጉበት፡፡ ዳግመኛም ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ መጥቶ ይህንን መከራ ከሕፃኑ አራቀለት፡፡ ዳግመኛም ሹሙ በመቃን ውስጥ ጨመረው በገመድ እንዲሰቅሉት አዘዘ፡፡ ከዚህም መከራ መልአኩ አዳነው፡፡ በዛሬዋ ዕለት ሐምሌ 19 ቀን በዓሉን በታላቅ ድምቀት የምናከብረው ይህንን ሁሉ የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤልን ተራዳኢነት በማሰብ ነው፡፡
ንጉሡም በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ በብዙ ጭንቅና ሥቃይ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ለ፫ ዓመታት አሠቃያቸው፡፡ እነርሱም መከራን እየተቀበሉ በከሀዲው ንጉሥ ፊት የአምላካቸውን ስም እየጠሩ መሰከሩ፡፡ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና ክብሩን ይመሰክሩለት ዘንድ የቢታንያን ድንጋዮችና የበለዓምን አህያ አንደበት ከፍቶ ያናገረ አምላክ ሦስት ዓመት እንኳን ባለሞላው በሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወር ሕፃን ልጅ ላይ አድሮ በወቅቱ የነበሩ ዓላውያን ነገሥታት ክብሩን እንዲያውቁ አደረገ፡፡
በመጨረሻም ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጋድሎውን ፈጽሞ ጥር ፲፭ ቀን በ፫ ዓመት ከ፩ ወር ከ፫ ቀኑ አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ ሰማዕትነትን ተቀብሏል፡፡ ሲሰየፍም ከአንገቱም ደም፣ ውኃና ወተት የወጣ ሲሆን ሦስት አክሊላትም ወርደውለታል፡፡ ጌታችንም የመከራውን ጽናት የትዕግስቱን ብዛት አይቶ ከመከራ ሊያሳርፈው ፈቀደና ተገልጾለት ‹‹ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ቂርቆስ›› አለው፡፡ ‹‹ሰላም ላንተ ይሁን፤ የመከራህን ጽናት፣ የትዕግስትህን ብዛት አይቼ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍህ መጣሁ” ብሎ ብዙ ቃልኪዳን ሰጠው፡፡ “…ስምህ በተጠራበት፣ ቤተመቅደስህ በታነጸበት፣ ስዕልህ ባለበት ቦታ ሁሉ የሕፃናት እልቂት፣ የከብት በሽታ፣ የእህል እጦት ርሀብ፣ ቸነፈር አይደርስም›› የሚል አስደናቂ ቃልኪዳንም ገብቶለታል፡፡ ሕፃኑም በምድር ላይ አልተቀበረም ይልቁንም ጌታችን በኤልያስ ሰረገላ ሥጋውን አሳርጎለታል፡፡ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣም በጥር ፲፮ ቀን ሰማዕትቷን በክብር ፈጽማለች፡፡
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፡፡ እኛንም በአማላጅነታቸው የምታመን ሁላችንን የብርሃናዊውን መልአክ የቅዱስ ገብርኤልን፣ የሕጻኑ ቂርቆስንና የቅድስት ኢየሉጣን ረድኤት በረከታቸውን ያሳድርብን፡፡ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
_________________________________________
Like this:
Like Loading...