Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for August 10th, 2020

አሁንስ እነ አሳምነውን፣ ሽመኘውን ምናልባትም ተማሪዎቹን የገደሏቸው ዐቢይና ሽመልስ መሆናቸው ተረጋገጠላችሁ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 10, 2020

👉 ዘፋኝ ሃጫሉንም ያስገደሉት ዐቢይ አህመድ፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ ጀዋር መሀመድ እና ለማ መገርሳ ናቸው። 100%

ሽመልስ አብዲሳ፣ ለማ መገርሳ፣ ጀዋር መሀመድ፣ በቀለ ገርባ የተናገሯቸው ነገሮች ዐቢይ አህመድ ከተናገራቸው በምን ይለያሉ? በምንም! ሁሉም አንድ ናቸውና! እስኪ መልስ ብለን ግራኝ ዐቢይ አህመድ በወሎ፣ በስልጤ፣ በሐረር፣ በባሌና በካይሮ የተናገራቸውን ጽንፈኛ ንግግሮች በድጋሚ እናዳምጣቸው፤ በጽንፈኝነታቸው ከእነ ሽመልስ ቢከፉ እንጅ አያንሱም።

የልዑል እግዚአብሔር መልአክ ቁራውን አብዲሳን(ሺቁራው አብዲሳ)ያስለፈለፈው እኮ መንፈሳዊ ዓይኑ የታወረበት፣ ጆሮው የተደፈነበት ወገን ዓይቶና ሰምቶ ይነቃ ዘንድ ነው። በጣም የሚያሳዝን ነው፤ ምንም ዘመናዊ ትምህርት ወይም የዶክትሬት ማዕረግ የሌላቸው ቆሎ እየቆረጠሙ የሚኖሩ እናቶችና አባቶች እኮ ገና ከመጅመሪያው ለዐቢይ አህመድ አሊ የሥልጣኑ ዙፋን ሲያስረክቡት ግራኝ ተመልሶ መጣብን!” በማለት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ነበር። ይህ መመጻደቅ አይደለም፤ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁንና እኅተ ማርያም እና እኔም ከሌሎች ጥቂት ወገኖች ጋር ያው ከመጀመሪያው ሰዓት አንስተን ለአንዲትም ደቂቃ ያህል ለዚህ አውሬ ሰው እጃችንን ሳንሰጥና፤ እንደ አብዛኛው ግብዝ ወገን ከነፍሳችን ቆርሰን በመሸጥ ወለምዘለም እያልን ሳንጓዝ እስከ ዛሬው ዕለት ድረስ ለመዝለቅ በቅተናል። በሌላ በኩል ግን አውቀናል፣ መረጃ እናገኛለን፣ ሜዲያውንም ይዘናል፣ ከኛ ሌላ ዋ!” የሚሉት ወገኖች፤ የተመረጡት ሳይቀሩ ስጋዊ የዲቃላ ማንነትና ምንነት እንዳላቸው ግለሰቦች ሆነው መርህ እና አቋም በሌለው እርካሽና ኋላቀር አካሄድ፣ ዛሬ ደጋፊ፣ ነገ ተጠራጣሪ፣ ከነገ ወዲያ ተቃዋሚ ናቸው፤ በዚህም እውንተን ይዘው ቀጥተኛውን መንገድ በመምረጥ ፈንታ እንደ እባብ ጠመዝማዛውን መስመር ተከትለው በመሄድ ሲሰነካከሉ ለማየት በቅተናል። ዛሬም እንኳን ምናልባት ዐቢይ ባይሳካለት በሚል መደናገጥ ሌላውን መሀመዳዊ አታላይ አጋሩን የሶማሌውን ሙስጠፌን ከፍ ከፍ በማድረግ ላይ ናቸው። ዋናው ቁምነገር ስልጣን ከእጃችን መውጣት የለበትም፤ ተዋሕዶ የሆነ የሰሜን ሰው አይምጣብን እንጅ ካስፈለገም ኢትዮጵያ ትፍረስ…” በሚል ዲያብሎሳዊ ምኞት ተጠምደው። ለማ እና ተዋሕዶ እና ዐቢይ ትግሬ ባለመሆናቸው ነበር ዋው! ቲም ለማ፣ ሙሴያችን ቅብርጥሴእያሉ ሲሰግዱላቸው የነበሩት። እነዚህ ሰነፎች በዚህም ጭፍን እና ደካም አካሄዳቸው ብዙዎችን አሳስተዋል፤ ዛሬም በማደናገርና በማሳሳት ላይ ናቸውና በኢትዮጵያ እየተካሄደ ላለው ግልጽ የሃገር ማጥፋት ዘመቻ አብረው ተጠያቂዎች ይሆናሉ ማለት ነው።

ላለፉ ዓመታት ለተፈፀመው የዘር እልቂት ተጠያቂዎቹ ዐቢይ አህመድ፣ ለማ መገርሳ፣ ሽመልስ አብዲሳና መንጋዎቻቸው ናቸው። ከእንግዲህ ወዲህ ለሚገደል አንድ የተዋሕዶ ልጅ ተጠያቂዎቹ ከእነዚህ ወንጀለኞች ጋር የተደመራችሁና ዛሬም ድጋፍ በመስጠት ላይ ያላችሁ ወገኖች ትሆናላችሁ። ተዋሕዶ ነን የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ነንብላችሁ ከገዳይ ዐቢይ ጎን የቆማችሁ ሁሉ ዐቢይ አህመድ አሊን እስከ መስከረም ፩ ድረስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አኝካችሁ ለመትፋት ዝግጁነታችሁን በአደባባይ ካላሳያችሁ ከእነ ዐቢይ አህመድ ጋር ወደ ሲዖል አብራችሁ እንደምትጠረጉ ከወዲሁ እውቁት። ዝም አንላችሁም!

_____________________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ደጉ ግዮን “አነሰን” ሲሉ ጨመረላቸው | ሱዳን በጎርፍ ተጥለቀለቀች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 10, 2020

_____________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Life | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: