Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ዶ/ር አበባ | አብይ የኢትዮጵያ መሪ አይደለም ፥ እርስበርስ እንድንጫረስ ይረዳ ዘንድ የተሾመ የኦሮሚያ መሪ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 4, 2020

👉 /ር አበባን ጊዜ ወስደን በጥሞና እናዳምጣታቸው፤ ብዙ ጠቃሚና እውነተኛ የሆኑ ነጥቦችን አንስተዋል። እንደዚህ በግልጽ ወጥቶ እውነቱን የሚናገሩ ሰዎች በጠፉበት ዘመን፡ በእውነት ሴቶቻችን ወንዶቹን አስንቀዋል። መርህ አልባ፣ አቋም የለሽ ከሆኑትና እንደ ዳክዬ ወለም ዘለም እያሉ ሕዝቡን ወዳልሆነ መንገድ ከሚመሩት ወንዶቻችን የተሻሉ ሆነው ተገኝተዋል። ወይ በራድ ወይ ትኩስ ያልሆኑ፣ ዛሬ ደጋፊ ነገ ተቃዋሚ የሆኑትን ብልህመሳይ “ምሁራንን” መስማት ጆሮ ያቆስላል። በተለይ “ተዋሕዶ ነን” የሚሉትን የገዳዩን ደጋፊዎች በጣም እንቃቸዋለሁ።

/ር አበባ ከተናገሯቸው ነገሮች መካከል

  • 👉 አብይ ለኢትዮጵያ አይሆንም፤ 32 ዓመት ለለፋለት ኦሮሙማ ፕሮጀክት ግን ችሎታውን በተግባር አሳይቷል። ይህንም ሳይደብቅ በግልጽ እየነገረን ነው።
  • 👉 አብይ ለሃገር መሪነት የሚያስችል ብቃትም፣ አቅምም፣ ችሎታም የለውም!
  • 👉 ከስነ ልቦና አንጻር አብይ የአጥፍቶ ጠፊዎች ዓይነት ስብዕና ያለው አደገኛ ሰው ነው
  • 👉 ችሎታ የሌለውን መሪ የሚፈልግ ሕብረተስብ ምንያህል ከዚያ ችሎታ ከሌለው ግለስብ በታች መሆኑን ነው የሚጠቁመን”
  • 👉 የሚያሳፍር የድንቁርና ዘመን ላይ ነን ፥ ትልቁ ወንጀል እነ አብይ እና ወያኔዎች በሃገራችን በጣም ትልቅ ድንቁርና እንዲሰፍን አድርገዋል።
  • 👉 የክርስቲያኖችን ሕይወትን ከሚቀጥፈው ገዳይ አገዛዝ ጋር አትደመሩ፤ በጣም አደገኛ የሆነ አምባገነናዊ የአውሬ ሥርዓት ይፈጠራችሁ ነው!
  • 👉 የደምቢዶሎ ሴት ተማሪዎችን አግተው የሰወሯቸው፤ ሕዝቡን ለማኮላሸት፣ ሞራሉን ለመስበር ከሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች መካከል አንዱ ነው። ይህ ደግሞ አብይ ለኢትዮጵያውያን ምን ያህል ንቀትና ጥላቻ እንዳለው፣ ሕይወታችንም ለእርሱ ከንቱ እነሆነና ዋጋ እንዳልተሰጠው ነው የሚያሳየን። ስለዚህ ሰውዬውን በጭራሽ ልንሸከመው አይገባንም።

_______________________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: