Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for August 4th, 2020

ቤይሩት ባቢ’ሌባኖን በኃይለኛ ፈንጅ ጋየች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 4, 2020

በይፋ አስር ሰው እንደሞተ ቢነገርም ምናልባት በብዙ ሺሆች የሚቆጠሩ ሰዎች ሳይሞቱ እንደማይቀሩ ይገመታል። እኔ የምጠረጥረው የዲያብሎስ አርበኞቹ ሂዝቡላ ከፓኪስታን የኑክሌር መሣርያ ሳያገኙ አልቀሩም ይባላል። ምናልባት እዚህ ግምጃ ቤት ውስጥ ደብቀውት ከሆነ ምንም ነገር የማያመልጣቸው እስራኤሎች ቦታውን አመድ አድርገውታል። ለማንኛውም እህቶቻችንን እንደ ቆሻሻ ወደ መንገድ የወረወረችውን የሊባኖስን ጉዳይ በቅርቡ እንከታተለዋለን።

_______________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

አዲስ አበቤዎችና ኮሮና ሰንደቃችንን ያቃጠሉትን ፖሊሶች በማሳደድ ላይ ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 4, 2020

  • 👉 በጆሞ ክፍለ ከተማ ፖሊሶች ላይ ተኩስ ተከፈተባቸው።
  • 👉 የነፃነትና የሕይወት አርማችንን ሰንደቃችንን እሑድ ዕለት የለከፉት ፖሊሶች በኮሮና ተለከፉ።

እናንት እራስጠል ከሃዲዎች ገና እሳቱ ይወርድባችኋል!

________________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ዶ/ር አበባ | አብይ የኢትዮጵያ መሪ አይደለም ፥ እርስበርስ እንድንጫረስ ይረዳ ዘንድ የተሾመ የኦሮሚያ መሪ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 4, 2020

👉 /ር አበባን ጊዜ ወስደን በጥሞና እናዳምጣታቸው፤ ብዙ ጠቃሚና እውነተኛ የሆኑ ነጥቦችን አንስተዋል። እንደዚህ በግልጽ ወጥቶ እውነቱን የሚናገሩ ሰዎች በጠፉበት ዘመን፡ በእውነት ሴቶቻችን ወንዶቹን አስንቀዋል። መርህ አልባ፣ አቋም የለሽ ከሆኑትና እንደ ዳክዬ ወለም ዘለም እያሉ ሕዝቡን ወዳልሆነ መንገድ ከሚመሩት ወንዶቻችን የተሻሉ ሆነው ተገኝተዋል። ወይ በራድ ወይ ትኩስ ያልሆኑ፣ ዛሬ ደጋፊ ነገ ተቃዋሚ የሆኑትን ብልህመሳይ “ምሁራንን” መስማት ጆሮ ያቆስላል። በተለይ “ተዋሕዶ ነን” የሚሉትን የገዳዩን ደጋፊዎች በጣም እንቃቸዋለሁ።

/ር አበባ ከተናገሯቸው ነገሮች መካከል

  • 👉 አብይ ለኢትዮጵያ አይሆንም፤ 32 ዓመት ለለፋለት ኦሮሙማ ፕሮጀክት ግን ችሎታውን በተግባር አሳይቷል። ይህንም ሳይደብቅ በግልጽ እየነገረን ነው።
  • 👉 አብይ ለሃገር መሪነት የሚያስችል ብቃትም፣ አቅምም፣ ችሎታም የለውም!
  • 👉 ከስነ ልቦና አንጻር አብይ የአጥፍቶ ጠፊዎች ዓይነት ስብዕና ያለው አደገኛ ሰው ነው
  • 👉 ችሎታ የሌለውን መሪ የሚፈልግ ሕብረተስብ ምንያህል ከዚያ ችሎታ ከሌለው ግለስብ በታች መሆኑን ነው የሚጠቁመን”
  • 👉 የሚያሳፍር የድንቁርና ዘመን ላይ ነን ፥ ትልቁ ወንጀል እነ አብይ እና ወያኔዎች በሃገራችን በጣም ትልቅ ድንቁርና እንዲሰፍን አድርገዋል።
  • 👉 የክርስቲያኖችን ሕይወትን ከሚቀጥፈው ገዳይ አገዛዝ ጋር አትደመሩ፤ በጣም አደገኛ የሆነ አምባገነናዊ የአውሬ ሥርዓት ይፈጠራችሁ ነው!
  • 👉 የደምቢዶሎ ሴት ተማሪዎችን አግተው የሰወሯቸው፤ ሕዝቡን ለማኮላሸት፣ ሞራሉን ለመስበር ከሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች መካከል አንዱ ነው። ይህ ደግሞ አብይ ለኢትዮጵያውያን ምን ያህል ንቀትና ጥላቻ እንዳለው፣ ሕይወታችንም ለእርሱ ከንቱ እነሆነና ዋጋ እንዳልተሰጠው ነው የሚያሳየን። ስለዚህ ሰውዬውን በጭራሽ ልንሸከመው አይገባንም።

_______________________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጀነሳይድ እየተፈጸመ ዳንኪራ? ልትጠፋ ያለች ከተማ በሃዘን ግዜ ዳንኪራ ታበዛለች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 4, 2020

ከሺህ በላይ ክርስቲያን ወገኖች በተጨፈጨፉበት ማግስት፣ ዓብያተ ክርስቲያናት እንደ ችቦ በጋዩበት ማግስት፣ መኖሪያ ቤቶቻቸውን ያጡ ሦስት ሺህ የሚጠጉ የተዋሕዶ ልጆች በየዓብያተ ክርስቲያኑ ተጠልለው በሚገኙበት በዚህ ክፉ ወቅት፣ ለአዲስ አበባ ነዋሬዎች ሕይወታቸውን በነፃ የሰጡት እነ እስክንድር እስር ቤት ውስጥ ለረሃብ፣ ድብደባና ኮሮና በተጋለጡበት በእነዚህ ቀናት፣ የምስኪን ገብሬ ሴት ልጆች ታግተው በተሠወሩበት በዚህ ዘመን ይህን ያህል ደስታ ከየት ነው ሊገኝ የሚችለው?

ያውም ወራዳና ገዳዩ አገዛዝ ለጠራው “የድጋፍ ሰልፍ?”፣ ገዳዩ “ደግፉኝ፣ ካልደገፋችሁኝ አስራችኋለሁ፣ እገድላችኋለሁ!” የሚልበት ዘመን ላይ ነው የምንገኘው እኮ! ሁሌ ድጋፍ የሚሻው ገዳይ ዐብይ እራሱ በዚህ ያልተጠበቀ ድጋፍ ሳይናደድ አልቀረም፤ የገዳይ ባሕርይ ነውና! ለዚህም ይመስላል ፖሊሶቹ ሰንደቃችንን እንዲቀሟቸው ትዕዛዝ የሰጣቸው።

አቤት ውርደት! አቤት ቅሌት! ይህ በጣም የሚያስቆጣ ነገር እኮ ነው፤ ጃል! ምን ዓይነት መርገም ነው?! እንደው እንኳን የዋቄዮአላህ ልጆች ሜንጫ ከሰማይ እሳት ቢወርድብን ሊያስገርመን ይችላልን? በፍጹም!

ከአራት ዓመታት በፊት በአሜሪካዋ ከተማ በኦርላንዶ ፍሎሪዳ “ፑልስ” በተባለው የግብረሰዶማውያን የዳንኪራ ቤት ውስጥ ቦምብ ፈንድቶ 49 የሚሆኑት ግብረስዶማውያን እንደ ዝንብ ሲረግፉ የተረፉት ግብረሰዶማውያን “ሂ! !” በማለት ጭፈራቸውን ያለማቋረጥ ቀጥለውበት ነበር። እግራችው ሥር ሙታን እየተንጠባጠቡ ይደንሳሉ፤ በዓለም ፍጻሜ ይጨፍራሉ!

ሰዶም እና ጎሞራ ሊጠፉ የቻሉበት ምክንያት እኮ ነውራቸው ሳያሳፍራቸው ዳንኪራ በማብዛታቸው ነበር። በደላቸውን እንደ መላካም ነገር በመናገር፣ ሃጥያታቸውን እንደ ጽድቅ በማውራታቸው፣ ነውራቸውን በአደባባይ ያለ ህፍረት በመግለጻቸው ነበረ የጥፋት እሳት ወርዶ ያጠፋቸው። ዛሬም ገዳይን እንደ ጀግና፣ በዳይንና ጨቋኝን እንደ መልካም አስተዳዳሪ፣ በመቁጠር መልሰው መላልሰው ነውራቸውን ይነግሩናል። እኛም ስንመልስ ተዉ…. ዛሬ እዩኝ እዩኝ ነገ ደብቁኝ ይመጣል፣ ግዜ ያነሳውን ግዜ ይጥለዋል፣ መግቢያ እስቀሚጠፋባችሁ ድረስ የጭንቅ ቀን ይመጣባችኋል፣ እያለን ሰሚ ከተገኘ ከቅድመ አደጋ በፊት ማሳሰቢያዎችን ከመናገር ውጪ ሌላ የምናደርገው ነገር የለንም። ሁሉም ነገር ያሳዝናል!

________________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: