Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

መድኃኔ ዓለም | ተዋሕዷውያን ለተዋሕዶ ልጆች በተለየ መልክ መልካም ማድረግ ይገባቸዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 2, 2020

[፩ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕራፍ ፭፥፰]

ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።”

ብዙዎች በሃይማኖት ከሚመሳሰሏቸው ጋር በማበርና አንድ ከመሆን ይልቅ ለጠላቶቻቸው ሲቆሙና ድጋፍ ሲሰጡ ይታያሉ። ይህ ትልቅ ስህተት ነው! የተዋሕዶ ልጅ ከሌሎች ማስቀደም ያለበት እንደርሱ ተዋሕዶ የሆኑትን ወገኖቹን ብሎም በተለየ መልክ መልካም አያያዝ ሊያደርግ የሚገባው ለመድኃኔ ዓለም ልጆች መሆን አለበት ፤ በተለይ በዚህ ከማይመስሉን ሁሉ መራቅ በሚገባን ዘመን። ማንነታቸውን ባለማወቅ ወይም እራሳቸውን በመጥላት፣ ወይም በምዕራቡ ለብ ለብ ለዘብተኝነት ስልተወሰዱና መሃልስፋሪያዊ ማንነት በመያዛቸው “ሁሉን አቃፊ” ለመሆን ሲወራጩ ይታያሉ። “ገለልተኝነት”፣ “ሚዛናዊነት” እና “ሁሉን አቃፊነት” ከላይ ቆንጆ የሚመስሉ ነገር ግን ውስጣቸው ከንቱ የሆኑና በዓላማየለሽኝነት ላይ የተመረኮዙና በስንፍና ቅመም የተከለሱ የለዘብተኛነት መገለጫ ከኮሮና የከፉ በሽታዎች ናቸው። አንድ ዜጋ ወይ ኢትዮጵያዊ ነው ወይም አይደለም ፥ ወይ ከተዋሕዶ ነው ወይም አይደለም ፥ ወይ ጥሩ ወይም መጥፎ ፥ ወይ በስትግራ ፣ ወይም በስተቀኝ ፥ ወይ በራድ ወይም ትኩስ ፣ ወይ ከእውነት ጋር ወይም ከሐስት ጋር ፥ ወይ ከበጉ ጋር ወይም ከፍየሎች ጋር ፥ ወይ ከመድኃኔ ዓለም ጋር ወይም ከዋቄዮአላህ/አዱኛ ፈይሳ ጋር።

አህዛብ የዋቄዮአላህ ልጆች ምንም እንኳን ፍቅረቢሶችና ብቻቸውንም ሲቀሩ እርስበርስ የሚነካከሱ ግብዞች ቢሆኑም ቅሉ ለጋራ ግባቸው ሲሉ ግን እርስበርስ ሲተባበሩ ይታያሉ፤ ነገራቸው ሁሉ በጥላቻ ላይ የተመረኮዘ ቢሆንም ግን ለዓላማቸው ሲሉ በአንድነት ይቆማሉ። ዓላማቸው ኢትዮጵያን፣ ተዋሕዶ ባሕሏን፣ ቁንቋዋን እና ሃይማኖቷን ለማጥፋት ስለሆነ ኢትዮጵያና አምላኳ እስካሉ ድረስ ከዚህ ዓላማቸው ፎቀቅ አይሉም። ልክ እንደ ነቀርሳ፤ የሚመገበው ጤናማ ሕዋሳት እስካሉ ድረስ እነርሱን እይተመገበ ይስፋፋል፤ ጤናማው ህዋሳት ሲያልቅ ነቀርሳው እራሱን በልቶ ይጠፋል።

የዘመናችን ተዋሕዷውያን ተገቢ በሆነ መልክ እርስበርስ እንዳይተባበሩና የራሳቸው የሆነውን ነገር ሁሉ እንዳያስቀድሙ እንቅፋት የሆኑባቸው ነገሮች፦ ማንነታቸውን በሚገባ አለመገንዘባቸው፣ መድኃኔ ዓለም የሰጣቸውን ፀጋና በረከት ዋጋ ባለማወቃቸው፣ ሃገራቸውና ሃይማኖታቸው ያሰቀመጧቸውን ተልዕኮዎችና ዓላማዎች ባለመከተላቸው እንዲሁም የአምላካቸውንና የራሳቸውን ጠላት በብልጠት እንዲያውቁ ባለመፍቀዳቸው ብሎም ለመዋጋት ቁርጠኝነት ባለማሳየታቸው ነው።

እስኪ እናስበው፤ የዋቄዮአላህ ልጆች ፍቅርአልባ በሆነ የጥላቻ መንፈስ ተነሳስተው ዲያብሎሳዊ አላማዎቻቸውን ሁሉ ለጊዜውም ቢሆን አንድ ባንድ በማሳካት ላይ ናቸው ፥ በሌላ በኩል፡ በፍቅር የተሞሉት የመድኃኔ ዓለም ልጆች ኃያሉን አምላካቸውን አጥብቀው በመያዝና ቅዱሳን ሠራዊቱንም ከጎናቸው በማሰለፍ እርስበርስ እየተሳሰቡና እየተደጋገፉ በአንድ ዓላማ ቢኖሩ ምን ያህል መሬት አንቀጥቅጥ ውጤት ሊያመጡ እንደሚችሉ። እስኪ እናስበው! አዎ! የመድኃኔ ዓለም ጠላት የሆኑት የዋቄዮአላህ ልጆች 150 ዓመት አይደለም አንድ ቀን እንኳን አይቆዩም ነበር።

____________________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: