ተወዳጁ የኮምፒውተር ጨዋታ ‘ሥልጣኔ ፮’ | ኢትዮጵያ በሚኒልክ መሪነት ዓለምን ትገዛለች
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 24, 2020
ጨዋታው Civilization VI ((CIV6) / ሥልጣኔ ፮ – የኢትዮጵያ ጥቅል ብሎ ተብሎ ይጠራል።
የዚህ በጣም ተወዳጅ የሆነውና በትናንትናው ዕለት ለገበያ የወጣው የኮምፒውተር ጨዋታ ጥቅል ይዘት ዳግማዊ አፄ ምኒልክን እንደ ኢትዮጵያ መሪ ያስተዋውቃል። ኢትዮጵያ ሳይንስ እና ባህሏን ለማሳደግ እምነቷን በማመንጨት እና የምኒልክን “የሚኒስትሮች ምክር ቤት” ችሎታ በመጠቀም ኢትዮጵያ በተራራማ ቦታዎች ላይ በተገነቡ ከተሞች ላይ ታተኩራረች።
ይህ ጨዋታ “ጨዋታ” ብቻ አይደለም፤ ዛሬ መውጣቱም በአጋጣሚ አይደለም! ጊዜው መገጣጠሙ በጣም አስገራሚ ነው። እንግዲህ ለኢትዮጵያ አንገዛም ያሉት የኢትዮጵያ ጠላቶች ያብዳሉ! ይቃጠላሉ! የጨዋታውን ባለቤት ካልገደልን በማለት እየተንፈራፈሩ ወደ ጥልቁ ይገባሉ!
ለተጨማሪ መረጃ፦ https://www.epicgames.com/store/en-US/product/sid-meiers-civilization-vi/ethiopia-pack
Leave a Reply