Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

መላው ዓለም የኢትዮጵያ ካላንደር ነው ትክክለኛው፤ ቅዳሜ ለ፲፮ ሰዓት እንፁም እያለ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 18, 2020

  • 👉 በመጨው እሑድ አሮጌው ዘመን ይፈጸማል፤ ኋለኛው ዘመን በአዲሱ ዘመን ይተካል
  • 👉 በ ፪ሺ፲፪ (2012) .ም ምድራችንን ከባባድ ፈተናዎች ገጥመዋታል

ምድራችን በእኛ አቆጣጠር በ ፪ሺ፲፪ (2012) .. በፈረንጆቹ 2020 .. ላይ በከባድ ፈተናዎች ውስጥ እያለፈች ነው። እጅግ ጥንታዊው ከ1200 ዓመታት በፊት የነበረው የማያ የዘመን ቀመር ዐዲስ ያልተለመደ ክስተት የሚጀምርበት ዑደቱ የሚጠናቀቅበት የተፈጥሮ አደጋዎች በዝተው የሚታዩበት 2012 ላይ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ ብዙ ዓለም ዐቀፍ ተመራማሪዎች በፈረንጆቹ 2012 ላይ መስሏቸው ብዙ አስተያየት በጊዜው ሲሰጡ ቆይተው ነበር። 2012 የሚል አስፈሪ ፊልም ከማያ የዘመን ቀመር በመነሣት የፈረንጆቹ ፪ሺ፲፪ (2012) ከመድረሱ ፫/ 3 ዓመት ቀድሞ በ2009 ላይ በሆሊውድ ተሠርቶ በሮናልድ ኤመሪክ ዳይሬክት ተደርጎ ሁላችንም ተመልክተነዋል።

በፈረንጆቹ ፪ሺ፲፪ (2012) /ሚ መለስ ዜናዊን ጨምሮ ሦስት አፍሪቃውያን መሪዎች አርፈዋል/ተገድለዋል፤ ሆኖም ሌሎች ብዙ ክስተቶች ሳይከሠቱ የእኛው ፪ሺ፲፪ (2012) .ም ላይ እንገኛለን። ፪ሺ፲፪ (2012) ዓመት ግን ገና ከመጀመሩ ለዓለማችን በጣም አስደንጋጭ ነበር። በዚህ ዓመት በመላው ዓለም ኮሮናን ጨምሮ በርካታ አስደንጋጭና አስደናቂ ነገሮች በመታየት ላይ ናቸው።

በመጭው እሑድ ሰኔ ፲፬ / ፪ሺ፲፪ (14/2012 .) June 21 – 2020

ከኢትዮጵያውያን ጋር ዝምድና ሊኖራቸው ይችላል ተብለው የሚነገርላቸው የአሜሪካዎቹ ማያዎች አሮጌው ዘመን ይፈጸማል፤ ኋለኛው ዘመን በአዲሱ ዘመን ይተካልይላሉ።

👉 ሰኔ ፲፬ / ፪ሹ፲፪ (14/2012 .) አቡነ አረጋዊ

ሁሉም ነገር ከኢትዮጵያ ቀመርና ከመጭው የፀሐይ ግርዶሽ ጋር መገጣጠሙ የሚገርም ነው።

🌑 ፪ሹ፲፪ /2012 .ም ግርዶሽ የሚታየው፡

  • ሰኔ ፲፬ / ፪ሺ፲፪ (14/2012 .) June 21 – 2020
  • በግርዶሹ 600 ሰዓት የሚፈጅ ጨለማ ይታያል፡፡
  • በመላ ኢትዮጵያ ይታያል፡፡
  • በተለይ ወለጋ፣ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ አላማጣ፣ ኢንጂባራ 98% ጨለማ ሆኖ ይታያል፡፡
  • የዓለምን አሰራር የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካን፣ የከፍተኛ የተፈጥሮ ኃይል ሊገኝ ይችላል ብለው ሳንቲስቶች ሀሳባቸውን እየሰነዘሩ ይገኛሉ፡፡
  • ከምዕራብ ኢትዮጵያ እስከ ሰሜን ኢትዮጵያ ድረስ ግርዶሹ ይታያል፡፡
  • ፀሐይ 98% ትሸፈናለች፡፡

🌑 የሚታይበት እና የሚያበቃበት፡

ከማዕከላዊ አፍሪካ ከኮንጎ ይነሳል፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ የመን፣ ፓኪስታን፣ ታይዋን፣ ንድና ቻይናን አቋርጦ ፓስፊክ ውቂያኖስ ላይ ያበቃል፡፡

🌑 ሙሉ ግርዶሹ የሚታይበት ወቅት

  • ከሌሊቱ ሰኔ 14/2012፲፬ / ፪ሺ፲፪ (14/2012 .) June 21 – 2020 .
  • – 1100 ሰዓት ይጀምራል፣
  • ከጠዋቱ 1245 እስከ ቀኑ 633

👉 ማስጠንቀቂያ፡

  • በዓይን ለማየት አይቻልም ዐይን ያሳውራል፣
  • በሱቅ ውስጥ የሚሸጥ መነጽር መጠቀም አይገባም፡፡
  • ለፀሐይ ግርዶሽ ተብሎ የተዘጋጀ መነጽር አለ፡፡
  • መነጽሩ አገር ውሰጥ አይገኝም፡፡
  • ለፀሀይ ግርዶሽ የሚሆን መነፀር አለን ከሚሉ አጭበርባሪዎች ጥንቃቄ ያድርጉ
  • ሲጨልም ማየት እንችላለን ነገር ግን ያለመነጽር ለማየት አንሞክር፣በጣም ጥንቃቄ ሊታከልበት ይገባል
  • ዐይናችን ሊፈስ ይችላል

የነገ ሰው ይበለን!

_______________________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: