ተክልዬ የሃይማኖትን ገዳዮች ዛፍ ከሥሩ ይነቅሉታል ፥ የኢትዮጵያን ጠላትም በእሳት ይጠርጉታል
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 1, 2020
አባታችን ተክልዬ፤ ልጅዎንና እህታችንን ተማሪ ሃይማኖትን በምን ዓይነት አሰቃቂ መልክ እንደገደሏት መዝግበዋልና፡ ተጨማሪ ወንጀል ከመፈጸማቸው በፊት ገዳዮቿን ዛሬውኑ ከምኒሊክ ቤተ መንግስት አውጥተው ኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ ውስጥ ይክተቱልን። አሜን!
👉 መታሰቢያነቱ ለ እህታችን ሃይማኖት በዻዻ!
የአባታችን የአቡነ ተክለ ሐይማኖት ረድኤትና በረከት፡ ምልጃና ጸሎት በሀገራችን በኢትዮጵያ እንዲሁም በመላው ሕዝበ ክርስቲያን ላይ አድሮ ይኑር፡ ሀገራችንን ሊያጠፋ የተነሳውን መንፈስ ያጥፉልን፤ ለዘላለሙ አሜን!
ተክለ ሐይማኖት ፀሐይ
የክርስቲያኖች መመኪያ
ተክለ ሐይማኖት ጻድቅ
የእንባችን ማበሻ
ከፈጣሪ የምታስታርቅ
ሰባሊ ወንጌል መናኝ
ሰማያዊ አርበኛ
በጸሎትህ ትሩፋት
ፀሐይ ያበራህ ለእኛ
ቅዱስ አባትችን ሆይ
ሀጢአታችን ስለበዛ
በቃልኪዳንህ አማልደን
በነፍሳችን ሁናት ቤዛ።
አደራ!
Leave a Reply