የትናንቶቹ አባቶቻችን ቅዱስ ጊዮርጊስን መከታ አድርገው ታቦቱን ይዘው ድል አደረጉ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 31, 2020
ከሁለት ቀናት በፊት በማርያም ዕለት ስለ አዲስ አበባ የታየኝን አስገራሚ ህልም ከማውሳቴ በፊት ይህ ልዩ የሰንበት እይታየ ነው፦
በጣም የሚገርም ነው፤ ልክ በአድዋው ታሪካዊ ድል ማግስት ነበር የኢትዮጵያ ውድቀት የጀመረው። የአደዋው ድል የአሁኑን ከሃዲ ትውልድ አፍርቷል! ረባሽ ዓረፍተ ነገር፡ አደል?!
ግን ምክኒያቱ፦ በወቅቱ ታይቶ በነበረው አስከፊ ረሃብና እስካፍንጫው በታጠውቀው በአህዛብ ጠላት ላይ ድል ያጎናጸፈውን እግዚአብሔር አምላኩን በመክዳት ለስጋዊው የአህዛብ ዓለም እውቀትና ጥበብ እጁን በመስጠቱ የቀጣዮቹን ሦስትና አራት ትውልዶች ለመፈጠር በመብቃቱ፤ በዚህም ሃገር አጥፊ ስጋዊ የዲቃሎች መንጋ ስልጣኑን እንዲቆጣጠረውና የሃገሪቱንም ውድቀት እንዲያፋጥነው ዋናውን ሚና በመጫወቱ ነበር/ነው። ልከ እንደ ምስጋና–ቢሶቹ እስራኤላውያን!
ወቅቱ አሁን ያለው አራተኛው ከሃዲ ትውልድ ተገርስሶ በቅርቡ የኢትዮጵያ ትንሣኤ የሚታይበት ወቅት ነው። ነገር ግን፡ አሁንም ይህ ትውልድ ለአህዛብ ኤዶማውያን እና እስማኤላውያን ምድራዊ እውቀትና ጥበብ መገዛቱን እስካላቆመ ድረስና ይህ አሁን የሚታየው አራተኛው ዲቃላ ትውልድ ስጋዊ ማንነቱንና ምንነቱን በመካድ፣ ንሥሐ ገብቶ የቀደሙ አባቶቹን ለድል ያበቃቸውን እግዚአብሔርን እና ዘላለማዊ ሕጉን ካልተከተለ ሰቆቃው፣ ባርነቱ፣ ሰቆቃውና ውድቀቱ ይቀጥላል። ይህን የማያይ ዛሬም ስጋዊ ነው!
የፈረሰኛው ሰማእት የቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤትና ምልጃ አይለየን!
Leave a Reply