አውሬው መንግስት ቤተ ክርስቲያንን በድጋሚ ለማዘጋት የታማሚውን ቁጥር ከፍ ያደርገዋል
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 29, 2020
ይህ አጥንትን አለምላሚ የእመቤታችን ክብረ በዓል በ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም / ፭ኪሎ አዲስ አበባ ፥ መስከረም ፳፩ / ፪ሺ፲፪ ዓ.ም ነበር የተካሄደው።
የዲቃላው ግራኝ አህመድ አውሬ መንግስት ተቀዳሚ ፍልሚያ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጋር እንደሆነ የሚጠራጠር የተዋሕዶ ልጅ ካለ በጣም አዝናለሁ።
አሁን የአህዛብ ረመዳን አልቋል፤ ከንቱዎቹ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችም የፀሎትና ቅዳሴ መርሐ ግብርን ማስተላለፋቸውን አቁመዋል (እሰየው!) … ስለዚህ በመጪዎቹ ቀናትና ሳምንታት የጤና ሚንስትሯ ወይዘሮ ኮሮና በቀን አንዴ ብቅ እያለች “በወረርሽኝ ታሟል” የሚባለውን ሰው ቁጥር ከፍ፣ ከፍ በጣም ከፍ እያደረጉ ይመጣሉ። ዋናው ዓላማቸው ለዲያብሎሳዊ ተግባራቸው እንቅፋት የሆነችባቸውን ቤተ ክርስቲያንን እንደገና ማዘጋት ነው።
እንግዲህ ልብ በሉ፤ አደጉ በተባሉት አገራት አሁን የወጣ መረጃ እንደሚጠቁመን፤ “ስዎች በተቀራረቡና በተገናኙ ቁጥር በኮሮና ቫይረስ የመጠቃት ዕድላቸው በጣም ዝቅ ያለ ነው።” ስለዚህ ሰዎች በተቃራኒው አሁን በጣም ቢቀራረቡና ቢገናኙ ይመረጣል ማለት ነው!
በአዲስ አበባ ልደታ ማርያም (ሜክሲኮ) አካባቢ ችግር መፍጠራቸው ያለ ምክኒያት አይደለም። ላለፈው መስከረም ፬/4 ተጠርቶ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ በዋናነት ያካሄደችው ቅድስት ልደታ ማርያም ቤተክርስቲያን ብቻ ነበረች። የመንፈሳውያኑ ኢትዮጵያውያን ጠላት የሆነው የግራኝ አህመድ መንግስት ይህን ያውቀዋል፣ ይህን ደግሞ በጣም ይፈራዋል። ስለዚህ አሁንም የእንቅስቃሴ እገዳውን በልደታ ሠፈር ጀምሯል። ባለፈው ኅዳር ወር እነ ታከለ ዑማ ልክ በአንቦ ተዋሕዷውያን ላይ እንደሚያደርጉት በአዲስ አበባም የመረዟቸው የተዋሕዶ ህፃናት ተማሪዎች የሚገኙት በልደታ ነው። እዚህ ገብተው ያንብቡ፦ የሞት ፍሬ በ ፍሬህይወት | ወገን፡ እነ ታከለ ልጆቻችሁን እየመረዙባችሁ ነው”
ሌላ የሚገርመው ነገር፤ ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ የሚገኘው የሜክሲኮ ኤምባሲ ለግብረ–ሰዶማውያን የድጋፍ መግለጫ ማውጣቱ ነው። በአጋጣሚ?
እናታችን ቅድስት ማርያም ከሚታየው እና ከሚሰማው ክፉ ነገር ሁሉ ትጠብቀን፣ ረድኤትና በረከቱ፣ ምልጃና ፀሎቷ አይለየን። አሜን! አሜን! አሜን!
Leave a Reply