Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2020
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    25262728293031
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for May 28th, 2020

ደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 28, 2020

  • 👉 ቅድስተ ቅዱሳን
  • 👉 ሰዓሊተ ምሕረት
  • 👉 ተላኪተ እግ ዚአብሔር ወ ሰብእ
  • 👉 ቤዛዊተ አለም
  • 👉 ኪዳነ ምህረት
  • 👉 ንጽሕይተ ንጽሐን
  • 👉 ድንግል በክልኤ
  • 👉 ድንግል ወእም
  • 👉 ፍጽምተ ሥጋ ወነፍስ
  • 👉 በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የፀናች
  • 👉 እመብርሃን
  • 👉 ምልዕተ ጸጋ
  • 👉 እመቤታችን
  • 👉 ወላዲተ አምላክ

__________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

የዘረኝነት አጋንንት | በኒው ዮርክ መናፈሻ ነጯ ያለምንም በቂ ምክኒያት በጥቁሩ ላይ ፖሊስ ጠራችበት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 28, 2020

በኒው ዮርክ ማዕከላዊ የመናፈሻ ፓርክ ከእህቱ ጋር እየተዘዋወረ ወፎችን ፎቶ የሚያነሳው ጥቁር አሜሪካዊ ክርስቲያን ኩፐር/ Christian Cooper በገመድ ያልተያዘውን ውሻዋን የለቀቀችውን ነጯን ኤሚ ኩፐር / Amy Cooper ውሻዋን እንድታስር ሲጠይቃት ነበር የኒው ዮርክ ከተማ ፖሊስ መምሪያን ደውላ ድራማ የሠራችው፡፡

ግጭቱ የተከሰተው በኒው ዮርክ ከተማ ማዕከላዊ ፓርክ ክፍል ሲሆን ውሾች እንዳይለቀቁና ታስረው እንዲንቀሳቀሱ የሚያዙ ህጎች ባሉበት የመናፈሻው ጫካማ የሆነ ቦታ ላይ ነው።

ቪዲዮውን የቀረጸችው የክርስቲያን ኩፕር እህት ሜሎዲ ኩፐር / Melody Cooper ስትሆን፡ ወንድሟ መቀረጽ የጀመረውና ግጭቱም የተቀሰቀሰው ኤሚ ኩፐር ውሻዋን ለማሠር ፈቃደኛ ሳትሆን በመቅረቷ ነበር።

ከቪዲዮው እንደሚሰማው ክርስቲያን ኩፐር ኤሚ ኩፐር ወደ እሱ እንዳትቀርብ ጠየቃት ፣ እናም ልውውጡ ተባባሰ። ከዚያ ለፖሊስ በመደወል ጥቁር ሰው ሕይወቷን አደጋ ላይ እንደጣለው ነገረቻቸው ፡ ሴትየዋ በ 911 ጥሪዋ ላይ በተደረገው ንግግር የክርስቲያን ኩፐርን ዘር ደጋግማ እየገለጸች “ፖሊሶች ወዲያውኑ እንዲላኩ” ጠይቃለች፡፡

አንድ አፍሪካዊ አሜሪካዊ ሰው እዚህ አለ ፣ በቪዲዮ እየቀረጸኝ እኔንና ውሻዬን ስጋት ላይ ጥሎናል” አለች ፡፡ ቪዲዮው ሴቲቱን ሲያስፈራራት አያሳይም፡፡

በዚህ መላዋ አሜሪካን ኡ!! ባሰኝ ቪዲዮ ምክኒያት ሴትዮዋ አሁን ከፍተኛ ደሞዝ ከሚሰጠው ስራዋ ተባርራለች፡፡ አሁን ህይወቴ ተበላሸ፤ ይቅርታ!” ማለት ጀምራለች። ሰውዬም ይቅርታዋ እውነተኛ ከሆነ ይቅር እላታለሁብሏል።

በትንሽና በማይረባ ነገር በየትኛውም ቀን ሳናስበውና ሳንዘጋጅበት ሕይወታችን ግልብጥብጥ ሊል እንደሚችል ነው ይህ ታሪክ የሚያስተምረን፤ በተለይ እንደ ዘረኝነት ያለ ጋኔን ተሸካሚዎች ከሆንን።

የሚገርመው፦

  • 👉 ፎቶው ላይ እንደሚታየው ነጯና ጥቁሩ የሆነ የሚመሳሰል ነገር አላቸው
  • 👉 የሁለቱም ስም ኩፐር / Cooper“ ነው

_________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Life | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ዐረገ በስብሐት ዐረገ በእልልታ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 28, 2020

ዕርገት› በግእዝ ቋንቋ ማረግ፣ ከታች ወደ ላይ መውጣት ማለት ሲኾን የጌታችን ትንሣኤ በተከበረ በዐርባኛው ቀን የሚውለው ዐቢይ በዓልም ‹ዕርገት› ይባላል (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፯፻፷)፡፡ በዓለ ዕርገት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለዐርባ ቀናት በግልጽም በስውርም ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳት አንስት መጽሐፈ ኪዳንን፣ ትርጓሜ መጻሕፍትን፣ ምሥጢራትን፣ ሕግጋትንና ቀኖናተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተምር ቆይቶ ወደ ቀደመ ዙፋኑ ወደ ሰማይ በክብር በምስጋና ማረጉን በደስታ የምንዘክርበት ዐቢይ በዓል ነው፡፡ በዓለ ዕርገት በቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉ የሚውልበት ዕለት ሐሙስን ባይለቅም ቀኑ ግን የአጽዋማትና በዓላት ማውጫ ቀመርን ተከትሎ ከፍ እና ዝቅ ይላል፡፡

በዚህ መሠረት የዘንድሮው በዓለ ዕርገት ግንቦት ቀን ፳፻፲ .ም ይውላል ማለት ነው፡፡ ከጌታችን የዕርገት በዓል ጀምሮ (ከበዓለ ትንሣኤ ዐርባኛው ቀን) እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ ዋዜማ (ዐርባ ዘጠነኛው ቀን) ድረስ ያለው ወቅትም ‹ዘመነ ዕርገት› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዘመነ ዕርገት ውስጥ በሚገኘው እሑድ (ሰንበት) ሌሊት ሊቃውንቱ የሚያደርሱት መዝሙርም ‹‹በሰንበት ዐርገ ሐመረ›› የሚል ሲኾን ይኸውም ጌታችን በሰንበት ወደ ታንኳ በመውጣት ባሕርንና ነፋሳትን እንደ ገሠፀ፤ ሐዋርያቱንም ‹‹ጥርጥር ወደ ልቡናችሁ አይግባ፤ አትጠራጠሩ›› እያለ በሃይማኖት ስለ መጽናት እንዳስተማራቸው፤ እንደዚሁም ወንጌልን ይሰብኩ፣ ያስተምሩ ዘንድ በመላው ዓለም እንደሚልካቸው፤ በሰማያዊ መንግሥቱ ይኖሩ ዘንድም ዳግመኛ መጥቶ እንደሚወስዳቸው የሚያስገነዝብ መልእክት አለው (ሉቃ.፰፥፳፪፳፬፤ ዮሐ.፲፬፥፪፤ ፳፥፳፩)፡፡

በበዓለ ዕርገት ሊቃውንቱ ሌሊት በማኅሌት፣ በዝማሬ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡ ሥርዓተ ማኅሌቱ እንዳበቃ የሚሰበከው የነግህ ምስባክም፡‹‹ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ ናሁ ይሁብ ቃሎ ቃለ ኃይል›› የሚለው የዳዊት መዝሙር ሲኾን፣ ቀጥተኛ ትርጕሙ፡ ‹‹በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ (ላረገ) ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ የኀይል የኾነውን ቃሉን እነሆ ይሰጣል፤›› ማለት ነው (መዝ.፷፯፥፴፫)፡፡ ምሥጢራዊ ትርጕሙ ደግሞ ‹‹ነፍሳትን ይዞ ከሲኦል ወደ ገነት ለወጣ፤ አንድም በደብረ ዘይት በኩል ላረገ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ›› የሚል መልእክት አለው፡፡ እንደዚሁም ጌታችን በዐረገ በዐሥረኛው ቀን ‹የኀይል ቃል› የተባለ መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት እንደ ላከላቸው፤ በተጨማሪም ጌታችን በሕያዋን እና በሙታን (በጻድቃን እና በኃጥአን) ላይ ለመፍረድ ዳግም እንደሚመጣ፤ እኛም ይህንን የጌታችንን የማዳን ሥራ እያደነቅን ለእርሱ ምስጋና፣ ዝማሬ ማቅረብ እንደሚገባን ያስረዳናል – ምስባኩ፡፡

በነግህ (ከቅዳሴ በፊት የሚነበበው) ወንጌል ደግሞ ሉቃስ ፳፬፥፵፭ እስከ መጨረሻው ድረስ ያለው ኃይለ ቃል ነው፡፡ ቃሉም ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት እንደሚወርድ፣ የሰውን ልጅ ለማዳን ሲል መከራ እንደሚቀበል፣ እንደሚሞት፣ ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሣ፣ ወደ ሰማይ እንደሚያርግና ዳግም እንደሚመጣ በነቢያት የተነገረው ትንቢት መፈጸሙን፤ ለዚህም ቅዱሳን ሐዋርያት ምስክሮች መኾናቸውን ማለትም በመላው ዓለም እየዞሩ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ እንዲሰብኩና በሰማዕትነት እንዲያልፉ፤ እንደዚሁም ሰማያዊ ሀብትንና ዕውቀትን እስኪያገኙ ድረስ በኢየሩሳሌም እንዲቆዩ መታዘዛቸውን ያስረዳል (ትርጓሜ ወንጌል)፡፡ ይህ ምሥጢር ለጊዜው የሐዋርያትን ተልእኮ የሚመለከት ይኹን እንጂ ለፍጻሜው ግን ዅላችንም ቅዱሳት መጻሕፍት የተናገሩትን ቃል አብነት አድርገን የእግዚአብሔርን ሰው መኾንና የማዳኑን ሥራ አምነን፣ ሌሎችንም በማሳመን በሃይማኖታችን ጸንተን መኖር እንደሚገባን፤ እግዚአብሔር አምላካችን ኃይሉን፣ ጸጋውን፣ ረድኤቱን እንዲያሳድርብንም ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን መለየት እንደሌለብን የሚያስገነዝብ መልእክት አለው፡፡

በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ዕብራውያን ፩፥፩ እስከ ፍጻሜው ድረስ፤ ከሌሎች መልእክታት ደግሞ ፩ኛ ጴጥሮስ ፫፥፲፰ እስከ ፍጻሜው፤ የሐዋርያት ሥራ ፩፥፩፲፪ ሲኾኑ፣ ምስባኩም ‹‹ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ›› የሚለው ነው፡፡ ትርጕሙም ‹‹በዕልልታና በመለከት ድምፅ ላረገ ለአምላካችን፣ ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና አቅርቡ›› ማለት ነው (መዝ.፵፮፥፭)፡፡ ወንጌሉ ደግሞ፣ ማርቆስ ፲፮፥፲፬ እስከ ፍጻሜ ድረስ ሲኾን ቃሉም በነግህ ከተነበበው የወንጌል ክፍል ቃል ተመሳሳይነት አለው፡፡ ቅዳሴውም ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ሲኾን ይህ ቅዳሴ ከሦስቱ አካላት አንዱ የኾነውን የእግዚአብሔር ወልድን (የኢየሱስ ክርስቶስን) ዘለዓለማዊነት የሚያስረዳ፤ ሥጋዌዉን፣ ሕማሙን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤዉን፣ ዕርገቱንና ዳግም ምጽአቱንም የሚናገር በመኾኑ በዘመነ ትንሣኤ፣ በዘመነ ዕርገትና በበዓለ ኀምሳ ሰሙን ይቀደሳል፡፡

ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በቅዳሴዉ መጀመሪያ ላይ ሀልዎተ እግዚአብሔርንና ምሥጢረ ሥላሴን መሠረት በማድረግ ለእግዚአብሔር ምስጋና ካቀረበ በኋላ፣ ቍጥር ፴፩ ላይ ‹‹… ወበ፵ ዕለት አመ የዐርግ ሰማየ አዘዞሙ እንዘ ይብል ጽንሑ ተስፋሁ ለአብ፤ … ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በዐርባኛው ቀን በብርሃን፣ በሥልጣን፣ በይባቤ ወደ ሰማይ በሚያርግበት ጊዜ አብ የሚሰድላችሁ መንፈስ ቅዱስን እስክትቀበሉ ድረስ ከዚህ ቆዩ ብሎ አዘዛቸው፤›› በማለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ በኾነ ቋንቋ የጌታችንን ወደ ሰማይ ማረግና ለሐዋርያት የሰጠውን አምላካዊ ትእዛዝ ይናገራል (ሉቃ.፳፬፥፵፱)፡፡

ምንጭ

___________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: