የ EBS “ማሕተብ-አውልቍ” ቅሌት ብዙ የሚጠቁመን ነገር አለ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 27, 2020
ይህ EBS/ኢ.ቢ. ኤስ የሠራው ቪዲዮ ነው። ካሜራው ወደ አቃቂ አድቬንቲስት አዳሪ ተማሪ ቤት አምርቶ ነበር። እዚያም የተዋሕዶ ተማሪዎች ወደዚህ ተማሪ ቤት ለመግባት ማህተባቸውን መበጠስ አለባቸው ፥ ሙስሊሞቹ ግን ከእነ ሂጃባቸው መግባት ተፈቅዶላቸዋል።
ግን እያየን ነው፤ የአህዛብን፣ የመናፍቃንን እና የዘረኞችን በተዋሕዶ ላይ ያነጣጠረውን ሕብረት?! ተመሳሳይ ላባ ያላቸው ወፎች አንድ ላይ ይበራሉ ፥ ተኩላውም ቀስ በቀስ ለምዱን እየገፈፈ ነው።
ከጥቂት ዓመታት በፊት፤ በጥምቀት ከተራ ፪ሺ፱ ዓ.ም፡ እ.አ.አ በ1943 ዓ.ም በተቋቋመው የአቃቂ የአድቬንቲስት አዳሪ ተማሪ ቤት “ተማሪዎች” የሆኑት የተዋሕዶ ልጆች ከግቢው መውጣት ስላልተፈቀደላቸው፤ ወደ በሩ ተጠግተው፤ “የኛ!” እያሉ በመዘመር ለጥምቀት በዓል ከመንበራቸው በክብር የወጡትን ታቦታት ይቀበሏቸው ነበር። በወቅቱ ጠይቄ እንደተረዳሁት ከሆነ፡ የተዋሕዶ አዳሪ ተማሪዎች ውደ ትምህርት ቤቱ ሲመዘገቡ፡ ማሕተባቸውን እንዲያወልቁ ተደርገው ነው፤ አልያ መግባት አይችሉም።
የኢቢ ኤስ ቪዲዮ እራሱ እንደሚያሳየው መሀመዳውያኑ ግን ከነሂጃባቸው እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል፤ ጉድ የሚያሰኝ አሳዛኝ ጉዳይ ነው። በ21ኛው ክፍለ ዘመን ልክ እንደ ቅኝ ተገዢዎች ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው መብትና ምጫ የላቸውም ፤ የተዋሕዶ በሆነቸው በሃገረ ኢትዮጵያ! ያው እንግዲህ የደቡባውያኑ የእነ አፄ ኃይለ ሥላሴ ፈረንጅ አፍቃሪነትና ሁሉን አቃፊነት እምቧይና እሾህ አፍርቶ ይታያል።
Leave a Reply