Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2020
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    25262728293031
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for May 27th, 2020

የ EBS “ማሕተብ-አውልቍ” ቅሌት ብዙ የሚጠቁመን ነገር አለ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 27, 2020

ይህ EBS/.. ኤስ የሠራው ቪዲዮ ነው። ካሜራው ወደ አቃቂ አድቬንቲስት አዳሪ ተማሪ ቤት አምርቶ ነበር። እዚያም የተዋሕዶ ተማሪዎች ወደዚህ ተማሪ ቤት ለመግባት ማህተባቸውን መበጠስ አለባቸው ፥ ሙስሊሞቹ ግን ከእነ ሂጃባቸው መግባት ተፈቅዶላቸዋል።

ግን እያየን ነው፤ የአህዛብን፣ የመናፍቃንን እና የዘረኞችን በተዋሕዶ ላይ ያነጣጠረውን ሕብረት?! ተመሳሳይ ላባ ያላቸው ወፎች አንድ ላይ ይበራሉ ፥ ተኩላውም ቀስ በቀስ ለምዱን እየገፈፈ ነው።

ከጥቂት ዓመታት በፊት፤ በጥምቀት ከተራ ፪ሺ፱ ዓ.ም፡ እ..አ በ1943 .ም በተቋቋመው የአቃቂ የአድቬንቲስት አዳሪ ተማሪ ቤት “ተማሪዎች” የሆኑት የተዋሕዶ ልጆች ከግቢው መውጣት ስላልተፈቀደላቸው፤ ወደ በሩ ተጠግተው፤ “የኛ!” እያሉ በመዘመር ለጥምቀት በዓል ከመንበራቸው በክብር የወጡትን ታቦታት ይቀበሏቸው ነበር። በወቅቱ ጠይቄ እንደተረዳሁት ከሆነ፡ የተዋሕዶ አዳሪ ተማሪዎች ውደ ትምህርት ቤቱ ሲመዘገቡ፡ ማሕተባቸውን እንዲያወልቁ ተደርገው ነው፤ አልያ መግባት አይችሉም።

የኢቢ ኤስ ቪዲዮ እራሱ እንደሚያሳየው መሀመዳውያኑ ግን ከነሂጃባቸው እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል፤ ጉድ የሚያሰኝ አሳዛኝ ጉዳይ ነው። 21ኛው ክፍለ ዘመን ልክ እንደ ቅኝ ተገዢዎች ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው መብትና ምጫ የላቸውም ፤ የተዋሕዶ በሆነቸው በሃገረ ኢትዮጵያ! ያው እንግዲህ የደቡባውያኑ የእነ አፄ ኃይለ ሥላሴ ፈረንጅ አፍቃሪነትና ሁሉን አቃፊነት እምቧይና እሾህ አፍርቶ ይታያል

_________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አህዛብ፣ መናፍቃንና ዘረኞች ከኢትዮጵያ ምድር በእሳት ይጠረጋሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 27, 2020

እግዚአብሔር የጠራት የመንፈሣዊቷ ኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላቶች ሦስት ናቸው፦

  • 👉 1.አህዛብ
  • 👉 2.ዘረኞች
  • 👉 3.ግብረሰዶማውያን

[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፳፩፥፰]

ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።

______________________________

 

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , | 1 Comment »

በኢትዮጵያ ጽኑ መናወጥ ይሆናል፣ ይህም የአሜሪካን፣ አውሮፓንና አረቢያን ውድቀት ያስከትላል!!!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 27, 2020

ይህ ግሩም ትንቢትአዘል ትምህርት የቀረበው ከሦስት ዓመታት በፊት ነበር። በወቅቱ በሌላኛው ቻነሌ አቅርቤው ነበር። ከግማሽ ሚሊየን በላይ ክሊክ አግኝቶ ነበር። እግዚአብሔር ይይላቸውና በተዋሕዷውያን ዘንድ ተወዳጅ የነበረውን ቻኔሌን የግራኝ አብይ አህመድ ደጋፊዎች የሆኑት ተዋሕዶ ነንየሚሉ ግን እንደሚመስለኝ የተሀድሶየሆኑት ቻነሎች አዘግተውብኛል (“Semayat/ ሰማያት” + “ሉሌ ቋንቋየ ነሽየተባሉት)። የተዋሕዶ ልጆች፤ ተጠንቀቁ! የበግ ለመድ ከለበሱት ይሰውራችሁ!

በሃገራችን እየሆነ ያለው ሁሉ ይህ ነው!

👉 ከሦስት ዓመታት በፊት የሚከተለውን በጦማሬ ጽፌ ነበር

የኢትዮጵያችን ውድቀት የተጀመረው ከ 1500 ዓመታት በፊት፤ ሮማውያ ወኪሎቻቸው የሆኑትን እነ መሀመድ እና ተከታዮቹ ወደ ኢትዮጵያ ልከው ነገሥታቶቻችን ካታለሉበት ጊዜ ጀምሮ ነበር። ባለፉት 100 ዓመታትም ቢሆን፣ ነገሥታቶቻችን ላይ የምዕራባውያኑ እና የአረቦቹ ተጽእኖ በደንብ ይታይባቸው ነበር። የነግሥታቶቻችን አማካሪ ማጣትና መታለል ባለፉት 40 ዓመታት ኢአማኒያዊ እና እስላማዊ ለሆነው የመከፋፈያ መንገድ በሩን ከፍቷል። ላለፉት 40 ዓመታት ዓለማዊ ኢአማንያንና ሙስሊሞች ኢትዮጵያን ያስተዳድሯታል ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም።

በቅርቡ እንኳን፣ በስጋውያኑ ኤዶማውያ ምዕራባውያን እና እስማኤላውያን ልጆች ርኩስ ርዕዮተ ዓለማት የተታለሉት የአፄ ኃይለ ሥላሴ እና የክሎኔል መንግስቱ መስተዳደሮች(ልብ እንበል፡ መስተዳደር)ወሎን፣ ትግራይን እና ኤርትራን ለምዕራባውያኑ የዓየርጠባይ ቅየራ ቴክኖሎጁ በሩን በመክፈት ለአስቃቂ ድርቅና ረሃብ እንዲጋለጡ አደርገዋቸው ነበር። ልክ ይህን ድርጊት ከፈጸሙ በኋላ የኔቶ ሠራዊት በ”እርዳታ ሰጭነት” መልክ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ እንዲገባና ያዘጋጇቸውን የጊዜ ቦንቦችን በድብቅ እንዲቀብሩ አደረጉ። መንፈሳዊ ኢትዮጵያውያን የሆኑት የተዋሕዶ ልጆች በረሀብና በድርቅ ብዙ ተሰውተዋልአፄ ሚኒልክ የምወዳቸው ድንቅ ንጉሥ ቢሆኑም፤ ነገር ግን በአባታቸው በኩል ያገኙትን መንፈሳዊ ማንነት በመርሳት ስጋዊ የሆነውን የእናታቸውን ማንነት በመውሰዳቸው ከባዕዳውያኑ ስጋውያን(ከጣልያንና ጀርመን)ጋር በመቀራረባቸው በሃገረ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ድርቅና ረሃብ ተከስቶ ነበር። ምናልባት የመጀመሪያው፤ በጣልያኖች በኩል መርዛማ አጽዋትን ከውጭ አስመጥተው እንዲተከሉ በመፍቀዳቸው። በዚህም ድርቅና ረሃብ የተቀጠፉት መንፍሳውያኑ ኢትዮጵያውያን ነበሩ (የሰሚን ሸዋ፣ የቤተ አምሃራ እና የትግራይ ነዋሪዎች)። ይህም ለስጋውያኑ የጋላ ነገዶች ተከታታይ መስፋፋት አመቺ ሁኔታ ፈጥሯል።

ከታሪክ ለመማር ፈቃደኞች አይደለንምና ሰሜን ኢትዮጵያ ወይም ኤርትራ ከእናቷ እንደተቆረሰችም፣ የ ጠ/ምኒስትር መለስ ዜናዊ (ነፍሳቸውን ይማርላቸው!)እና ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለምዕራባውያኑ እና ለአረቦቹ በገቡላቸው ቃል መሠረት፤ “ባድሜ የኛ ነው” በሚል ሰበብ በሚሊየን የሚቆጠሩ መንፈሳውያኑ ክርስቲያን ኢትዮጵያውያንን በድጋሚ ለመሰዋት በቅተዋል።

ሚቀጥለው የእብዶች ዙር ደግሞ እስካሁን በጦርነቱም ሆነ በረሃቡ ጉዳት ያልደረሰባቸውና ከሰሜኑ ጋር ሲወዳደር እምብዛም ደማቸው ያልፈሰሰውና “ተበድላችኋል!“ እየተባሉ፡ ልክ እንደ አረብ ፍልስጤሞች የተበዳይነት ካርድ እንዲጫወቱ የተደረጉት ኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችንን ነው በመጠቀም ላይ ያሉት። ይህ ታዲያ በጣም አያሳዝንም? መቼ ነው የምንማረው? ያሰኛል። በመጽሐፍ ቅዱሳችን፡ እግዚአብሔር “ሕዝቤ እውቀት ከማጣት የተነሳ ጠፍቷል።ያለዉ ይህን ለማናስተውል ህዝቦች መሆኑ ነው።

ባጭሩ፡ የጨካኞቹ ኤዶማውያእና እስማኤላውያን መንፈስ አገራችን ከገባበት ጊዜ አንስቶ ባልሆነ ነገር እርስበርስ ለመከፋፈል ስለበቃን ሳንወድ በግድ ከጠላቶቻችን ጋር እንደንመሳጠር፣ ለእነርሱ የረጅም ጊዜ የጥፋት ሤራ እንድንጋለጥ ተደርገናል። እግዚአብሔር ከሌላ ደም መፋሰስ ይጠብቀን፡ ነገር ግን ከመጣም፤ ኢትዮጵያውነታቸውንና ክርስቶስን የካዱት እንዲሁም በኢትዮጵያ ላይ ሰይፋቸውን የመዘዙት ሁሉ ፍርክስክሳቸው ለመጨርሻ ጊዜ መሬት ውስጥ ተቀብሮ ይቀራል። በዚህ አንጠራጠር!”

👉[ወደ ገላትያ ሰዎች ምዕራፍ ፬፥]

  • ፳፰ እኛም፥ ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጆች ነን።
  • ፳፱ ነገር ግን እንደ ሥጋ የተወለደው እንደ መንፈስ የተወለደውን በዚያን ጊዜ እንዳሳደደው ዛሬም እንዲሁ ነው።
  • ነገር ግን መጽሐፍ ምን ይላል? የባሪያይቱ ልጅ ከጨዋይቱ ልጅ ጋር አይወርስምና ባሪያይቱን ከልጅዋ ጋር አውጣት።
  • ፴፩ ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ የጨዋይቱ ልጆች ነን እንጂ የባሪያይቱ አይደለንም።

_____________________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: